መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሃገር ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚል ዜጋ ሁሉ በቅድሚያ የሃገርን ሰላም ማስጠበቅና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ማንሳት እንደሚገባ ያመላከቱት የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ ናቸው፡፡ የልዩነት ጥያቄዎችን በሰለጠነ መልኩ በማንሳት የህዝብን ሰላም መጠበቅ ላይ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አክለው፣ በግጭቶች ምንም አይነት መፍትሔ ማምጣት ስለማይቻል ለሰላም ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ላለፉት 50 አመታት ባልተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንድታልፍና በአንዳንድ አካባቢዎች አለመረጋጋቶች እንዲፈጠሩ ያደረገው፣ ሃገራዊ የሆኑ መግባባቶች ላይ ትኩረት ባለማድረጋችን መሆኑን ገልጸው፣ አሸናፊነት በሃይል ላይ የተመሰረተ ከሆነ ለውጥ ማምጣት ስለማይቻል ወጣቶች፣ የሲቪል ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በመንግስት በኩል ለሰላም ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ አስምረውበታል፡፡ ሠላም የሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነና ከጦርነት የምናተርፈው ነገር እንደሌለ የገለፁት ደግሞ ሌላኛው ‹የአዲስ ትውልድ ፓርቲ› ፕሬዝዳንትና የኦሮምያ የጋራ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ሰለሞን ታፈሰ፣ ጦርነት ንብረት ከማውደም፣ ህዝብን በስነ-ልቦናና በአካል ከመጉዳት ውጭ ትርፍ ስለሌለው እርቅን ማስቀደም ይገባል ብለዋል፡፡ በሃሳብ አለመግባባቶች ምክኒያት አዛውንቶች እንዲሰደዱ ህፃናት እንዳይማሩና ንብረት እንዲወድም ምክኒያት እንዳንሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ወጣቶችና የሃይማኖት አባቶች በሙሉ ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ከግጭት የምናተርፈው ነገር ስለሌለ በሃገር አቀፍ ደረጃ ሰላምን ለማስፈን ሁሉም አካል በያገባኛል ስሜት ሊሰራ እንደሚገባ ፓርቲዎቹ አመላክተዋል፡፡ ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በታክስ ስወራ፣ የተጨማሪ ታክስ አለመክፈል፣ በኮንቶሮባንድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተከሰሱ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በታክስ ስወራ፣ የተጨማሪ ታክስ አለመክፈል፣ በኮንቶሮባንድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል... read more
የሀሳብ እና የጤና ውህደት የሚፈጥሩት ሃይል….
https://youtu.be/OiX1D87jowU
read more
በትግራይ ክልል 1 ሚሊየን የሚገመቱ ተፈናቃዮች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ
ከዓመታት በፊት በነበረው የሰሜኑ ጦርነት ተፈናቅለው ወደ ቀድሞ ቀዬአቸው ያልተመለሱ ዜጎች ቁጥር በርካታ መሆኑን እና በዘላቂነት ማቋቋም እንዳልተቻለ ተገልጿል፡፡
ከፕሪቶሪያው የሰላም... read more
የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገለፀ
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጪው መስከረም 16 ቀን 2019 የሚከበረው የደመራ እንዲሁም የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ቢሮው... read more
በትግራይ ክልል በ1 ሺህ 800 ሄክታር መሬት ላይ የዛፍ አንበጣ መንጋ መከሰቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
በትግራይ ክልል አዲስ መጤ ‹የዛፍ አንበጣ› የተባለ ተምች መከሰቱን እና እስከአሁንም በ1 ሺህ 800 ሄክትር መሬት ላይ እንደተሰራጨ በግብርና ሚኒስቴር... read more
አፍሪካ ላይ የፍልሚያ ሻምፒዮና ይደረጋል
በርካታ የእግርኳስ ቤተሰቦች የአለማችን ትልቁ የሀገራት የውድድር መድረክ የሆነው የአለም ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአህጉራችን አፍሪካ ላይ እንዲከናወን ፊፋ እድሉን... read more
በበዓል ወቅት የሚያጋጥሙ ሃሰተኛ የብር ኖት ስርጭት እና ህገ ወጥ ግብይትን ለመቆጣጠር ዲጂታል የመገበያያ አማራጮችን መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ
ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) መጪውን የገና በዓል አስመልክቶ በሚደረገው ግብይት ህገ ወጥ የንግድ እና የማጭበርበር እንቅስቃሴ እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ማድረግ... read more
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አንድ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ
ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አንድ ሞቢል እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በእንጨትና... read more
ከአድዋ ድል ባሻገር….
https://youtu.be/gJFVVdYp7R4
read more
የህግ ታራሚ ወላጆች የቅርብ ቤተሰብ እያላቸው የቅጣት ማቅለያ ይደረግልናል በሚል በሃሰተኛ ምስክር ከልጆቻቸው ጋር ማረሚያ እንደሚገቡ ተገለፀ
ግንቦት 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በወላጆቻቸው ጥፋት ምክንያት አብረዋቸው ማረሚያ ለሚገቡት ህፃናት የሚደረገውን ድጋፍ ለማሻሻል እየተሰራ ነው... read more
ምላሽ ይስጡ