መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጪው መስከረም 16 ቀን 2019 የሚከበረው የደመራ እንዲሁም የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ቢሮው የሰላምና ፀጥታ ሥራውን እየሠራ እንደሚገኝ ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሥሐ ጥበቡ፤ በዩኔስኮ የተመዘገበው የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር የፀጥታ አካላት በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። አስቀድሞ ከማህበረሰቡ ጋር በቂ ውይይት መደረጉን የተናገሩት አቶ ፍሥሐ፤ የኢትዮጵያን ገጽታ ሊገነባ በሚችል ደረጃ በዓሉ እንዲከበር ከፀጥታ አኳያ ተገቢው ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል። ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም የሃይማኖት አባቶች በሚያስቀምጡት ሥርዓት መሠረት በዓሉ እንዲከበር ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ አሳስበዋል። ከፀጥታ ጎን ለጎን በየሰፈሩ በሚካሄደው የደመራ ማብራት ሥርዓት ላይ ምንም ዓይነት አደጋ እንዳይከሰት ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በዚህ በዓል ላይ በርካታ የሀገር ውስጥ እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ቱሪስቶች የሚገኙ በመሆኑ፣ የፀጥታ አካላት አስቀድመው ሕግና ሥርዓትን በጠበቀ መልኩ የፍተሻ እና የቅኝት ሥራዎችን እንደሚያደርጉ አመላክተዋል። መስቀል እንዲሁም በቀጣይ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለአማራ ክልል ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የምግብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ
ታኅሳስ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአማራ ክልል በተከሰተው ድርቅ የከፋ ችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች ከ5 ሚሊዮን ብር... read more
በግድቡ ግንባታ ወቅት የነበሩት ፈተናዎችን ለመቋቋም የታየውን ሀገራዊ አቋም በድህረ ምረቃውም ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ
ጥቅምት 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቅድመ ግንባታ እና በግንባታው ሒደት የነበሩ ፈተናዎች የተቀለበሱበት መንገድ፤ በድህረ ምረቃውም መቀጠል... read more
የዌይሞ አሽከርካሪ አልባ ታክሲዎች ከሰው አሽከርካሪዎች በ68% አነስተኛ አደጋ አጋጠማቸው!
ሐምሌ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢንሹራንስ ኢንስቲትዩት ለትራፊክ ደህንነት (IIHS) ይፋ የተደረገ አዲስ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ዌይሞ (Waymo) የተሰኙት አሽከርካሪ አልባ... read more
የውሾች አፍንጫ፡ ከቦምብ መለየት እስከ ካንሰር ምርመራ
መስከረም 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ውሾች ከሰው ልጅ እጅግ የላቀ የሆነ የማሽተት ችሎታ ያላቸው መሆናቸውን ሳይንሳዊ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በአፍንጫቸው ውስጥ እስከ... read more
የውጭ ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ መቀዛቀዝ በሴቶችና በእናቶች ላይ የሚሰሩ ስራዎቸን ፈትኗል ተባለ
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተያዘው በጀት አመት በአለም አቀፍ ደረጃ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ የተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ መቀዛቀዝ በሴቶችና... read more
አባት አርበኞች ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ
ትውልዱም የሀገርን ዳር ድንበር በውል ማወቅና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መከበር ውግንናውን ማሳየት እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡
አባት አርበኞች ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር አሁንም... read more
ባለፉት አራት ወራት ውስጥ 420 ሚሊየን ዶላር የውጪ ምንዛሬ ለባንኮች ተሽጧል ተባለ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ብሄራዊ ባንክ ከመጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀመሮ በየሁለት ሳምንት ሲያካሂደ የነበረው የውጪ ምንዛሬ ጨረታ... read more
“ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የዛሬዉን ትዉልድ ከታሪክ ተወቃሽነት ያዳነ የጋራ አሻራችን ነዉ”👉 ዶ/ር ሂሩት ካሳ
ታላቁ የኢትየጵያ ህዳሴ ግድብ የዛሬውን ትውልድ ከታሪክ ተወቃሽነት ያዳነ የጋራ አሻራችን ነው ሲሉ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም... read more
ኅዳር 21 በአክሱም ከተማ በድምቀት ለሚከበረው ኅዳር ጽዮን ክብረ በዓል የተለያየ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
ኅዳር 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዘንድሮውን ዓመት የኅዳር ጽዮን ክብረ በዓል በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ለማድረግ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን... read more
ስዊዘርላንድ ከአሜሪካ ጋር የገባችውን የፓትሪዮት ሚሳኤል ስምምነት ልታቋርጥ እንደምትችል አስጠነቀቀች
መጋቢት 24 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአውሮፓዊቷ ሀገር ስዊዘርላንድ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ግዢ ስምምነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ... read more
ምላሽ ይስጡ