መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ በተካሄዱ ጦርነቶች ምክንያት የመጣውን ጉዳት በመገንዘብ፣ ዳግም ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ መስራት እንደሚገባ የሀገር ሽማግሌ ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ ተናግረዋል፡፡ ሁሉም ዜጎች “ጦርነት አያስፈልግም” ቢሉም፣ ወደ ችግሩ ሲገባ ግን እየተስተዋለ መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰር አህመድ፣ ችግር መፍታት ላይ ሁሉም በኃላፊነት መስራት ይገባዋል ብለዋል፡፡ በተለይም ወጣቱ የልማት ሰራዊት ለመሆን መስራት እንደሚገባውና ባሳለፍነው የሰሜኑ ጦርነት ወጣቱ ከማንም በላይ ተጎጂ በመሆኑ፣ ይህን በመገንዘብ ለሰላም መስራት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተውበታል፡፡ ከሃይማኖት አባቶች ጋር በመተባበር በሀገሪቱ ሰላም እንዲረጋገጥ እየሰሩ መሆናቸውን የሚናገሩት በኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት ጉባኤ ሴቶች ላይ የሚሳተፉት ወ/ሮ መአዛ በቀለ፣ ከምንም በላይ ስለ ሀገርና ስለ ቤተሰብ ማሰብ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ “ጦርነት የሚመጣውን ችግር በጣም የተረዳ ህዝብ ነው” የሚሉት ወ/ሮ መአዛ፣ በዚህ ላይ እናቶች ሰላም እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ችግሮችን በውይይትና በመነጋገር መፍታት ይገባል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ያሏትን የሰላም እሴቶች ተጠቅማ ችግሮች እንዲፈቱ መስራት እንደሚገባም ተመልከቷል፡፡ ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ቢሮው በሕዝቡ ፍላጎት ላይ መሰረት ባደረገው ጥናት 46 አዳዲስ የሚከፈቱና 12 መራዘም ያለባቸው የትራንስፖርት መስመሮች መለየታቸውን አስታወቀ
መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተጠቃሚ ያላቸው ነገር ግን ከአውቶቡስ ውጭ ምድብተኛ የሆነ የታክሲ አገልግሎት... read more
ባለፉት ስምንት ወራት ለ20 ሚሊየን ዜጎች የወባ ምርመራ ተደርጎላቸዉ 8.2 ሚሊየን የሚሆኑት በደማቸዉ ዉስጥ ወባ መገኘቱ ተገለጸ
አለም አቀፉ የወባ ቀን የፊታችን ሚያዝያ 17 ቀን 2017 በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ኹነቶች እንደሚከበር በተገለጸበት የጤና ሚኒስቴር መግለጫ ላይ የጤና... read more
ከደረሰኝ ጋር የተገናኙ ጠቅላላ ወንጀሎች
👉ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሃያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50... read more
ሚኒ ፓኪው ወደ ቦክሱ አለም እንደሚመለስ አሳውቋል
በ2021 የቦክስ ጓንቱን የሰቀለው አንጋፋው ቡጢኛ ማኒ ፓኪው ከስፖርቱ ራሱን አግልሎ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተጠምዶ በሀገሩ ፊሊፒንስ ከ2016-22... read more
የመሬት መብቶችን ማረጋገጥ ለዜጎች ኑሮ መሻሻል ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
ታህሳስ 16 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ላንድ ፎር ላይፍ ኢትዮጵያ (Land for Life Ethiopia) "የመሬት አስተዳደርን ማጠናከር እና የመሬት መብቶችን... read more
ያልተገባና መሠረት የሌለው መግለጫ የሚያሰራጩ አካላት እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ለአንዴየና ለመጨረሻ ጊዜ በጥብቅ አሳስቧል
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5... read more
ሳይንቲስቶች ከጨረቃ አፈር ውኃና ኦክሲጅን በፀሐይ ብርሃን በማውጣት አዲስ ግኝት አስመዘገቡ
በጨረቃ ላይ መኖር ይቻል ይሆን?
ሐምሌ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሳይንቲስቶች ከጨረቃ አቧራ (regolith) ውኃና ኦክሲጅንን በፀሐይ ብርሃን ብቻ ማውጣት የሚያስችል አዲስ... read more
የጦር መሳሪያዎችን በአግባቡ ማስተዳደር የሚያስችል አሰራር እየተቀረጸ ነዉ ተባለ
ታኅሳስ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝዉዉር በየጊዜዉ እየጨመሩ ካሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶች መካከል እንደሆነ ይገለጻል፡፡
የፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ... read more
በአዲስ አበባ ከተማ የዩኒቨርሲቲ መንደር ሊገነባ መታቀዱ ለትምህርት ዘርፉ መነቃቃትን የሚያመጣ ነው ተባለ
ጣቢያችን ያነጋገራቸው የከተማ ልማት እና የኪነ ህንጻ ባለሙያ አቶ ቤንጀዲድ ሃይለሚካኤል ለአንድ ከተማ ከሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች ውስጥ አንዱ የትምህርት ተቋም... read more
ምላሽ ይስጡ