ጥቅምት 19 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው የህዋ ምርምር ማዕከል (NASA) ከአውሮፓ ህዋ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በሰው አካል ላይ የረጅም ጊዜ የህዋ ጉዞ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለማጥናት የሚያስችል የምርምር መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል።
ይህ “Bed Rest Study” በመባል የሚታወቀው ጥናት በህዋ ውስጥ ባለው አነስተኛ የስበት ኃይል ምክንያት በሰው አካል፣ በጡንቻዎች፣ በአጥንት እና በደም ዝውውር ላይ የሚፈጠሩ ለውጦችን በጥልቀት ለመረዳት ያለመ ነው።
በዚህ ጥናት ላይ የሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ለ60 ቀናት ያህል ሙሉ በሙሉ ከአልጋ ሳይነሱ እንዲቆዩ ይደረጋል። በቆይታቸው ወቅት መመገብን፣ መታጠብን እና መጸዳዳትን ጨምሮ ሁሉም እንቅስቃሴዎች አልጋ ላይ ሆነው የሚከናወኑ ሲሆን፣ የደም ዝውውሩ በህዋ ውስጥ ያለውን ሁኔታ እንዲመስል አልጋው በስድስት ዲግሪ ማዕዘን ዘንበል ብሎ ተዘጋጅቷል።
ለዚህ ከፍተኛ አካላዊ እና አእምሮአዊ ፈተና ለሚወስዱ ተሳታፊዎች ተቋሙ ከ18,000 እስከ 19,000 የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የገንዘብ ካሳ እና አበል ይከፍላል።
ይሁን እንጂ በጥናቱ ለመሳተፍ ከፍተኛ የጤና ምርመራዎችን ማለፍ፣ የቋንቋ እና የነዋሪነት መስፈርቶችን ማሟላት እንዲሁም ከጥናቱ በኋላ የሚደረጉ አስገዳጅ የጡንቻ ማገገሚያ ስልጠናዎችን ማጠናቀቅ ግዴታ ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ