መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም. የሚከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሲንቢሩ ተናግረዋል። “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል፣ በተለይ ከሀገራዊ ምክክሩ ማግስት መከናወኑ የ2019 ዓ.ምን አከባበር ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። እንዲሁም የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቆ የመንግሥት ምሥረታ ዋዜማ ላይ መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገው ተጠቅሷል። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ለባህልና ለኪነ ጥበብ ሥራዎች እየሠራ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊዋ፣ በተለይ ኢሬቻን በማስተዋወቅ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንዲሆን እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። በተለይም ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ፣ ሚስ ኢሬቻ እና የኢሬቻ ኮንሰርት በዓሉን ለማስተዋወቅ ከተሠሩትና ከሚሠሩት ሥራዎች መካከል ማሳያዎች ናቸው ብለዋል። በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ የሚከበሩትን የኢሬቻ በዓላት ምክንያት በማድረግ፣ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት እና የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂደዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ጊዜዉ ያለፈበት መድሃኒት ቀላቅለዉ ሲሸጡ በተገኙ 105 የመድሃኒት መሸጪያ መደብሮች ላይ አስተዳደረዊ እርምጃ ተወሰደ
በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ መድኃኒት መደብሮች የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ቀላቅለው ይዘው የተገኙና አላግባብ ያስቀመጡ 105 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ... read more
የዉጭ ሃገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን የሚወስነዉ አዋጅ ህገ-መንግስታዊ ተቃርኖ የለበትም ተባለ
ሰኔ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለ ይዞታ የሚያደረጋቸው ረቂቅ አዋጅ ህገ መንግስታዊ መርሆችን ማዕከል... read more
ሳውዲ አረቢያ ከኑክሌር ሀያሏ ፓኪስታን ጋር ስምምነት ተፈራረመች፡ ለእስራኤል መልእክት መሆኑ ተጠቆመ
መስከረም 08 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሳውዲ አረቢያ መንግስት ከኑክሌር የታጠቀችው ፓኪስታን ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረሙ ተዘግቧል። ይህ ስምምነት በጂኦፖለቲካዊው መድረክ... read more
በትምህርት ቤቶች ለሚደረገው አማተር የኪነ ጥበብ ሰዎችን የማብቃት ስራ ውስጥ አካል ጉዳተኞች በተለያዩ ዘርፎች እንደሚሳተፉ ቢሮው አስታወቀ
የከተማ አስተዳደሩ የኪነ-ጥበብ ዘርፉን ለማሳደግ በሚደርገው አማተር የጥበብ ሰዎችን የማፍራት ስራ ውስጥ ከከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቤቶች ጋር በቅርበት እንደሚሰራ የአዲስ... read more
1ሺህ 500 የሚሆኑ እና ከአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ዜጎች ተሳታፊ የሚሆኑበት 3ኛው የስራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ሊካሄድ እንደሆነ ተገለጸ
ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ ካላት እምቅ የሰው ሀይል መካከል ወጣት ክፍሉ ይገኝበታል ያለው የኢፌድሪ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ነው።
የሚኒስቴር... read more
ምክር ቤቱ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የሦስት ዓመት የስራ አፈፃፀምን እያዳመጠ ይገኛል
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመት የስራ... read more
ልጆችን ከማንነት ቀውስ ለመጠበቅ ታሪክና ሃይማኖትን በቅጡ ማሳወቅ እንደሚገባ የሐመረ ብርሃን የብራና እና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት ገለጸ
ነሐሴ 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ድርጅቱ የልጆችን ማንነት አስጠብቆ ለመዝለቅ ከነሐሴ 28 እስከ መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም የሚቆይ የልጆችና... read more
ላሚን ያማል ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ መሆኑ ተረጋገጠ
ሕዳር 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስፔን ብሔራዊ ቡድን እና የባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ በላሚን ያማል ጉዳይ የገቡበት ውዝግብና አለመግባባት እንደቀጠለ... read more
የሩበን አሞሪም የመጀመሪያው ፈራሚ ዲዬጎ ሊዮን እንደሚሆን ይገመታል
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ17 አመቱ ፓራጓዊ ዲዬጎ ሊዮን ክለቡን በመልቀቅ ሴሮ ፖርቴኖን በመልቀቅ ፊርማውን ለማንቸስተር ዩናይትድ ለማስቀመጥ ወደ... read more
ምላሽ ይስጡ