መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚው በአቶ አንዋር አብራር በኩል ባወጣው ይፋዊ የሚዲያ መግለጫ፣ ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ባከናወነው ሰፊ ሥራ በጉራጌ ዞን በእኖር እና እዣ ወረዳዎች የሚገኙ 19 የገጠር መንደሮችን በበዓሉ ዋዜማ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል። ቀድሞም ቢሆን በደማቅ የመስቀል በዓል አከባበሩ የሚታወቀው አካባቢው፣ አሁን ደግሞ በእነዚህ መንደሮች ኤሌክትሪክ መግበቡ የበዓሉን አከባበር ይበልጥ ያሳምረዋል ተብሏል። ይህን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ ለሥራው ስኬትም 25.92 ኪሎ ሜትር መካከለኛ እና 38 ኪሎ ሜትር ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል። በፕሮጀክቱ 2 ሺህ 295 የሚጠጉ ቆጣሪዎች የተገጠሙ ሲሆን፣ በአንድ ቆጣሪ አማካይ 5 የቤተሰብ አባላት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ በተሰላው መሠረት 11 ሺህ 475 ዜጎችን የመብራት ባለቤት ማድረግ ተችሏል። በተጨማሪም ከወጣው አጠቃላይ ወጪ ውስጥ 40 ሚሊዮን የሚሆነው በሕብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜት የተሸፈነ መሆኑ የሕዝብና የተቋሙን አብሮነት ድንቅ ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ የልማት ሥራ የአካባቢውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማነቃቃትና በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና ከመጫወቱም በላይ፣ የዘንድሮውን የመስቀል በዓል ለነዋሪዎቹ ልዩ እንደሚያደርገው ይጠበቃል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በበዓል ወቅት የሚያጋጥሙ ሃሰተኛ የብር ኖት ስርጭት እና ህገ ወጥ ግብይትን ለመቆጣጠር ዲጂታል የመገበያያ አማራጮችን መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ
ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) መጪውን የገና በዓል አስመልክቶ በሚደረገው ግብይት ህገ ወጥ የንግድ እና የማጭበርበር እንቅስቃሴ እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ማድረግ... read more
በበጀት ዓመቱ 5 ወራት ከ47 ሺህ በላይ አዲስ ነጋዴዎች ወደ ንግድ ስርዓቱ ሲገቡ፤ ከ15 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከንግድ ስርዓቱ መውጣታቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሐምሌ ወር ጀምሮ በከተማዋ 15 ሺህ 99 ነጋዴዎች ከንግድ ስርዓቱ መውጣታቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ... read more
የትግራይ ህዝብ ጦርነት ይብቃ፤ሰላም ይስፈን እያለ በአደባባይ ሐሳቡን መግለጹን ቀጥሏል ተባለ
ሐምሌ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትላንትናው ዕለት በትግራይ ክልል ደቡብዊ ዞን በምትገኘው መኾኒ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሒዷል።
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የዲሞክራሲያዊ... read more
ሰበር ዜና | የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የቀድሞዋን የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን አዲስ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ኃላፊነት ላይ ሾሙ!
ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፥ የቀድሞዋን የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን በምስራቅ አፍሪካ... read more
አውስትራሊያ ያረጁ ጎማዎችን ወደ ባቡር ሀዲድ አስደንጋጭ መምጠጫ በመቀየር የጥገና ወጪን እየቀነሰች ነው ተባለ
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አውስትራሊያ የባቡር ሀዲድ ጥገና ወጪን ለመቀነስ እና የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ ዘዴ ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን... read more
የህፃናትን መብት እና ደህንነት ለማስጠበቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የአፍሪካ ህፃናት ቀንን ምክንያት በማድረግ ህፃናት ከፍተኛ ትኩረትን የሚሹ እንደመሆናቸው በቢሮ ደረጃ... read more
በጨረቃ ላይ ውሃ ተመረተ
ሐምሌ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቻይና ሳይንቲስቶች የጨረቃን አፈር በመጠቀም ከ50 ኪሎ ግራም በላይ ውሃ ማምረት መቻላቸውን ይፋ አደረጉ።
ይህ ታላቅ... read more
በአዲስ አባባ ከተማ ከህንጻ ተደራሽነት ጋር በተያያዘ ግልጽ የአቤቱታ ማቅረቢያ መድረክ አዘጋጅቶ መፍትሔ እያሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ
በመዲናዋ በህንጻ ተደራሽነት ዙሪያ ግልጽ የአቤቱታ ማቅረቢያ መድረክ ተዘጋጅቶ አካል ጉዳተኞች ለመንግስት አመራሮች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ ማግኘታቸውን ኮሚሽኑ ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ... read more
23 ሚሊዮን አሜሪካውያን የቸኮሌት ወተት የሚመጣው ከቡናማ ላሞች ነው ብለው ያምናሉ ተባለ
ሐምሌ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)23 ሚሊዮን አሜሪካውያን የቸኮሌት ወተት የሚመነጨው ከቡናማ ቀለም ካላቸው ላሞች ነው ብለው እንደሚያምኑ ተገለጸ። ይህ መረጃ... read more
የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ በArtificial Intelligence ለማዘመን ያለመው ግዙፉ “ሁዋዌ ፋይናንስ ሰሚት 2026” በአዲስ አበባ ተካሄደ
ሰኔ 16 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የዓለማችን የቴክኖሎጂ ተቋም የሆነው ሁዋዌ (Huawei Ethiopia Enterprise Business Group) የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ወደ ዲጂታል... read more
ምላሽ ይስጡ