ሕዳር 11 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኒውሮሎጂስቶች ማኅበር 30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን በዛሬው ዕለት አክብሯል፡፡
የኢትዮጵያ ኒውሮሎጂስቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት እና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኒውሮሎጂስት ዶክተር ሰብለወንጌል አስማረ ማኅበሩ ሲቋቋም የባለሙያዎች ቁጥር አነስተኛ እንደነበር አስታውሰው፤ ነገር ግን ማኅበሩ ከተቋቋመ ከ10 ዓመታት በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥር የኒውሮሎጂ ዲፓርትመንት ከተከፈተና የትምህርት መርሐ ግብር ከተጀመረ ወዲህ መሻሻሎችን አሳይቷል ብለዋል፡፡ በዚህም በሀገሪቱ ከ100 በላይ ኒውሮሎጂስቶችን ማፍራት ቢቻልም፣ ከአፍሪካ አንጻር ከፍተኛ ቁጥር ቢሆንም ከሕዝብ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር አሁንም ዝቅተኛ እንደሆነ ያነሳሉ።
በአሁኑ ወቅት አንድ ኒውሮሎጂስት ለ1.5 ሚሊዮን ሕዝብ የሚደርስ ሲሆን፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አዳዲስ ተመራቂዎች ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመሰማራት አገልግሎት ቢጀምሩም አብዛኛው ባለሙያ አሁንም በዋና ከተማዋ የሚገኝ በመሆኑ አገልግሎቱ በቂና ተደራሽ አለመሆኑን አስታውቀዋል።
በተለይ እንደ ስትሮክ፣ ኢፒሌፕሲ፣ የፓርኪንሰን ሕመም፣ የራስ ምታትና የወገብ ሕመም ያሉ በርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የሚጎዱ ችግሮችን በመጀመሪያ ደረጃ ለማከምና ሪፈር ማድረግ ሲገባ መቼና እንዴት መከናወን እንዳለበት ግልጽ ለማድረግ መመሪያው ወሳኝ እንደሚሆን ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ኒውሮሎጂስቶች ማኅበር ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ከሕክምና መመሪያው በተጨማሪ የነርቭ ሕመሞች አገልግሎትን ለማጠናከር የሚያግዙ ሌሎች በርካታ ሥራዎችንም እያከናወነ መሆኑ ተመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ