መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም. የሚከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሲንቢሩ ተናግረዋል። “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል፣ በተለይ ከሀገራዊ ምክክሩ ማግስት መከናወኑ የ2019 ዓ.ምን አከባበር ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። እንዲሁም የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቆ የመንግሥት ምሥረታ ዋዜማ ላይ መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገው ተጠቅሷል። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ለባህልና ለኪነ ጥበብ ሥራዎች እየሠራ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊዋ፣ በተለይ ኢሬቻን በማስተዋወቅ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንዲሆን እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። በተለይም ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ፣ ሚስ ኢሬቻ እና የኢሬቻ ኮንሰርት በዓሉን ለማስተዋወቅ ከተሠሩትና ከሚሠሩት ሥራዎች መካከል ማሳያዎች ናቸው ብለዋል። በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ የሚከበሩትን የኢሬቻ በዓላት ምክንያት በማድረግ፣ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት እና የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂደዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በምርጫ ህጉ የሚጠበቁ ማሻሻያዎች ምንድናቸው?
👉
https://youtu.be/NgfOdRJMnM0
read more
ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋ ለቻይና ልትልክ ነው
ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋ ለቻይና ልትልክ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አስታወቀ።
የኢፌደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች... read more
በጀርመን እስረኛ ከእስር ለማምለጥ ቢሞክር ወንጀል አይደለም ተባለ
👉ነጻነትን የማግኘት ሙከራ ሰብዓዊ መብት ነው ተብሏል
ሐምሌ 29 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የጀርመን የፍትህ ስርዓት በአንድ አስገራሚና ልዩ ህግ ይታወቃል የተባለ ሲሆን... read more
በአማራ እና ትግራይ ክልል ያሉ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ቀጣዩን የክረምት ወቅት ዝናብ እና ጎርፍ መቋቋም እንደማይችሉ ተገለጸ
በተለያዩ ጊዜያት በሀገሪቱ የተከሰቱትን ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተከትሎ በርካታ ዜጎች በመጠለያ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ቀጣዩን የክረምት ወቅት ተከትሎ... read more
ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶክተር) ለ129ኛው የዐድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
👉ሙሉ መልዕክታቸው እንደሚከተለው ቀርቧል
ለ29ኛው የዐድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።
ዐድዋ ለሰላም የተደረገ ዘመቻ ነው። ከዐድዋ ዘመቻ በፊት ኢትዮጵያውያን ለሰላም ያላቸውን... read more
በፍቅር መውደቅ እና የኮኬይን ሱስ ስሜት ተመሳሳይ ናቸው ተባለ
ነሐሴ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በፍቅር መውደቅ እና አደንዛዥ እጽ መጠቀም በአንጎል ውስጥ ተመሳሳይ ምላሽ እንደሚፈጥር የሳይንስ ጥናቶች ማረጋገጣቸው ተዘገበ።
በፍቅር ስሜት... read more
የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ማህበረሰቡ የሚቀላቀሉ ታጣቂዎች ቁጥር ቢጨምርም፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ እገታና ዘረፋዎች ስጋት መፍጠራቸው ተገለጸ
ሚያዚያ 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአማራ ክልል መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ መደበኛ ሕይወታቸው የሚመለሱ ታጣቂዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም፣ አሁንም... read more
የጎዶ ፕሮፐርቲስ ኤግዚቢሽን ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜ 3 ድረስ ለጎብኚዎች ክፍት መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ ሥር ከሚገኙ ድርጅቶች አንዱ የሆነው ጎዶ ሀውሲንግ ኤንድ ስማርት ሪልስቴት የሚያስገነባቸውን ቤቶች... read more
ቼልሲ ወሳኝ ክህሎት ያለውን ተጫዋች ለረጅም አመት አራዝመዋል
ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ጆሽ አቼምፖንግ በሪያል ማድሪድ እንዲሁም በሌሎች ሊጎች በጥብቅ ሲፈለግ የቆየ ተጫዋች እንደነበር አይዘነጋም። ይህ ተጫዋች ውሉ... read more
በወልዲያና አካባቢው የሃይል አቅርቦት ተቋረጠ
ከአላማጣ - ኮሞቦልቻ የተዘረጋ 230 ኪ.ቮ ከፍተኛ ሃይል አስተላለፊ መስመር ላይ ብልሽት ስላጋጠመ ከዶሮ ግብር ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሃይል ያገኙ... read more
ምላሽ ይስጡ