ነሐሴ 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በተካሄደ ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ የተመቱ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ባስከተሉት ተደጋጋሚ የነዳጅ መፍሰስ ምክንያት፣ የኢራን የባህር ዳርቻዎች በተለይም በቀሽም (Qeshm) እና ላራክ (Larak) ደሴቶች አካባቢ በወፍራም የነዳጅ እና ታር (tar) ቆሻሻ መሸፈናቸው ተገለጸ።
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የባህር ዳርቻዎቹ ሙሉ በሙሉ ወደ ጥቁርነት መቀየራቸውንና የነዳጅ ቆሻሻው የባህር ውኃውን መሸፈኑን ያሳያሉ። ይህ የአካባቢ ጥበቃ ውድመት የጀመረው ከየካቲት 2026 ጀምሮ በቀጣናው በተቀሰቀሰው ግጭትና በንግድ መርከቦች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት እንደሆነ ተመልክቷል።
ይህ የነዳጅ ብክለት ጥበቃ የሚደረግለት የሀራ ማንግሩቭ (Hara mangrove) ደን የመጨረሻ ክፍሎች የደረሰ ሲሆን፣ የፋርስ ባሕረ ሰላጤ የውኃ ጥልቀት ማነስና አነስተኛ የውኃ እንቅስቃሴ አደጋውን አባብሶታል። ሁኔታው በኮራል ሪፎች፣ በባህር ህይወታውያን እና በአካባቢው አሳ አጥማጆች መኖሪያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
የኢራን አስቸኳይ ጊዜ ባለስልጣናት የብከላውን ስፋት አረጋግጠው የፅዳት ስራዎችን ያዘዙ ቢሆንም፣ አደጋው ከአንድ ነጠላ ክስተት ይልቅ ለወራት ከቀጠለው ወታደራዊ ግጭት የተከማቸ እንደሆነ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ከኦማን ዳርቻ አቅራቢያ ከሩሲያ የነዳጅ ጫኝ መርከብ የወጣ ሌላ የነዳጅ ብክለት የተስተዋለ ሲሆን፣ ይህም ክስተት ግጭቱ ካበቃ በኋላም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የአካባቢ ውድመት እንደሚያስከትል ስጋት ፈጥሯል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ሕልሞቻችንን እንደ ፊልም መመልከት
👉አዲስ የሕልም መቅጃ ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ
ሰኔ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሳይንቲስቶች ሕልሞቻችንን መቅዳትና መልሶ ማጫወት የሚችል አብዮታዊ አዲስ ሄድሴት ይፋ አደረጉ።... read more
ጉግል ማጭበርበርያ ድረ-ገጾችን ለመለየት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መጠቀም ጀመረ
ጉግል በ Chrome ማሰሻው፣ በፍለጋ አገልግሎቱ እና በአንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ የማጭበርበር ተግባራትን ለመከላከል አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መጠቀም መጀመሩን አስታወቀ።
የኩባንያው... read more
🚀 የሰማይ የፍጥነት አውሬዎች፡ MiG-31፣ F-15EX እና Su-27 – ከፍተኛ ፍጥነታቸው ምን ያህል ነው?
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአለማችን ላይ ባሉ እጅግ ዘመናዊ እና ፈጣን የጦር አውሮፕላኖች የፍጥነት አቅም ላይ የሚያጠነጥን መረጃ ቀርቧል። እነዚህ... read more
ዲሚትሪ ፓዬት ከእግር ኳስ ሜዳ ተሰናበተ
መጋቢት 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ፈረንሳዊው የአማካይ መስመር ተጫዋች ዲሚትሪ ፓዬት ለ21 ዓመታት የዘለቀውን ስኬታማ የእግር ኳስ ዘመን በይፋ ማክተሙን አስታውቋል።... read more
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ አሽከርካሪዎች የሚያደርጉት የታሪፍ ማሻሻያ ሕገ-ወጥ መሆኑ ተገለፀ
ሚያዚያ 29 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሰሞኑ የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ፣ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ እስካሁን ምንም ዓይነት ውሳኔ... read more
በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል ተገቢውን የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ የሚያገኙት 2.8 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ተባለ
ሰኔ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በንፅህና መጠበቂያ እጥረት እና በግንዛቤ ክፍተት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የሚቀሩ ሴት ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።
ለወር... read more
ኢራን ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን አረጋገጠች
ሰኔ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢራን የፀጥታ ምክር ቤት ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን ማረጋገጡን የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።... read more
በአሳማ ስጋ መመገብ ምክንያት የተከሰተው ወረርሽኝ እስከ 40 ሺሕ ኢትዮጵያዊያንን ቀጥፎ አልፏል // የህዳር ሲታጠን ሚስጢር
https://youtu.be/X60MwJISe2k
read more
ከ1ሺሕ በላይ ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮች መጣራታቸው ተገለጸ
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) - በ2017 በጀት ዓመት ከ1ሺሕ በላይ ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮችን ማጣራቱን የህገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
የመሬት መንቀጥቀጥ እና የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ባለባቸው አካባቢዎች ለተለያየ ጉዳይ የሚያቀኑ ግለሰቦች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቆመ
ጥር 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) እሳተ ገሞራና የመሬት መንቀጥቀጥን የመሳሰሉ ድንገተኛ የተፈጥሮ አደጋዎችን ሁነት በምስል ለማስቀረት እና ለመመልከት ወደ ስፍራው... read more
ምላሽ ይስጡ