ጥቅምት 09 ቀን 2019 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከህወሓት እና አጋሮቹ የማረካቸውን የጦር መሳሪያዎች ለተለያዩ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ማስጎበኘቱ በጦር ሜዳ የተገኘውን ድል በፖለቲካና ዲፕሎማሲ መድገም መሆኑን የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
በዲላ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ ዶክተር አብዱ መሀመድ ይህ ዓይነቱ አካሄድ በዓለም አቀፍ መድረክ የተለመደ መሆኑን በመግለጽ፣ ወታደራዊ ድል በዲፕሎማሲና ፖለቲካ ካልታጀበ ሙሉ አይሆንም ብለዋል።
በታሪክ አጋጣሚዎች ከዚህ ቀደም በጦር ሜዳ የተገኘው ወታደራዊ ድል በዲፕሎማሲና ፖለቲካ ባለመታጀቡ ኢትዮጵያ ዋጋ የከፈለችባቸውን ጊዜያት በማስታወስ፣ የአሁኑ እርምጃ ከዚያ ትምህርት የተወሰደበትና የዲፕሎማሲ የበላይነትን ለመያዝ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የጦር መሳሪያ በሚያቀብሉ እና በሚሸጡ ሀገራት ላይ ጫና ለማሳደር ትልቅ ጉልበት እንዳለው አስምረውበታል።
ጉብኝቱ ቀጠናውን ወደ ትርምስና አለመረጋጋት ለማስገባት ታጣቂዎችን ሲያስታጥቁ ለነበሩ ሀገራት ያለው መልዕክት ጉልህ ነው ያሉት ደግሞ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ አበራ ሄፕሶ ናቸው።
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በግብፅ አስተባባሪነት አካባቢውን በትርምስ ውስጥ ለማቆየት የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንዲረዳ ያደርጋል ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ መመለስ ያለውን ፋይዳ ለማሳየት ይረዳል ባይ ናቸው።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ ኢትዮጵያ ከተገንጣዮችና ሽብርተኞች ካሏቸው ኃይሎች ራሷን ለመከላከል ተመጣጣኝ ምላሽ እየወሰደች መሆኑን አሜሪካ እንደምትረዳ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የህብረት ስራ ሸማች ማህበራት ያሉበት ደረጃ ወቅታዊ ሁኔታውን እንደማይመጥን የፌደራል የህብረት ስራ ኮሚሽን ገለጸ
የህብረት ስራ ሸማች ማህበራት አምራቹ ምርቶችን በተገቢው ዋጋ ለገበያ እንዲያቀርብ፤ ሸማቹም አላስፈላጊ በሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይጎዳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የፌደራል... read more
ስኳር ፋብሪካዎች ከክረምት ጥገና በኋላ መደበኛ ስኳር የማምረት ሥራ መጀመራቸው ተገለጸ
ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት መግባት ጋር ተያይዞ አጠቃላይ የጥገና ሥራ ሲያከናውኑ የቆዩት ስኳር ፋብሪካዎች መደበኛ... read more
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ለስፔስ ኤክስ (SpaceX) መስራች ኢሎን መስክ ከፍተኛ የመንግሥት የክብር ሜዳሊያ አበረከቱ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ የስፔስ ኤክስ (SpaceX) ባለቤት ለሆኑት ኢሎን መስክ የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሜዳሊያ... read more
በ30 ሚሊዮን ዶላር የተሠራው የአርቴሚስ 2 የጠፈር መንኮራኩር ሽንት ቤት በመንገድ ላይ ብልሽት አጋጠመው
መጋቢት 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ወደ ጨረቃ በመጓዝ ላይ የሚገኘው የአርቴሚስ 2 (Artemis II) የጠፈር መንኮራኩር፣ ጉዞ ከጀመረ ጥቂት ሰዓታት በኋላ... read more
በካናዳ ቅዝቃዜውን የሚያቀልሉ ‘የልብስ ደኖች’፡ ለችግረኞች የሚቀርብ ልብ የሚነካ የሙቀት ስጦታ
መስከረም 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በካናዳ በክረምቱ ወቅት ሰዎችን ከብርድ ለመጠበቅ ያለመ “የልብስ ደኖች” የሚል ልብ የሚነካ ሰብአዊ ተነሳሽነት በመላ... read more
በሸዋሮቢት ከተማና አካባቢው የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉ ተገለጸ
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት በአካባቢው አጥፊው የግሪሳ ወፍ መከሰቱን መግለጹ ይታወቃል።... read more
ጤናማ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ምን ታስቧል?
👉
https://youtu.be/FZBLR3gfBf0
read more
የኢትዮጵያ መድሃኒት አምራቾች የፋይናስ ችግርን ለመፍታት ከባንኮች ጋር ዳግም ስምምነት ሊደረግ ነዉ ተባለ
በኢትዮጵያ የሚገኙ 13 የመድሃኒት አምራች ፋብሪካዎች የፋይናንስ ችግራቸው ከተፈታ እንደ ሀገር አሁን ላይ ከሚሸፍኑት 30 በመቶ ወደ 60 በመቶ ከፍ... read more
ያላገቡ ሰራተኞች እንዲያጋቡ ቀነ-ገደብ ያስቀመጠው የቻይና ኩባንያ ለቀረበበት ትችት ምላሽ ሰጠ
እስከ መስከረም መገባደጃ ያላገቡ ሰራተኞችን ጋብቻ ካልፈጸሙ የስራ ዉል እንደሚያቋርጡ የሚያስፈራራ ፖሊሲ ያስተዋወቀው በቻይና የሚገኝ አንድ ኩባንያ ማሳሰቢያውን አንስቻለሁ ብሏል።
በምስራቅ... read more
ምላሽ ይስጡ