መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 2.9 ሚሊየን ድጋፍ የሚሹ ተረጂዎች እንዳሉ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን መረጃ አመላክቷል። የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ በድንገተኛ አደጋዎች ጊዜ የውጭ እርዳታ ጥገኛ ከመሆን ይልቅ በሀገር ውስጥ አቅም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በአዋጅ የተቋቋመ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ሥርዓት መሆኑ ይታወቃል። ፈንዱ ከቴሌኮም እና ባንክ አገልግሎቶች ክፍያ፣ ከሎተሪ አገልግሎት፣ ከአክስዮን ክፍፍል፣ ከኬሚካል ሽያጭ፣ ከፓስፖርት፣ ቪዛ፣ ንግድ ፈቃድ አገልግሎቶች እና ከሌሎችም አማራጮች የሚሰበሰብ ነው። በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ስር በሚተዳደረው በዚህ “የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” በ6 ወር ውስጥ 15.5 ቢሊየን ብር እንደተሰበሰበ ኮምሽኑ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተገልጿል። ከተሰበሰበው የገንዘብ መጠን ውስጥ 4.9 ቢሊየን ብር ለአደጋ ጊዜ ምግብ ግዢ እንደዋለም ተገልጿል። በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ 2.9 ሚሊየን ድጋፍ የሚሹ ተረጂዎች ያሉ ሲሆን፣ በአደጋ ስጋት ምላሽ የሚሰበሰበው ፈንድ እነርሱን ለመደገፍ አገልግሎት ይውላል ተብሏል። ይሁን እንጂ አንዳንድ የአገር ውስጥ እና የውጭ ድርጅቶች የግል ጥቅማቸውን ማዕከል በማድረግ በኢትዮጵያ ያሉትን የተረጂዎች ቁጥር አጋነው እንደሚያቀርቡ ተመላክቷል። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠቃሚ ተብለው የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎች:- የእለት ደራሽ እርዳታ ፈላጊዎች፣ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች፣ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተፈናቀሉ፣ ጎዳና ተዳዳሪዎችና በየቦታው የሚኖሩ ዜጎች፣ የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች እንዲሁም የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው የስደት ተመላሾች መሆናቸው ተገልጿል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የቴክኒካል ጥገና ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ገለጸ
👉የፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከቻይና አጋር አካላት ጋር በጋራ በመሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የቴክኒካል ጥገና ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገለጸ
ነሐሴ... read more
ሰበር ዜና፡ ከሰሜን ኮሪያ የተተኮሰው ሚሳኤል የቀጣናውን ውጥረት እንደገና አናጋው!
ነሐሴ 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ሊያካሂዱት ካዘጋጁት ግዙፍ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ፣ ሰሜን... read more
ተቅማጥና ትውከት በሽታ
በጋምቤላ ክልል ኑዌር ብሔረሰብ ዞን አራት ወረዳዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ተከሰተ
🔰በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ የዘጠኝ ሰው ሕይወት ሲያልፍ 136... read more
የዘለንስኪ ልፋት ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የቸለሰው የትራምፕ ውሳኔ
https://youtu.be/NqY57YAokwU?si=GTy9_t5Oo1uH5v3q
read more
ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ ለአገር ውስጥ ጥቅል ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጠቃሚ እንደሚሆኑ ተጠቆመ
ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሥራ እንዲጀምሩ አዋጅ... read more
የደም ካንሰርን ለመግታት አለምአቀፍ አዲስ ሕክምና ይፋ ሆነ
ሰኔ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የ"ትሮጃን ፈረስ" ተብሎ የተሰየመው የደም ካንሰር ሕክምና በእንግሊዝ የጤና አገልግሎት (NHS) በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ መቅረብ ጀመረ።... read more
ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለትግራይ ልማት ማህበር የተሰጠ ማሳሰቢያ
ሙሉ መግለጫው ከታች ተያይዟል
ጉዳዩ፡ ማህበሩ በቅርቡ ያካሄደው ጉባኤን ይመለከታል
የትግራይ ልማት ማህበር (ትልማ) በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በመዝገብ... read more
የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት አዳራሽ የተቀሩ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑ ተገለጸ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኘው አዲሱ አዳራሽ ውስጥ የሚያስፍልጉ መገልገያ ግበቶችን የማሟላት ስራ እየተከናወነ... read more
የትራፊክ አደጋ አሁን ላይ በሽርፍራፊ ሰከንዶች ከ20 እስከ 60 ሰዎችን እየነጠቀን ነዉ ተባለ
የኮቪድ 19 ወረርሽ ዓለም ላይ በተከሰተበት ወቅት በሽታውን ለመግታት መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ በርካታ ያደረጉት ርብርብ ውጤት ማስመዝገቡን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡
የመንገድ ደህንነትና... read more
የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች ዓርበኞች ማህበር እየሰራ ባለው የታሪክ ማሰባሰብ ሂደት አንዳንድ ዓርበኞች የሚያውቁትን ታሪክ ለመናገር ፈቃደኛ አለመሆናች ችግር እንደፈጠረበት ተገለጸ
የካቲት ወር የድል በዓላት የሚበዙበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ኢትዮጲያዊያን ዓርበኞች የሚዘከሩበት እና ገድላቸው የሚነገርበት መሆኑ የሚታወቅ ነው ። ድል... read more
ምላሽ ይስጡ