መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ 5 ነባር ብሔረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ ቋንቋ የመጥፋት አደጋ ላይ በመሆኑ የመንግሥትን ትኩረት እንደሚሻ የአካባቢው ተወላጅና ፖለቲከኛው ዶ/ር መብራቱ አለሙ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። እያንዳንዱ አርሶ አደር ቢያንስ አንድ ዲግሪ ያለው ልጅ ያለው መሆኑ የቦሮ ሺናሻን ማኅበረሰብ ልዩ ያደርገዋል የሚሉት ዶክተር መብራቱ፣ የብሔረሰቡ ምሁራን ቋንቋውን ለማስቀጠል የማስተዋወቅና የምርምር ሥራ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። መንግሥት ለብሔር ብሔረሰቦች መብት፣ እኩልነትና ባህላቸውን ለማስተዋወቅ የሚያደርገው ድጋፍ አበረታች ቢሆንም፣ ባህል፣ ወግና ቋንቋቸው የመጥፋት አደጋ ለተጋረጠባቸው ብሔረሰቦች ልዩ ትኩረት በመስጠት ጥናት ማድረግ እንደሚገባው ፖለቲከኛው ገልጸዋል። በተለይ ከብሔረሰቡና ከክልሉ ውጪ ለሚኖሩ የብሔረሰቡ ተወላጆች ቋንቋውን በማስተላለፍና በማስቀጠል ረገድ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርን ትኩረት እንደሚሻ ዶክተር መብራቱ ተናግረዋል። እንደ ማኅበረሰብ አናሳ ከሚባሉት መካከል የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ ተጠቃሽ ቢሆንም አናሳነቱ በቁጥር እንጂ በባህል ሀብት አይደለም የሚሉት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የባህልና ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ኃላፊ አቶ በላይ አፋ ናቸው። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አሁን ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ የብሔረሰቡን ቋንቋ የመጠበቅና የማስተዋወቅ ሥራ ሊሠራ እንደሚገባው ገልጸዋል። ብሔር ብሔረሰቦች በመዲናዋ ባህላቸውንና የዘመን መለወጫ ሥርዓታቸውን እንዲያከብሩ ከመፍቀድና ከማገዝ በተጨማሪ ቋንቋና ባህላቸው የመጥፋት አደጋ ለተጋረጠባቸው በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ በመሥራት መጠበቅ እንደሚገባም ተመልክቷል። የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ከመስከረም 11 እስከ መስከረም 18 ባሉት ቀናት እየተከበረ ይውላል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የፍሳሽ አወጋገድን በተመለከተ የወጣው መመሪያ አቅመ ደካሞችን ያማከለ አይደለም ተባለ
👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በበኩሉ የዜጎችን ህገ-መንግስታዊ መብት ያስጠበቀ መመሪያ ነው ብሏል።
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)ቅሬታቸውን... read more
በማረሚያ ተቋማት የሚወለዱ ህጻናትን የሚመለከት የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው
ህዳር 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በማረሚያ ተቋማት እየተሰራ ያለው የእድሳት ስራ የሚበረታታ መሆኑን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ... read more
ለኤሊኖን ብቻ ሳይሆን ከኤሊኖን ባሻገር ምላሽ ለመስጠት ተዘጋጅተናል:- የፌደራል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን
መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኤሊኖን ለዘመናት በተለያየ ስያሜ እየተጠራ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያሳድር የቆየ አለም አቀፍ ክስተት እንደሆነ የኢትዮጵያ የአደጋ... read more
በአማራ ክልል በተያዘው መጋቢት ወር መጨረሻ የአጀንዳ ማሰባሰብ እንደሚጀመር ተገለጸ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመጋቢት ወር መጨረሻ ቀናት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
በመሆኑም የወረዳ... read more
“በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ ዲጂታል ማንነት ተስፋ ሰጪ ከሆነው ፈጠራ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሠረታዊ ምሦሶ ተሻሽሏል።
ከአሁን በኋላ አማራጭ ሳይሆን ሰዎችን ከአገልግሎቶች፣ ከማኅበረሰቦች፣ ከተቋማት እና ከመንግሥታት ጋር የሚያገናኝ አስፈላጊ መሠረተ ልማት ነው።ከአምስት ዓመት በፊት በዲጂታል ኢትዮጵያ... read more
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚፈጠሩ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመቆጣጠር የቅድመ መተንበያ መሳሪያዎችን ለማሟላት እየሰራሁ ነዉ አለ
መጋቢት 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚፈጠሩ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመቆጣጠር የቅድመ መተንበያ መሳሪያዎችን ከአጋር አካላትና... read more
ግማሽ ጭንቅላቷን ብታጣም ተስፋ አልቆረጠችም፦ የክሪስቲና ሳንታውስ አስገራሚ የሕይወት ታሪክ
መጋቢት 08 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በስምንት ዓመቷ ሕይወቷን አደጋ ላይ የሚጥልና በቀን እስከ 150 ጊዜ የሚደርስ የሚጥል በሽታ (seizure) ያጋጥማት... read more
ቻይና ሰው ሰራሽ የሰው ልጅ ጽንስን(ሽል) ወደ ጠፈር ጣቢያዋ በመላክ ታሪካዊ ሙከራ አደረገች
ግንቦት 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰውን ልጅ ወደ ማርስ እና ጨረቃ ለማጓጓዝ እንዲሁም በህዋ ላይ በቋሚነት ለማስፈር ለሚደረገው ጥረት ትልቅ... read more
ከአደጋ ቁጥሮች በስተጀርባ ያሉ ህይወቶች፡ በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ መዋቅራዊ ለውጥ ለምን ያስፈልጋል?
በየእለቱ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ዜናዎች ላይ “በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ” የሚሉ መርዶዎችን መስማት የተለመደ የዕለት ተዕለት ክስተት ሆኗል። ነገር... read more
ለወራት በአየር ላይ የሚቆዩት “የሰማይ ላይ ሳተላይቶች”፦ የHALE ድሮኖች አዲስ አስገራሚ ስኬት!
ሚያዚያ 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአውሮፕላን ምህንድስናው ዘርፍ ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆኑት High-altitude long-endurance (HALE) የተሰኙት ድሮኖች በከፍተኛ ከፍታ ላይ ለረጅም... read more
ምላሽ ይስጡ