መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) መስከረም 17 ቀን የሚከበረውን የመስቀል በዓል ለመታደም እና ሀገሪቷን ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶች በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማህበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል። የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ከሚከበሩ ታላላቅ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት አንዱ በመሆኑ፣ ለጎብኚዎች የበዓሉን ሥርዓቶች እንዲሁም የሀገሪቱን ባህል፣ ትውፊት እና እሴቶች በስፋት ለማስተዋወቅ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የማህበሩ ዋና ፀሐፊ አቶ ፋሲል አበበ ገልጸዋል ። በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ቱሪስቶች የመስቀል በዓልን ሃይማኖታዊ ሥርዓት በሚገባ እንዲረዱ እና የሀገሪቱን መልካም ገጽታ በሚያሳይ መልኩ ባለሙያዎቹ የማስጎብኘት አገልግሎት እንዲሰጡ ቅድመ ውይይት መደረጉንም አብራርተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ቱሪስቶች አዳዲስ መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ እና በአጠቃላይ በዓሉ ወደሚከበርባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚወስዷቸው ጠቅሰዋል። የቱሪስቶች ወደ ሀገር ውስጥ መምጣት ከኢኮኖሚ ፋይዳው ባለፈ ሀገሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የሚረዳ በመሆኑ፣ ባለሙያዎቹ ሙያውን በተከተለ መንገድ አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡ ማህበሩ ከቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የመስቀል በዓልን እንዲሁም አብሮ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀንን ለማክበር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
100 አዳዲስ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን አስገብተን አገልግሎት እየሰጡ ነው 👉ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ 100 አዳዲስ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን በማስገባት በቀን 1,408 (97.5%)... read more
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሰራሩን ሊያሻሽል እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አመላከተ
የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የብድር አሰጣጥና አመላለስ ላይ በቀረበው ኦዲት በተሰጡ ሃሳቦች ላይ የኢትዮጵያ ልማት... read more
ዛጎል የጉዞ መተግበሪያ በቱሪዝምና በዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ፣ የጉዞና የቱሪዝም እንቅስቃሴ ዘመናዊ የዲጂታል መፍትሔዎችን በማቅረብ የሚታወቀው ዛጎል ሴሊቲዮስ ትራቭል፣ በዛሬው ዕለት በሰጠው... read more
በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የምርጫ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ተገለጸ
ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቀጣይ አመት በሚካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በተወሰነ መልኩ የምርጫ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ... read more
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ358 ሰነዶችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ባካሄደው ምርመራ 73 በመቶ ሀሰተኛ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ አለ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከቀረቡለት 191 የወንጀል ጉዳዮች እና 167 ከፍታብሔር ጋር የተያያዙ የምርመራ ጥያቄዎችን ከፖሊስና... read more
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የወደሙ የትምህርት ተቋማትን ለመጠገን የሚያስፈልገዉን 3 ቢሊየን ብር የማሰባሰብ ስራ እንደተጀመረ ተገለጸ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት አራት ዓመታት በነበረው ግጭትና በተያያዥ ችግሮች የተነሳ ከ300 ሺሕ ተማሪዎች ውስጥ፣ ከ50 ሺሕ በላይ የሚሆኑት እስከ... read more
ለኤርሊንግ ሀላንድ በሲቲ የሚዪቆየውን ውል ለማደስ ተቃርቧል
ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይፋዊ ንግግሮችን በወኪሉ አማካኝነት ከክለቡ ጋር መጀመሩ ሲገለጽ መቆየቱ አይዘነጋም።
ጎል ማስቆጠርን እና የሚያገኛቸውም እድሎች በሚገባ... read more
ኤዱዋርዶ ሜንዲ ከብሄራዊ ቡድን ራሱን በማግለል ጓንት መስቀሉን ይፋ አድርጓል
መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ34 ዓመቱ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን እና የሳዑዲ ዓረቢያው አል-አህሊ ግብ ጠባቂ ኤድዋርድ ሜንዲ ከብሔራዊ ቡድን... read more
የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒት አቅርቦት ችግር መኖሩን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ
ኅዳር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጸረ-ተህዋሲያን መድሃኒት አቅርቦት ችግር መኖሩን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
ለጸረ-ተህዋሲያን የሚሆኑ መድሃኒቶች ከድህረ... read more
ቻይና ለባሕር ውስጥ ምርምርና ደኅንነት የሚሆን የሮቦት ዓሣ ይፋ አደረገች
መስከረም 06 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ) ቻይና በባሕር ውስጥ ምርምር እና የደኅንነት ቁጥጥር ዘርፍ አዲስ እምርታ ያሳየችበትንና የሰው ልጅ ቀጥተኛ እጅ... read more
ምላሽ ይስጡ