መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) «የምድር ጌጥ ኢትዮጵያ» በሚል ርዕስ ሲካሄድ የቆየው ታሪካዊና ባህላዊ አውደ ርዕይ የመጎበኛ ጊዜ፣ ከህዝብ የቀረበውን ከፍተኛ ፍላጎትና ጥያቄ መነሻ በማድረግ ለተጨማሪ ሶስት ሳምንታት መራዘሙ የዝግጅቱ አዘጋጅ «የሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት» አስታዉቋል፡፡ አውደ ርዕዩ ከዚህ ቀደም ከነሐሴ 28 እስከ መስከረም 10 ቀን ሲካሄድ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ የነበሩ የሃይማኖታዊና የባህላዊ በዓላት መደራረብ እንዲሁም ከቦታ ምቾት ጋር ተያይዘው የነበሩ ችግሮች የጎብኚዎችን ቁጥር እንደገደበዉ ድርጅቱ ገልጻል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ አውደ ርዕይ፤ ህፃናትና ቤተሰቦች የሀገራቸውን፣ የሃይማኖታቸውን፤ የቅዱሳት ቤተክርስቲያናትን ታሪክና ቅርሶች በቅርበት የሚያውቁበትን እድል የፈጠረ ነው ተብሏል። ዝግጅቱም በማየት፣ በመዳሰስ፣ በመስማት፣ በማሸተትና በመቅመስ አምስቱንም የስሜት ሕዋሳት በሚያሳትፍ ልዩ አቀራረብ የተዘጋጀ ሲሆን፤ የላሊበላ፣ የአክሱም፣ የደብረ ዳሞና የሌሎችም ታሪካዊ ቦታዎች ምስልና ቅርሶች ቀርበውበታል። በተጨማሪም በቦታው ላይ በርካታ ታሪካዊና ባህላዊ ይዘቶች በመኖራቸው፤ አውደ ርዕዩን ወደፊት «ቋሚ ሙዚየም» ለማድረግ የሚያስችል ሥራ በጥረት ላይ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። በዚሁ መሠረት አውደ ርዕዩ ከመስከረም 30 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር አጋማሽ ድረስ ባሉት ተከታታይ ሶስት ሳምንታት፤ በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል። አስተባባሪዎቹ አክለውም፤ እስካሁን አውደ ርዕዩን ያላዩ ህፃናትና ቤተሰቦች ከጦር ኃይሎች ወደ ቀራኒዮ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው «ሆላንድ ፓርክ» በመገኘት ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በመድኃኒት ፋብሪካ የደረሰ የኬሚካል ሬአክተር ፍንዳታ ቢያንስ 36 ሰዎችን ገደለ
ሰኔ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በህንድ ደቡባዊ ግዛት ቴልጋና በሚገኝ አንድ የመድኃኒት ፋብሪካ ውስጥ የኬሚካል ሬአክተር በመፈንዳቱ በተነሳ የእሳት አደጋ ቢያንስ... read more
የእርጅናን ፈተና በቴክኖሎጂ: ጃፓን ለሠራተኛ አረጋውያን የሮቦት ኃይል እየሰጠች ነው
መስከረም 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በዓለም ላይ ካሉ ከፍተኛ የእድሜ ባለፀጋዎች ብዛት አንዷ የሆነችው ጃፓን፣ አረጋውያን ሠራተኞቿን በሥራ ገበታቸው ላይ ረዘም... read more
መንግስት ጋብቻን የሚያበረታቱና ለቤተሰብ መጽናት አጋዥ የሚሆን ፖሊሲ ሊቀርጽ ይገባል ተባለ
ከጊዜ ወደ ጊዜ ከጋብቻዉ ቁጥር በዘለለ የሚሰማ የፍቺ ቁጥር እየተበራከተ በመምጣቱ መንግስት ለጋብቻ እና ቤተሰብ መጽናት የሚሆኑ ፓሊሲና የተለያዩ ህጎችን... read more
በመዲናዋ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጀምሮ የተላላፊ በሽታ ልየታ መጀመሩ ተገለፀ
ሕዳር 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በጂንካ ከተማ የተስተዋለውን የማርቨርግ ቫይረስን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ የቅድመ መከላከል ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ... read more
በኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን እንደመገበያያ መጠቀም የተከለከለ መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትላንትናው እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን እንደ መገበያያ... read more
የወረዳ እና የክፍለ ከተማ ቢሮዎች ወጥ በሆነ አሰራር እንዲሰሩ የሚያስገድድ ደረጃ መውጣቱ ተገለጸ
የወረዳ እና የክ/ከተማ ቢሮዎች ወጥ በሆነ አሰራር እንዲሰሩ የሚያስገድድ ስታንዳርድ ወይም ደረጃ መውጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት... read more
የአሜሪካው 82ኛው የአየር ወለድ ክፍለ ጦር ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመዝመት በተጠንቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ
መጋቢት 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታገን) በዓለም ላይ በፈጣን ደራሽነቱ የሚታወቀው 82ኛው የአየር ወለድ ክፍለ ጦር (82nd... read more
የሊቢያ ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በቱርክ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው አለፈ
ታህሳስ 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሊቢያ ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሌተናል ጄነራል መሀመድ አል-ሃዳድ በቱርክ በደረሰ አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው ማለፉ... read more
የ2017 ጳጉሜ ወር ቀናት ስያሜን መንግስት ይፋ አደረገ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለፉት 6 ዓመታት የጳጉሜ ወር ቀናት ስያሜ ተሰጥቶት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲከበር የቆየ ሲሆን፣ የ2017... read more
ኮሚሽኑ ሕፃናትን የሚመለከቱ አጀንዳዎችን በቀጥታ በስም ባይጠቅስም በአጀንዳዎቹ ውስጥ ማካተቱን ገልጿል
ሰኔ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ውይይትና ምክክር ሲያደርግባቸው ከቆየባቸው አጀንዳዎች መካከል የሕፃናት ጉዳይ እንደሚገኝበት ቀደም ሲል... read more
ምላሽ ይስጡ