ታዋቂው የቱርክ የሕክምና ተቋም አጂባደም በኢትዮጵያ ለሚገኙ ታካሚዎች ቀጥተኛ የመረጃና የድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥበትን አዲስ የሕክምና መረጃ ቢሮ በአዲስ አበባ በይፋ መክፈቱን አስታወቀ።
ይህ ቢሮ ታካሚዎች ወደ ውጭ ሀገር ሳይጓዙ በሀገር ውስጥ ሆነው የሕክምና አማራጮችን እንዲያገኙና ሂደታቸውን እንዲያመቻቹ ትልቅ እገዛ ያደርጋል። በዚህም መሠረት ታካሚዎች የሕክምና ሰነዶቻቸውን በማቅረብ ከቱርክ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ነፃ ሙያዊ አስተያየት እና የምክር አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።

አዲሱ ቢሮ በዋናነት በሚከተሉት የሕክምና ዘርፎች ዙሪያ መረጃና ቅድመ-ዝግጅት ያመቻቻል፦
• የካንሰር ሕክምና (ኦንኮሎጂ)
• የኩላሊትና ጉበት ንቅለ-ተከላ
• የኪስና አጥንት (ኦርቶፔዲክስ) ሕክምና
• የልብ ሕክምና
• የመካንነት (IVF) ሕክምና
ከሕክምና በፊት ያሉ የጉዞ ሂደቶችን ከማመቻቸት ባለፈ፣ ቢሮው ታካሚዎች ከሕክምና መልስ የሚያደርጉትን የቅርብ ክትትል ያቀልላል። የአጂባደም የሕክምና የታካሚዎች መረጃ ማዕከል የሚገኘው በቦሌ ኤድናሞል አለፍ ብሎ በሴንቸሪ ህንፃ ካሜሮን መንገድ ላይ ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ