መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት በአካባቢው አጥፊው የግሪሳ ወፍ መከሰቱን መግለጹ ይታወቃል። በጉዳዩ ላይ መናኸሪያ ሬዲዮ የክልሉን ግብርና ቢሮ አነጋግሯል። በአካባቢው የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ አደጋ እንዳያስከትል በአጭር ጊዜ መቆጣጠር መቻሉን የገለጹት በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ ናቸው፡፡ የግሪሳ ወፍ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት በመሆኑ ሸዋሮቢትን ጨምሮ በ5 ዞኖችና በ60 ቀበሌዎች ጭምር መታየቱን ተናግረዋል። ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት መደረጉን ገልጸው፤ አሁን ላይ ጉዳት በማያስከትልበት ደረጃ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል። የኤልኒኖ ሥጋት ባለበት በዚህ ወቅት ድርቅ፣ ያልተስተካከለ የዝናብ ስርጭትና የሰብል አጥፊ ተባዮች እንደሚከሰቱ የሚጠበቅ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የተለያዩ ወራሪ ተባዮችን ጨምሮ የግብርናውን ሥርዓት ከሚያዛቡ ነገሮች አስቀድሞ ለመከላከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ ያለው የሰብል ሁኔታ በግሪሳ ወፍ ለመበላት ያልደረሰ በመሆኑ የከፋ ጉዳት አለመድረሱን ተናግረው፤ እስካሁን የግብዓትና የኬሚካል እጥረት አለመኖሩን እንዲሁም የተጀመረው የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። መናኸሪያ ሬዲዮ በጉዳዩ ላይ የግብርና ሚኒስቴርን ቢጠይቅም በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥበት በመግለጽ ምላሽ ሰጥቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የኢትዮጵያ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት በሚቀጥሉት 4 ወራት እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ
በተያዘው አመት መስከረም ወር ላይ የተጀመረው የስነ-ህዝብና ጤና ቆጠራ ባለፉት 8 ወራት ውስጥ በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች በተሰራው ስራ ከግማሽ በላይ... read more
የንግድ ተቋማት ምዝገባ እስከ ቀጣይ ዓመት ሚያዝያ ወር ድረስ እንሚጠናቀቅ ተገለጸ
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በገጠር እና በከተማ የሚገኙ መደበኛም ሆነ ኢ-መደበኛ ነጋዴዎች ፣አምራቾች እና ኢንተርፕራይዞች ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ቆጠራ እንደሚደረግ... read more
በሰላም ሚኒስቴር የሰለጠኑት የሰላም ዘብ ወጣቶች መጨረሻቸው ምን ሆነ ?
👉
https://youtu.be/INyNu923kIo
read more
የአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ድንገተኛ ብልሽትን አስመልክቶ ከተቋሙ የተሰጠ መግለጫ
መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ ዌስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ (Addis West Substation) ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ የትራንስፎርመር ብልሽት... read more
የሕንድ አየር መንገድ ከደረሰበት አደጋ በኋላ ዓለም አቀፍ በረራዎቹን መቀነሱ ተገለጸ
ሰኔ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሕንድ ብሔራዊ አየር መንገድ የሆነው ኤር ኢንዲያ (Air India)፣ ባለፈው ሳምንት ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኑ ላይ... read more
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይኖሩ የነበሩ የህግ ታራሚዎች ገላን አካባቢ ወደ ተገነባው አዲስ ማረሚያ ቤት ሊዘዋወሩ መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ የህግ ታራሚዎች ቀደም ብለው ይኖሩበት ከነበረው አሮጌው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል አዲስ ወደተገነባው ገላን... read more
የመንገድ ደህንነት ጥራትን የሚያስገድድ አዲስ ዘመናዊ አሰራር ይፋ ተደረገ
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የመንገድ ላይ አደጋዎችን ለመቀነስ ወሳኝ እርምጃ ነው የተባለ ሲሆን፣ ጥራት እና ደረጃ የወጣላቸው የፍጥነት መቆጣጠሪያዎች፣ የደህንነት... read more
በሸዋሮቢት ከተማና አካባቢው አጥፊው የግሪሳ ወፍ በመከሰቱ ምክንያት አስቸኳይ የኬሚካል ርጭት ሊካሄድ ነው
መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም. (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ግብርና ፅህፈት ቤት በቀጠናው አጥፊው የግሪሳ ወፍ መከሰቱን አስታወቀ። ፅህፈት... read more
በቡርኪና ፋሶ የሀገር ፍቅር ስልጠና የጨረሱ 65 ሺህ ወጣቶች ተመረቁ፤ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ሀገራቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረቡ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ የሀገር ፍቅር ስልጠና የሰለጠኑ 65,000 ወጣቶች በምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት... read more
በኢራቅ የጠቅላይ ሚኒስትር አል-ሱዳኒ ጥምረት በፓርላማ ምርጫ አሸነፈ
ሕዳር 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ ሺዓ አል-ሱዳኒ ጥምር ፓርቲ በሀገሪቱ በተካሄደው የፓርላማ ምርጫ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ማሸነፉን... read more
ምላሽ ይስጡ