መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ ከታክስ በፊት 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ሲያስመዘግብ፣ ጠቅላላ ሀብቱም 111.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል። ባንኩ ከዚህ በፊት ባካሄደው 33ኛ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማድረጉንና ጠቅላላ ገቢው የ21 በመቶ እድገት በማስመዝገብ 16.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጿል፡፡ እ.ኤ.አ. የ2025-26 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን፣ የባንኩ የሂሳብ ሚዛን እና የካፒታል አቅም እያደገ መምጣቱን እንዲሁም የባንኩን መደበኛ ስራዎች የሚያቀላጥፉ ቴክኖሎጂ መር ፕሮጀክቶች መተግበራቸውን ገልፀዋል:: የቦርድ ሰብሳቢው አክለውም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ያጋጠሙትን የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ እና ሀገራዊ ተግዳሮቶች በመቋቋም በፋይናንስና ፋይናንስ ነክ ባልሆኑ የአፈፃፀም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቅሰዋል። የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ሰኔ 30 ቀን 2026 ዓ.ም. 111.3 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 84.3 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ32 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑን አቶ አብዲሹ ገልፀዋል። በተመሳሳይም የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 81.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን ጠቅሰው፣ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት 66.2 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ23 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን በመጠቆም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ጠንካራ የሀብት ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ማድረጉን እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡ በተያያዘም ባንኩ በበጀት ዓመቱ 366 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ያገኘ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አብዲሹ፣ ይህ አፈፃፀም እ.ኤ.አ. ከ2024-25 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ34 በመቶ ዕድገት እንዳለው ገልፀዋል። ባንኩ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሰጠው ጠቅላላ ብድርም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የ26 በመቶ እድገት በማስመዝገብ 67.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን ጠቅሰዋል፡፡ ባንኩ የቀጣይ ዓመታት የአዲሱን የዳይሬክተሮች ቦርድ የሥራ ድርሻ ያስቀመጠ ሲሆን፣ የዲጂታል አሰራርን ማስፋፋት፣ የአሰራር መዋቅርን ማሳደግ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓትን መከተልና መተግበር ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ ተመላክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የ6ኛ ክፍል ከተማና ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ክልሎች ገለጹ
ሰኔ 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ከተማና ክልል አቀፍ ፈተናን በተመለከተ ጣቢያችን የክልል ትምህርት ቢሮዎችን... read more
በህንጻዎች ክብደት የተነሳ ኒው ዮርክ ከተማ እየሰጠመች ነው
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአሜሪካ የሚገኘው ታላቁ የኒው ዮርክ ከተማ በየዓመቱ ቀስ በቀስ እየሰጠመ መሆኑን የሚያሳይ አዲስ አስደንጋጭ ጥናት በቅርቡ... read more
በልምድ የሚሰሩ ዜጎችን የስራ ላይ ስልጠና በመስጠት ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ
በተለያዩ ተቋማት እንዲሁም በተለያየ መስክ ላይ የሚገኙና በልምድ የሚሰሩ ዜጎች ያላቸው ምርታማነት አንሳ በመሆኑ በተለያዩ ዘርፎች የሚፈለገውን ያህል ውጤት አለመገኘቱን... read more
የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል የሚሰጠውን የ3.3 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ለማገድ በቀረበው ታሪካዊ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ሊመክር ነው
ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል የሚሰጠውን የ3.3 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ሙሉ በሙሉ ለማገድ በቀረበው አዲስ... read more
በኢትዮጵያ የግብርና ምርት ብክነትና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተግዳሮቶች
ግብርና የበርካታ አገራትን ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴ ያሳደገ፣ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር በፍጥነት እንዲሸጋገሩ ያደረገ መሆኑ ይታወቃል። እንደ ቻይና፣ አሜሪካ... read more
sport
ቼልሲ የፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ መርሀ-ግብራቸው እንዲሸጋሸግ ለፕሪሚየር ሊጉ ያስገቡት ደብዳቤ ውድቅ ተደረገ
ሐምሌ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ... read more
ወረቀትን ከሣር ማምረት ተጀመረ
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ወረቀትን ለማምረት ዛፎችን መቁረጥን የሚተካ አዲስ የዘላቂነት ፈጠራ ይፋ ተደርጓል። ተመራማሪዎች ሣርን ዋና ጥሬ እቃ... read more
በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጥል በሽታ መድሃኒት እጥረት መኖሩ ተገለጸ
በኢትዮጵያ የሚጥል በሽታ መድሐኒት እጥረት መኖሩን ኬር ኢፕሊብሲ ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው ያስታወቀው፡፡
የበሽታው ታማሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ... read more
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚፈጠሩ ሃይቆች በ72 ማህበራት ተደራጅተው የአሳ ማስገር ስራ እንደሚሰሩ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አስታወቀ
ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫነት ባሻገር፤ ተጨማሪ ግድቦችንና ሐይቆችን በመፍጠር በዓሳ ሃብት ላይም... read more
እግሯን በእንቅስቃሴ ላይ ሳለች በተቀበረ ቦምብ ያጣችው ዝሆን ሰው ሠራሽ እግር ተገጠመላት
መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በታይላንድ የምትገኘው ሞሻ የተባለችው እስያዊት ዝሆን፣ ገና በህፃንነቷ እንቅስቃሴ ላይ በነበረችበት ጊዜ በተቀበረ ቦምብ... read more
ምላሽ ይስጡ