መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚው በአቶ አንዋር አብራር በኩል ባወጣው ይፋዊ የሚዲያ መግለጫ፣ ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ባከናወነው ሰፊ ሥራ በጉራጌ ዞን በእኖር እና እዣ ወረዳዎች የሚገኙ 19 የገጠር መንደሮችን በበዓሉ ዋዜማ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል። ቀድሞም ቢሆን በደማቅ የመስቀል በዓል አከባበሩ የሚታወቀው አካባቢው፣ አሁን ደግሞ በእነዚህ መንደሮች ኤሌክትሪክ መግበቡ የበዓሉን አከባበር ይበልጥ ያሳምረዋል ተብሏል። ይህን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ ለሥራው ስኬትም 25.92 ኪሎ ሜትር መካከለኛ እና 38 ኪሎ ሜትር ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል። በፕሮጀክቱ 2 ሺህ 295 የሚጠጉ ቆጣሪዎች የተገጠሙ ሲሆን፣ በአንድ ቆጣሪ አማካይ 5 የቤተሰብ አባላት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ በተሰላው መሠረት 11 ሺህ 475 ዜጎችን የመብራት ባለቤት ማድረግ ተችሏል። በተጨማሪም ከወጣው አጠቃላይ ወጪ ውስጥ 40 ሚሊዮን የሚሆነው በሕብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜት የተሸፈነ መሆኑ የሕዝብና የተቋሙን አብሮነት ድንቅ ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ የልማት ሥራ የአካባቢውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማነቃቃትና በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና ከመጫወቱም በላይ፣ የዘንድሮውን የመስቀል በዓል ለነዋሪዎቹ ልዩ እንደሚያደርገው ይጠበቃል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ጃፓን ከህዋ የፀሐይ ኃይልን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመቀየር ሙከራ ልታደርግ ነው
መስከረም 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ጃፓን የፀሐይን ኃይል ከምድር ምህዋር ላይ ያለገደብ አሰባስቦ በገመድ አልባ መንገድ ወደ ምድር የማስተላለፍ ታሪካዊ ሙከራ... read more
በመሬት የይዞታ ማረጋገጥ ስራ ላይ ለሚነሱ ችግሮች በወረቀት ያለው ሰነድ ህጋዊ ሆኖ እንደሚቀርብ ተገለጸ
ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ላይ በዲጅታልና በወረቀት ሆኖ በሚቀርብበት ወቅት የሚፈጠሩ ቅሬታዎችና ክፍተቶች ካሉ... read more
የባህሬን ወደብ፤የአሜሪካ የባህር ኃይል መርከቦች ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ
የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ኃይል ንብረት የሆኑ ሁሉም የፊት መስመር መርከቦች ከባህሬን ቁልፍ ወደብ መውጣታቸውን የሳተላይት ምስሎች ማሳየታቸውን ኒውስዊክ ዘግቧል። ይህ... read more
ኢትዮጵያ በታሪክ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጉ ሴቶች ቢኖሯትም እዉቅና የመስጠት ልማዳችን ዝቅተኛ ነዉ ተባለ
መጋቢት 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በታሪክ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጉ ሴቶች እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁሟሉ፡፡ የታሪክ ባለሙያው አቶ በላይ ስጦታው እንደሚሉት ኢትዮጵያ... read more
ኢትዮጵያ ወጣቱን ያማከለ የዲፕሎማሲ አውድን መፍጠር እንዳለባት ተገለጸ
ወጣቱን በዲፕሎማሲው ዘርፍ ለማብቃት ወጥ እና ተከታታይነት ያለው ስልጠናዎችን መስጠት፤ ተቋማትንም ማደራጀት ይገባል ተብሏል፡፡
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና አለም አቀፍ ግንኙነት... read more
ከሰሞኑን በጸደቀው አዋጅ 1387/2017 መሰረት የሚደረገው ምርመራ ከመደበኛው የወንጀል ምርመራ ሂደት በተለየ ዘዴ መሆኑ ተገለጸ
ሰኔ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የቀድሞውን አዋጅ 780/2005ን ለማሻሻል የወጣው እና ሰኔ 10/2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው አዋጅ 1387/2017... read more
ቤጂንግ፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በትብብር ላይ ያተኮረ ወዳጃዊ ውይይት ጀመሩ
ግንቦት 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በቤጂንግ ባደረጉት ታሪካዊ መድረክ እጅግ ሞቅ... read more
ተጠባቂዎቹ ፍልሚያዎች በቀጣይ ወር ይከናወናሉ
የድብልድ ማርሻል አርት ክህሎት ያላቸው ተፋላሚዎች በየክብደት እርከናቸው ተከፋፍለው የሚያከናውኑት የፍልሚያ አለም በተለምዶ Professional fighters league ወይም PFl የፍልሚያ ጨዋታዎች... read more
36 ያህል ተጨማሪ የቅዳሜና እሁድ ገበያ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ነዋሪዎች እየገቡባቸው ባሉ አዳዲስ መንደሮች ላይ ተጨማሪ 36 የቅዳሜና እሁድ ገበያ ሊጀመር እንደሆነ የአዲስ አበባ... read more
የሴቶችን የአመራርነት ተሳትፎ የማሳደግ ስራ በሚፈለገው ልክ አይደለም ተባለ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን፤ ብቁ የትምህርት ደረጃ እና የስነ አመራር... read more
ምላሽ ይስጡ