መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በትግራይ ቴሌቪዥን (Tigray TV) ላይ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ እገዳ መጣሉን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ። ባለሥልጣኑ በመግለጫው እንዳስታወሰው፣ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል በፕሬቶሪያ የተፈፀመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ባደረገው ውይይትና በተደረሰበት ስምምነት መሠረት ቀደም ሲል በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነስቶ ወደ ሥራ መመለሱ ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ለትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች የሰላም ግንባታና የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ሚዲያው ወደ ሕገ-መንግሥታዊና ሙያዊ መስመር እንዲመለስ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ቴሌቪዥን በተሰጠው ዕድል ተጠቅሞ እና የሙያ ሥነ-ምግባር አክብሮ አገልግሎት መስጠት ሲገባው፣ የሀገርንና የሕዝብን ደህንነት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉ እና ፅንፈኝነትን የሚያበረታቱ መልእክቶች በተከታታይ እየተላለፉበት እንደሚገኝ በተደረገው የሚዲያ ይዘት ክትትልና ግምገማ ማረጋገጡን ባለሥልጣኑ ገልጻል። በመሆኑም በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት መሠረት በማድረግ ጣቢያው ላይ ይህንን እገዳ ለመጣል መወሰኑን አስታውቋል። በመጨረሻም ማንኛውም ዲጂታል፣ ብሮድካስትም ሆነ የሕትመት ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም የቴሌቪዥን ጣቢያው በሕገ-ወጥ መንገድ የሚያሰራጫቸውን ይዘቶች አሰራጭቶ ወይም አስተጋብቶ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ባለሥልጣኑ አሳስቧል። ይህንን መመሪያ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም ሚዲያ ላይ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎች የሚወስድ መሆኑን አጥብቆ አሳስቧል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በሰብዓዊ ደጋፍ እጥረት ምክንያት በደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች እየተሰደዱ ነዉ ተባለ
ታኅሳስ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በደብረ ብርሃን ቻይና መጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች በቂ የሆነ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፎች... read more
እንቅልፍ ማጣት ጤናማ የአእምሮ ክፍልን ሊያጠፋ እና እርጅናን ሊያፋጥን ይችላል ተባለ
መስከረም 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲስ የወጣ የምርምር ውጤት እንደሚያመለክተው በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ለአእምሮ ጤና እጅግ አሳሳቢ መዘዝ ያስከትላል። ጥናቱ... read more
በፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ1ሺህ 5መቶ በላይ የእግር መዞር እክል የገጠማቸዉ ህፃናት መገኘታቸው ተገለፀ
የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከዚህ ቀደም ባልተደረገባቸው 10 ክልሎች የተካሄደ ሲሆን ከተቀመጠው እቅድ በላይ ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት መከተባቸውን የኢትዮጵያ... read more
ሰበር ዜና | ሰሜን ኮሪያ ባህር ኃይሏን በኒውክሌር ታጥቃለች፤ ግዙፍ የጦር መርከቦችንም ትገነባለች ሲሉ ኪም ጆንግ ኡን አስታወቁ!
ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው የባህር ኃይል ክፍሏን በታክቲካል የኒውክሌር መሳሪዎች ለማስታጠቅ እና ይበልጥ... read more
በጀርመናዊ ወጣት የተደረገው “የቴስላ ጠለፋ” የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪውን አስደንግጧል
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ የ19 ዓመት ጀርመናዊ ወጣት የሆነው ዴቪድ ኮሎምቦ ከአገሩ ጀርመን ሆኖ ከ13 በሚበልጡ አገራት የሚገኙ... read more
“በፊት ፖሊስ እና ፖሊሲ ልዩነታቸውን ለይቸ አላውቅም ነበር” – የፊልም ፖሊሲ እንዲቀረጽ ያደረገው አርቲስት ደሳለኝ ሀይሉ👉
https://youtu.be/CBpXq4yIMMo
read more
“ምንም ስህተት አልሰራንም፣ ግን ተሸነፍን” 👉 የኖኪያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
ነሐሴ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በአንድ ወቅት የሞባይል ስልክ ኢንዱስትሪን በመምራት ይታወቅ የነበረው ኖኪያ፣ በቴክኖሎጂው ዓለም በፍጥነት መለዋወጥ ምክንያት... read more
ሳይንቲስቶች የዓለምን የቆሻሻ ችግር ለመፍታት “ሱፐር ዝንቦችን” በዘረመል እየቀየሩ ነው ተባለ
👉ዝንቦቹ የሰዎችን እዳሪ በመብላት ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሚሞቱ ናቸው ተብሏል።
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የዓለምን የቆሻሻ ችግር ለመፍታት ሳይንቲስቶች በዘረመል የተቀየሩ... read more
በኢትዮጵያ ባለፈው አመት ከ10ሺህ የሚበልጡ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ
ይህ የተገለጸው የህጻናትና እናቶች ሞትን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ በተደረገበት መድረክ ላይ ነው።
በአንድ ከተማ መስተዳደር እና በ5 ክልሎች ይተገበራል በተባለው... read more
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ55ኛ መደበኛ ስብሰባው በርካታ ረቂቅ አዋጆችን፣ ፖሊሲዎችንና ደንቦችን አጸደቀ
ግንቦት 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሚኒስትሮች ምክር ቤት ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 55ኛ መደበኛ ስብሰባው ሀገራዊ ኢኮኖሚን፣ ማኅበራዊ ልማትንና... read more
ምላሽ ይስጡ