መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ ከታክስ በፊት 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ሲያስመዘግብ፣ ጠቅላላ ሀብቱም 111.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል። ባንኩ ከዚህ በፊት ባካሄደው 33ኛ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማድረጉንና ጠቅላላ ገቢው የ21 በመቶ እድገት በማስመዝገብ 16.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጿል፡፡ እ.ኤ.አ. የ2025-26 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን፣ የባንኩ የሂሳብ ሚዛን እና የካፒታል አቅም እያደገ መምጣቱን እንዲሁም የባንኩን መደበኛ ስራዎች የሚያቀላጥፉ ቴክኖሎጂ መር ፕሮጀክቶች መተግበራቸውን ገልፀዋል:: የቦርድ ሰብሳቢው አክለውም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ያጋጠሙትን የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ እና ሀገራዊ ተግዳሮቶች በመቋቋም በፋይናንስና ፋይናንስ ነክ ባልሆኑ የአፈፃፀም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቅሰዋል። የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ሰኔ 30 ቀን 2026 ዓ.ም. 111.3 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 84.3 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ32 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑን አቶ አብዲሹ ገልፀዋል። በተመሳሳይም የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 81.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን ጠቅሰው፣ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት 66.2 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር የ23 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን በመጠቆም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ጠንካራ የሀብት ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ማድረጉን እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡ በተያያዘም ባንኩ በበጀት ዓመቱ 366 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ያገኘ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አብዲሹ፣ ይህ አፈፃፀም እ.ኤ.አ. ከ2024-25 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ34 በመቶ ዕድገት እንዳለው ገልፀዋል። ባንኩ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሰጠው ጠቅላላ ብድርም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የ26 በመቶ እድገት በማስመዝገብ 67.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን ጠቅሰዋል፡፡ ባንኩ የቀጣይ ዓመታት የአዲሱን የዳይሬክተሮች ቦርድ የሥራ ድርሻ ያስቀመጠ ሲሆን፣ የዲጂታል አሰራርን ማስፋፋት፣ የአሰራር መዋቅርን ማሳደግ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓትን መከተልና መተግበር ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ ተመላክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
Beyond the Statistics: Why Road Safety in Ethiopia Needs Systemic Change, Not Just Blame
Every day on the radio and television, routine announcements deliver the same grim reality: "Another fatal traffic accident has claimed... read more
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን የደብል ዲግሪ (ሁለት ዲግሪ) ፕሮግራም እንደሚጀምር አስታወቀ
መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዩኒቨርሲቲው ቀደም ሲል በአንድ የሜጀር ዘርፍ ብቻ ሲሰጥ የነበረውን ሥልጠና በማሻሻል ተማሪዎች በሁለት ተያያዥ የትምህርት... read more
በጥርስ እና ጸጉር ንቅለ ተከላ ዙሪያ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ከልክ በላይ የተጋነኑ በመሆኑ ቁጥጥር እና እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው ተባለ
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የንግድ ውድድሩን ተከትሎ የጤና ተቋማት አማላይ ማስታወቂያዎችን በማስነገር ህብረተሰቡን ወደ ተሳሳተ እይታ እየመሩት ነው ያለው... read more
የተፈጥሮ ድንቅ ምህንድስና፦ 40 ሺህ ጡንቻዎች ያሉት ዝሆን እና አስገራሚው ቱምቢ!
ግንቦት 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዱር እንስሳት ዓለም ውስጥ እንደ ዝሆን ስንጥቅ (trunk) ወይም ቱምቢ በሚል የሚጠራው አስገራሚና ሁለገብ የአካል... read more
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠውን ጊዜ በአግባቡ አልተጠቀመም ሲሉ የምክር ቤት አባላት ገለፁ
በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ3 ዓመት የስራ... read more
ትንታኔቴል አቪቭ ጎራዴዋን ታነሳ ይሆን?
https://youtu.be/AZQD1yXaa5g
read more
ሬናቶ ቭይጋ ወደ ቪላሪያል በቋሚነት ማቅናቱ ተረጋግጧል
ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስፔኑ ተወካይ ቡድን የክለባቸው ሪከርድ በሆነ ዋጋ ወይም 29.5 ሚሊዮን ዩሮ ለቼልሲ ወጪ የሚያደርጉ ይሆናል።
ይህ... read more
በኢትዮጵያ በኩላሊት በሽታ ላይ በቂ ጥናት እየተደረገ እንደማይገኝ የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ተናገረ
ነሐሴ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) እንደ ሀገር በገዳይነቱ እየታወቀ የመጣው የኩላሊት በሽታ ትኩረት ተሰጥቶት በቂ ጥናት እየተደረገበት አለመሆኑን የኩላሊት... read more
ህፃን አግተው ገንዘብ የጠየቁ ግለሰቦች በጽኑ እስራት ተቀጡ
ግንቦት 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ6 ዓመት ህፃን በማገት እና ቤተሰቦቹን ለገንዘብ በመደራደር ወንጀል የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች በ12 እና በ9... read more
ምላሽ ይስጡ