መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት በአካባቢው አጥፊው የግሪሳ ወፍ መከሰቱን መግለጹ ይታወቃል። በጉዳዩ ላይ መናኸሪያ ሬዲዮ የክልሉን ግብርና ቢሮ አነጋግሯል። በአካባቢው የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ አደጋ እንዳያስከትል በአጭር ጊዜ መቆጣጠር መቻሉን የገለጹት በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ ናቸው፡፡ የግሪሳ ወፍ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት በመሆኑ ሸዋሮቢትን ጨምሮ በ5 ዞኖችና በ60 ቀበሌዎች ጭምር መታየቱን ተናግረዋል። ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት መደረጉን ገልጸው፤ አሁን ላይ ጉዳት በማያስከትልበት ደረጃ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል። የኤልኒኖ ሥጋት ባለበት በዚህ ወቅት ድርቅ፣ ያልተስተካከለ የዝናብ ስርጭትና የሰብል አጥፊ ተባዮች እንደሚከሰቱ የሚጠበቅ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የተለያዩ ወራሪ ተባዮችን ጨምሮ የግብርናውን ሥርዓት ከሚያዛቡ ነገሮች አስቀድሞ ለመከላከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ ያለው የሰብል ሁኔታ በግሪሳ ወፍ ለመበላት ያልደረሰ በመሆኑ የከፋ ጉዳት አለመድረሱን ተናግረው፤ እስካሁን የግብዓትና የኬሚካል እጥረት አለመኖሩን እንዲሁም የተጀመረው የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። መናኸሪያ ሬዲዮ በጉዳዩ ላይ የግብርና ሚኒስቴርን ቢጠይቅም በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥበት በመግለጽ ምላሽ ሰጥቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ከዉጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ዉስጥ በማምረትና ለገበያ በማቅረብ ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ ማዳን መቻሉ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በተያዘው በጀት ዓመት በ9 ወራት ውስጥ 1 ሺህ 451 አምራች ኢንተርፕራይዞች ትስስር በመፍጠር 2 ሺህ 231 አነስተኛና... read more
ሳውዲ አረቢያ ከኑክሌር ሀያሏ ፓኪስታን ጋር ስምምነት ተፈራረመች፡ ለእስራኤል መልእክት መሆኑ ተጠቆመ
መስከረም 08 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሳውዲ አረቢያ መንግስት ከኑክሌር የታጠቀችው ፓኪስታን ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረሙ ተዘግቧል። ይህ ስምምነት በጂኦፖለቲካዊው መድረክ... read more
የቱሪስት ፍሰቱን የሚቆጣጠር የመረጃ ቋት አለመኖር የጎብኚዎች ቁጥር በግምት እንዲሰላ አድርጎታል ተባለ
በተለያዩ ጊዜያት ሀገሪቷን ለመጎብኘት የሚመጡ የሀገር ውስጥ እንዲሁም የውጭ ጎብኚዎች እንዳሉ ቢታወቅም በአብዛኛው በሚባል ደረጃ የጎብኚዎች ቀጥር እየተቀመጠ ያለው በግምት... read more
Fact_checking_tools
አሳሳች ወይም እውነትነታቸው ያልተረጋገጡ ምስሎችን ወይም ቪድዮዎችን ለማጣራት የሚጠቅሙ መሳሪያዎች እና የማረጋገጫ መንገዶች
👉Google Reverse Image Search
ይህ የምረጃ ማጣሪያ በፎቶሾፕ ተመሳስለው... read more
የቻይናው Z-19 የጦር ሄሊኮፕተር በውጊያ ሜዳ የሰው አልባ ድሮኖች መቆጣጠሪያ ማዕከል ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ
ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የቻይና ህዝብ ነፃ አውጪ ጦር በዘመናዊ የጦር አቪዬሽን ስልቱ «Manned-Unmanned Teaming» (MUM-T) በመባል የሚታወቀውን... read more
ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋ ለቻይና ልትልክ ነው
ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋ ለቻይና ልትልክ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አስታወቀ።
የኢፌደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች... read more
የትምህርት ሚኒስትር የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ የሚመደብ ይሆናል ቢልም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በበጀት ጉዳይ እንደማይመለከተው እና ስምምነቱ ተግባራዊ ቢደረግ በትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚፈጥር ተገለጸ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ የሚመደብ ይሆናል... read more
ከ200 በላይ የሚሆኑ የቀንድ ከብት ነጋዴዎች ንግድ ፍቃድ መውሰዳቸው ተገለጸ
ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች በህገወጥ መንገድ የቀንድ ከብት ንግድ ሲያከናውኑ የነበሩ ከ200 በላይ ነጋዴዎች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ... read more
በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በተከሰተ ግጭት የኢራኗ ቀሸም ደሴት በነዳጅ ተበከለች
ነሐሴ 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በተካሄደ ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ የተመቱ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ባስከተሉት ተደጋጋሚ የነዳጅ መፍሰስ... read more
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ህልፈት የተሰማትን ሀዘን ገለፀች
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን እና በዚህም ቤተክርስቲያኗ የተሰማትን ሀዘን ገልጻለች።
ቤተክርስቲያኗ በማህበራዊ... read more
ምላሽ ይስጡ