ጥቅምት 18 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሩሲያ ሰንደቅ ዓላማ በገነነበት እና አለማቀፍ የመከላከያ ተንታኞች ትኩረት በሳበው ታሪካዊ ክንውን፣ በዓለም ላይ ካሉ እጅግ ዘመናዊ እና ኃይለኛ የረጅም ክልል አየር መከላከያ ስርአቶች ግንባር ቀደም የሆነው ኤስ-400 ትሪምፍ (S-400 Triumf) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን መቀላቀሉ ይታወቃል።
ሩሲያ ያመረተችው ይህ የላቀ መከላከያ ቴክኖሎጂ የአየር ክልል ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ የሀገሪቱን የመከላከል አቅም ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋገር እንደሆነ ታምኖበታል።
ስርአቱ አራት መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ዒላማዎችን የመቆጣጠር እና የማጥፋት ብቃት ያለው በመሆኑ፣ የሀገሪቱን ሰማይ ከማንኛውም ያልተጠበቀ የአየር ላይ ስጋት በብቃት ለመጠበቅ ያስችላል።
በተለይም ዘመናዊ የጦር ጄቶች፣ ስልታዊ የቦንብ አውሮፕላኖች፣ ሰው አልባ ድሮኖች እንዲሁም ከባቢ አየርን ጥሰው የሚገቡ የባለስቲክ እና የክሩዝ ሚሳይሎችን በአንድ ጊዜ ለይቶ የመታገል አቅም ያለው መሆኑ ለዚህ ቴክኖሎጂ ልዩ ግርማ ሞገስ ሰጥቶታል።
ከዚህም በላይ እጅግ የረቀቀ የራዳር መረብ የተገጠመለት በመሆኑ፣ በራዳር በቀላሉ የማይታዩ እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚሾልኩ የጠላት ጄቶችን ጭምር ለይቶ ማወቅ እና መከታተል ያስችለዋል።
በተንቀሳቃሽ መኪኖች ላይ ተገጥሞ የሚዘለቀው ይህ ስርአት፣ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ በፍጥነት ቦታውን በመቀየር ከጠላት ጥቃት መጠበቅ እና ስልታዊ በሆነ መንገድ መዘርጋት የሚችል መሆኑ ለዘመናዊው ጦርነት ስልት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
የዚህ ኃይለኛ አየር መከላከያ ስርአት መታጠቅ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ መረጋጋትን በልበ ሙሉነት ለማረጋገጥ እና የሰላም ማስከበር አቅሟን ከፍ ለማድረግ ታላቅ ምዕራፍ እንደሆነ የዘርፉ ተንታኞች ይስማሙበታል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ