መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም. የሚከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሲንቢሩ ተናግረዋል። “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል፣ በተለይ ከሀገራዊ ምክክሩ ማግስት መከናወኑ የ2019 ዓ.ምን አከባበር ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። እንዲሁም የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቆ የመንግሥት ምሥረታ ዋዜማ ላይ መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገው ተጠቅሷል። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ለባህልና ለኪነ ጥበብ ሥራዎች እየሠራ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊዋ፣ በተለይ ኢሬቻን በማስተዋወቅ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንዲሆን እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። በተለይም ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ፣ ሚስ ኢሬቻ እና የኢሬቻ ኮንሰርት በዓሉን ለማስተዋወቅ ከተሠሩትና ከሚሠሩት ሥራዎች መካከል ማሳያዎች ናቸው ብለዋል። በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ የሚከበሩትን የኢሬቻ በዓላት ምክንያት በማድረግ፣ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት እና የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂደዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ወሳኝ ኩነቶቻቸውን በመደበኛው የምዝገባ ስርዓት በማስመዝገብ ህጋዊ እውቅናና ጥበቃ እያገኙ ነው ተባለ
ነሐሴ 15 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና የሞት ወሳኝ ኩነቶቻቸውን በመደበኛው የምዝገባ ስርዓት በማስመዝገብ... read more
በኢትዮጵያ ቋሚ የህፃናት የኩላሊት ዲያሊሲስ ህክምና መስጫ ተቋም አለመኖሩ ተገለጸ
በሃገሪቱ በኩላሊት በሽታ የተጠቁ ህፃናት ዲያሊስስ የሚያደርጉበት የህክምና መስጫ ተቋም አለመኖሩን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ህክምና የኩላሊት ስፔሻሊስ ዶክተር... read more
በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞች ሙሉ ለሙሉ የስማርት ቆጣሪ ገጠማ መደረጉ ተገለጸ
የከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞች የቆጣሪ ቅያሪ ለማድረግ እቅድ ተይዞ ሲሰራ መቆየቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት በሀገሪቱ... read more
27ሺሕ 755 ያህል ከክልል መሸኛ ይዘው ለመጡ ተገልጋዮች አገልግሎት መስጠቱን ኤጅንሲው አስታውቋል
ሐምሌ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከአሁን ቀደም ለበርካታ ጊዜ መሸኛ ይዘው ለሚመጡም ተገልጋዮች አገልግሎቱ ቆሞ የነበረ ቢሆንም በዚህ አመት ከህዳር... read more
የአሜሪካው 82ኛው የአየር ወለድ ክፍለ ጦር ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመዝመት በተጠንቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ
መጋቢት 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታገን) በዓለም ላይ በፈጣን ደራሽነቱ የሚታወቀው 82ኛው የአየር ወለድ ክፍለ ጦር (82nd... read more
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በእጣ እና በጨረታ ለነዋሪዎች የተላለፉና ባለድለኞች እንዲገቡ ያልኩባቸዉን ሁሉንም የመኖሪያ ሳይቶች የመሰረተ ልማት አሟልቼ ጨርሻለሁ አለ
👉ቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸዉ ቅሬታ አቅራቢዎች በበኩላችዉ ግቡ ተብሎ ቀነ ገደብ ቢቀመጥም ምንም የተሟላ መሰረተ ልማት የለም ሲሉ... read more
በክልሉ በፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የተሃድሶ ኮሚሽን ስልጠና ዳግም መጀመሩ ተገለጸ
በትግራይ ክልል ከ75,000 በላይ የሚገመቱ የቀድሞ ታጋዮችን ትጥቅ የማስፈታትና በዘላቂነት ወደ መደበኛ ሕይወት ለማስገባት የታቀደው የተሃድሶ ሥልጠና በክልሉ በተፈጠረው የፖለቲካ... read more
አፍሪካ በሁሉም መስክ ከተረጂነት ወጥታ ራሷን ለመቻል ጥረት ማድረግ ይገባታል ተባለ
ጥር 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አሜሪካ ከአለም የጤና ድርጅት አባልነት እንደምትወጣ ማስታወቋን ተከትሎ ውሳኔዋ የአለምን ብሎም የአፍሪካን የጤና ችግር ሊጎዳው እንደሚችል... read more
ከተማ አስተዳደሩ ለ2018 በጀት ዓመት 14.5 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት መያዙን ተገለጸ
ነሐሴ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኑሮ መጋራት በሚል በተለያዩ ዘርፎች ላይ በቀጥታ 14.5 ቢሊዮን ብር ድጎማ መዘጋጀቱን የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ... read more
በዓመት ሁለት ጊዜ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት የቦክስ ውድድር ለማካሄድ መታቀዱ ተገለጸ
ነሐሴ 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የፕሮፌሽናል ቦክስ ስፖርትን ለማሳደግና በዘርፉ ያሉ ስፖርተኞችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት... read more
ምላሽ ይስጡ