ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል አጀንዳ ለማሰባሰብ ክልሉን ወክለው ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ቢደረግም፣ እስካሁን የሚፈለገው ውጤት እንዳልመጣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
በክልሉ አስተማማኝ እና የተረጋጋ ሰላም ባለመኖሩ ምክንያት፣ እስካሁን በቦታው በአካል ተገኝቶ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ማከናወን እንዳልተቻለ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከሕወሃት አመራር፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበራት፣ ከጋዜጠኞች እና ይመለከታቸዋል ከተባሉ ሌሎች ተቋማት ጋር ከ22 ጊዜ በላይ ተደጋጋሚ ውይይቶችን ቢያደርግም፤ እስካሁን ድረስ ወደ ተግባር መግባት የሚያስችል ውጤት አልተገኘም ብለዋል።
በዚህም ምክንያት ኮሚሽኑ የመጨረሻ አማራጭን በመጠቀም፣ በአዲስ አበባ ከተማ ከትግራይ ተወላጆች ጋር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ማከናወኑን ፕሮፌሰሩ አስታውሰዋል።
በውይይቱ ላይም በቀጥታ ከትግራይ ክልል የመጡ 300 ተሳታፊዎች እና በአዲስ አበባ የሚኖሩ 400 የክልሉ ተወላጆች በጥቅሉ 700 ሰዎች መሳተፋቸውን ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ ሁሉንም አካላት ያካተተ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ በትግራይ ክልል ያለውን ተሳትፎ ለማረጋገጥ ሰፊ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ አስታውቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ግንባታቸው ከ80 በመቶ በላይ ያልተጠናቀቁ ሪል እስቴቶች ለሽያጭ እንደማይቀርቡ ተገለጸ
ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅን ለማፅደቀ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ... read more
ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋ ለቻይና ልትልክ ነው
ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋ ለቻይና ልትልክ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አስታወቀ።
የኢፌደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች... read more
በአማራ ክልል በተያዘው መጋቢት ወር መጨረሻ የአጀንዳ ማሰባሰብ እንደሚጀመር ተገለጸ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመጋቢት ወር መጨረሻ ቀናት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
በመሆኑም የወረዳ... read more
የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭት ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ሊስፋፋ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 08 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭትን ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ለማስፋፋት ዝግጅት... read more
ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ እስከ 2029 የማድሪድ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚቀጥሉ ታወቀ
ስኬታማ የቢዝነስ ሰው እና የክለብ ፕሬዚዳንት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ሮድሪጌዝ ለተጨማሪ 4 አመት የማድሪድ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚያገለግሉ በፊርማቸው አረጋግጠዋል።
ለፉክክር... read more
የምክር ቤት አባላት የሚከፈለን ወርሃዊ ደመወዝና አበል በቂ አይደለም አሉ
ሰኔ 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ ልዩ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች... read more
የአሜሪካው 82ኛው የአየር ወለድ ክፍለ ጦር ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመዝመት በተጠንቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ
መጋቢት 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታገን) በዓለም ላይ በፈጣን ደራሽነቱ የሚታወቀው 82ኛው የአየር ወለድ ክፍለ ጦር (82nd... read more
የኢትዮጵያ መድሃኒት አምራቾች የፋይናስ ችግርን ለመፍታት ከባንኮች ጋር ዳግም ስምምነት ሊደረግ ነዉ ተባለ
በኢትዮጵያ የሚገኙ 13 የመድሃኒት አምራች ፋብሪካዎች የፋይናንስ ችግራቸው ከተፈታ እንደ ሀገር አሁን ላይ ከሚሸፍኑት 30 በመቶ ወደ 60 በመቶ ከፍ... read more
አንድ ታይላንዳዊ ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ መጸዳጃ ቤት ሲጠቀም የዘር ፍሬውን በእባብ ተነከሰ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ35 ዓመት ወጣት ታይላንዳዊ ሰው በኖንታቡሪ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ የመታጠቢያ ክፍል ውስጥ መጸዳጃ ቤት ውስጥ... read more
ምላሽ ይስጡ