መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 2.9 ሚሊየን ድጋፍ የሚሹ ተረጂዎች እንዳሉ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን መረጃ አመላክቷል። የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ በድንገተኛ አደጋዎች ጊዜ የውጭ እርዳታ ጥገኛ ከመሆን ይልቅ በሀገር ውስጥ አቅም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በአዋጅ የተቋቋመ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ሥርዓት መሆኑ ይታወቃል። ፈንዱ ከቴሌኮም እና ባንክ አገልግሎቶች ክፍያ፣ ከሎተሪ አገልግሎት፣ ከአክስዮን ክፍፍል፣ ከኬሚካል ሽያጭ፣ ከፓስፖርት፣ ቪዛ፣ ንግድ ፈቃድ አገልግሎቶች እና ከሌሎችም አማራጮች የሚሰበሰብ ነው። በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ስር በሚተዳደረው በዚህ “የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” በ6 ወር ውስጥ 15.5 ቢሊየን ብር እንደተሰበሰበ ኮምሽኑ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተገልጿል። ከተሰበሰበው የገንዘብ መጠን ውስጥ 4.9 ቢሊየን ብር ለአደጋ ጊዜ ምግብ ግዢ እንደዋለም ተገልጿል። በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ 2.9 ሚሊየን ድጋፍ የሚሹ ተረጂዎች ያሉ ሲሆን፣ በአደጋ ስጋት ምላሽ የሚሰበሰበው ፈንድ እነርሱን ለመደገፍ አገልግሎት ይውላል ተብሏል። ይሁን እንጂ አንዳንድ የአገር ውስጥ እና የውጭ ድርጅቶች የግል ጥቅማቸውን ማዕከል በማድረግ በኢትዮጵያ ያሉትን የተረጂዎች ቁጥር አጋነው እንደሚያቀርቡ ተመላክቷል። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠቃሚ ተብለው የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎች:- የእለት ደራሽ እርዳታ ፈላጊዎች፣ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች፣ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተፈናቀሉ፣ ጎዳና ተዳዳሪዎችና በየቦታው የሚኖሩ ዜጎች፣ የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች እንዲሁም የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው የስደት ተመላሾች መሆናቸው ተገልጿል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ትንታኔተመድ በሩዋንዳ ላይ ያወጣው አነጋጋሪ ዘገባትንታኔ
👉
https://youtu.be/F8xA6MAmRB0
read more
በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከ20 ሺሕ የሚበልጡ ሴቶች በወሲብ ንግድ መሰማራታቸው ተገለጸ
በአማራ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ20 ሺሕ የሚበልጡ ሴቶች ወደ ወሲብ ንግድ መግባታቸውን የክልሉ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ... read more
የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና መሰጠት ጀመረ
በዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ... read more
የታማ ጥብቅ ደን በዙሪያው ባሉ አራት ብሄረሰቦች መጠበቁ ከቱሪዝም ጠቀሜታ ባሻገር፣የማህበራዊ ቁርኝትን ይበልጥ ያጠናክራል ተባለ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች አዋሳኝ ያለው የታማ ማህበረሰብ ጠብቅ ደን፣ በዙሪያው ባሉ አራት ብሄረሰቦች እንዲጠበቅ፣ ከአንድ ወር... read more
አስገራሚ የኤክስሬይ ግኝት!
👉ከወትሮው በእጥፍ የሚበልጡ ጥርሶች ተገኙ
ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሳይንሳዊ ልብወለድ የሚመስል ነገር ግን እውነተኛ ክስተት በቅርቡ ይፋ ሆኗል። ይህ... read more
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ መፍትሄ ሊያመጣ ያልቻለው ፖለቲካውን የሚዘውሩት አካላት ከህዝባዊነት ይልቅ ድርጅታዊ አስተሳሰብ ላይ በመጠመዳቸው ነው ተባለ
በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተከናወነው የሰላም ስምምነት ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለው እሳቤ በተግባር የተረጋገጠበት መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡
በ38ኛዉ... read more
የመክፍል አቅም ለሌላቸው ዜጎች መንግስት ወጪያቸውን ሊሸፍንላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት አስታወቀ
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ሁነው የመክፍል አቅም ለሌላቸው ዜጎች መንግስት ሙሉ ወጪያቸውን መሸፈን የሚችልበት አሰራር መዘጋጀቱን... read more
ኢትዮጵያ በአፋጣኝ የራሰዋን የንግድ ሰርአት ፖሊሲ በማሻሻል አሜሪካ ካወጣችዉ አለም አቀፍ ፖሊሲ ጋር እንዲጣጣም ማድረግ እንደሚገባት ተጠቆመ
በቅርቡ አሜሪካ ባስተላለፈችው የታሪፍ ማሻሻያ መሰረት ኢትዮጵያ ምን አይነት ስራዎች ይጠበቁባታል የሚለዉን መናኸሪያ ሬዲዮ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችን አነጋግሯል፡፡
ኢትዮጵያ ላይ የንግድ... read more
በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚስተዋሉ ጥቃቶችን ለመከላከል ከህጉ ባለፈ ማህበረሰቡን የሚያነቃ ስራ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ
ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የነጭ ሪቫን (የጸረ-ጾታዊ ጥቃት) ቀን በሀገራችን ኢትዮጵያ ለ19ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ... read more
ምላሽ ይስጡ