መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኤሊኖን ለዘመናት በተለያየ ስያሜ እየተጠራ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያሳድር የቆየ አለም አቀፍ ክስተት እንደሆነ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የስትራቴጂክና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አይድሩስ ሀሰን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሜትሪዮሎጂ ኢንስቲትዮት በሰጠው የትንበያ መረጃ፣ በአገሪቱ በ8 ክልሎች፣ በ37 ዞኖች፣ በ178 ወረዳዎች የኤሊኖን ክስተት እንደሚያጋጥም መገለጹን አስታውሰዋል። ዘንድሮ በተከሰተው ኤሊኖን ሁለት ከፍተኛ ተጽዕኖዎች ማለትም ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ወይም ድርቅ እና የጎርፍ አደጋ እንደሚጠበቅ ምክትል ኮምሽነሩ አመላክተዋል። ኮምሽኑ ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር በመሆን ለክስተቱ ብቻ ሳይሆን ከኤሊኖን ባሻገር ምላሽ ለመስጠት በቂ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል። ክስተቱን ተከትሎ ለሚያጋጥም አደጋ ምላሽ ለመስጠት የሰብዓዊ እርዳታን በራስ አቅም ለመሸፈን ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት በተጀመረው “የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” ትልቅ አቅም መፍጠር እንደተቻለ አመላክተዋል። በዚህም መሰረት እንደ አገር ለኤሊኖን ብቻ ሳይሆን፣ ከኤሊኖን ባሻገር ለሚያጋጥም አደጋ ምላሽ ለመስጠት በቂ ዝግጅት እንደተደረገ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የስትራቴጂክና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አይድሩስ ሀሰን አስታውቀዋል። ኮምሽኑ ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ጋር በጋራ ባዘጋጀው መድረክ ለፌደራል እና የክልል የኮምዩኒኬሽን እና ሚዲያ አካላት በኤሊኖን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት እና በተቀናጀ የሚዲያ እና መረጃ ልውውጥ ዙሪያ ምክክር እያደረገ ነው። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ የተጣራባቸው አሥራ አንድ ተጠርጣሪዎች ክስ ተመስርቶባቸዋል – የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
ሕዳር 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ የተጣራባቸው አሥራ አንድ ተጠርጣሪዎች ክስ እንደተመሰረተባቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ክስ የተመሰረተባቸውም1ኛ ተከሳሽ... read more
ኢትዮቴሌኮም በ2018 በጀት ዓመት 235 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን አስታወቀ
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት አመት 162 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ማስታወቁ ይታወሳል።
በ2018 በጀት አመት በገጠርና... read more
በትምህርት ቤቶች ዙሪያ ተሽከርካሪን ደርቦ ማቆም 1 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ ተገለጸ
መስከረም 05 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ዙሪያ ማንኛውንም ተሽከርካሪ ደርቦ ማቆም በጥብቅ እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት... read more
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በበጀት አመቱ ወደ 50 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ዋጋ የሚያወጣ መድሃኒት ማስወገዱ ተገለጸ
ሰኔ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በባለስልጣኑ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ገልገሎ ኦልጂራ፤ እንደ አገር የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው እና... read more
ድሪቤ ወልተጂ የመጀመሪያው የግራንድ ስላም ክብርን ካሸነፉ አትሌቶች መካከል አንዷ መሆኗ ተረጋግጧል
በትራክ ውድድሮች ታሪክ ከፍተኛውን የገንዘብ ሽልማት የሚያስገኘው የግራንድ ስላም ውድድር በጃማይካዋ ኪንግስተን ከተማ እየተከናወነ ይገኛል።
በቅርብ አመታት በውድድር ቁጥር ማነስ ምክንያት... read more
አፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት የሚያስፈልገውን የገንዘብ ድጋፍ በአፍሪካ ልማት ባንክ በኩል ማሰባሰብ ጀመረች
ነሐሴ 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአፍሪካ ልማት ባንክ (AfDB) እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡድን በቢሾፍቱ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ ፋይናንስ ለማሰባሰብ የሚያስችል... read more
ኢትዮጵያ የተቀቀሉ የሥጋ ምርቶችን ወደ ቻይና መላክ ልትጀምር መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ የተቀቀሉ የሥጋ ምርቶች እና ተረፈ ምርቶችን ለቻይና ገበያ ልታቀርብ መሆኑን የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የእንስሳት... read more
የሽንት ቤት ወረቀት ለማግኘት ማስታወቂያ መመልከት ግዴታ ሆነ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቻይና አንዳንድ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች፣ የሽንት ቤት ወረቀትን ለመስጠት ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠ አዲስ ሥርዓት መዘርጋታቸው... read more
ፓሪስ ሴንት ጄርሜ ሞሀመድ ሳላህን ለማስፈረም ይፋዊ ንግግር መጀመሩን የፈረንሳዩ ጋዜጣ ሌኪፕ ዘግቧል
ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ32 አመቱ ግብፃዊው ኮከብ ሞሀመድ ሳላይ የፈረንሳዩን ሀያል ክለብ ለመቀላቀል ይፋዊ በሆነ መልኩ ንግግሮችን መጀመሩ... read more
በረቂቅ አዋጁ እጩዎች 3ሺሕ ፊርማ እንዲያቀርቡ የሚጠይቀው ድንጋጌ ተሻሽሎ አለመቅረቡ ቅሬታ አስነሳ
ሐምሌ 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ምርጫ ቦርድ በስራ ላይ የሚገኘው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ስነ ምግባር አዋጅ 1162/2011 ላይ ማሻሻያ በማድረግ ለውይይት... read more
ምላሽ ይስጡ