መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ)በበጋ ወራት ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸውን በሚያገኙ የደቡብ እና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች የሚያገኙትን ዝናብ በአግባቡ ሊጠቀሙ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሜቴኦሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ ትንበያ መሠረት በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች፣ ከፊል አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች መረጃው እንዲደርስ እየተደረገ መሆኑን የተቋሙ የግብርና ሜቴኦሮሎጂ ባለሙያ አቶ ይመር አሰፋ ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች በወቅቱ የመሬት ዝግጅት፣ የዘር ምርጫ እና የግብዓት አቅርቦት ሥራ ማከናወን እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡ የተለያየ የዝናብ መጠን እና ሥርጭት ሊያጋጥም ስለሚችል አርሶ አደሮች ከአካባቢያቸው የግብርና ባለሙያዎች ጋር በመመካከር ለዝናብ ሁኔታው ተስማሚ ጊዜ እና የዘር ዓይነት መምረጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በበጋው ወራት የኤልኒኖ ክስተት ለእነዚህ አካባቢዎች አዎንታዊ ሚና እንዳለው የተናገሩት ባለሙያው፤ በሰሜን አጋማሽ አካባቢዎች ደግሞ ሰብል የሚሰበሰብበት ወቅት እንደመሆኑ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የሚያስከትል በመሆኑ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በተለያዩ አማራጮች የበጋ የአየር ትንበያ መረጃ ተደራሽ እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አቶ ይመር ገልጸዋል፡፡ በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች የበልግ ዝናብን የሚጠብቁ አርሶ አደሮች፣ የሚገኘውን የዝናብ ዕድል ወደ ምርት ለመቀየር የዘር፣ የመሬት፣ የግብዓትና የውኃ ዝግጅታቸውን በወቅቱ ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ተመልክቷል፡፡ ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የውጭ ባንኮች በሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቅድ አዋጅ ጸደቀ
ታኅሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የውጭ ባንኮች በሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ... read more
ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተሰጠ መግለጫ!
መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ ኤምባሲ ዶሎ ዞንን በተመለከተ ያወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ በአካባቢው ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አያንጸባርቅም! የሶማሌ ክልል... read more
ትራምፕ በውጭ አገር በተሠሩ ፊልሞች ላይ የ100% ቀረጥ ሊጥሉ ነው
መስከረም 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ ውጪ በሚመረቱ ሁሉም ፊልሞች ላይ የ100 በመቶ ቀረጥ (ታሪፍ) ለመጣል... read more
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የወደሙ የትምህርት ተቋማትን ለመጠገን የሚያስፈልገዉን 3 ቢሊየን ብር የማሰባሰብ ስራ እንደተጀመረ ተገለጸ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት አራት ዓመታት በነበረው ግጭትና በተያያዥ ችግሮች የተነሳ ከ300 ሺሕ ተማሪዎች ውስጥ፣ ከ50 ሺሕ በላይ የሚሆኑት እስከ... read more
የኢትዮጵያና ኬንያ የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማት የሸኔ ታጣቂ ላይ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ማካሄድ መጀመራቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ
የኢትዮጵያና ኬንያ የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማት በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ በሚንቀሳቀሰው የሸኔ ታጣቂ ላይ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ማካሄድ መጀመራቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት... read more
ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ከሃገር እንዳይወጡ የሚጠብቁ አነፍናፊ ዉሾች ወደ ስራ ሊገቡ ነዉ ተባለ
👉አብዛኛው ቅርስ እየወጣ ያለው በኢትዮጵያ አየር መንገድ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት... read more
ጆዜ ሞሪንሆ የሪያል ማድሪድ ቀጣዩ አሰልጣኝ የመሆን እድላቸው እጅግ ሰፊ መሆኑን Sky Sport አረጋግጧል
ግንቦት 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ቡድናቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት ያጋጠመው የዋንጫ እጦት በክለቡ ያልተለመደ እና እንግዳ ነገር መሆኑን... read more
ማንቸስተር ዩናይትድ ለክሪስቲያን ሮሜሮ የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ታወቀ
ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ዩናይትድ የቶተንሃሙን አምበል ክሪስቲያን ሮሜሮን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ እያዘጋጀ መሆኑ ተዘግቧል። የ28 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ተከላካይ... read more
የእስራኤል እና የኢራንን ወቅታዊ የህዝብ ብዛትና የቆዳ ስፋት እንዲሁም #ወታደራዊ አቅም ሲዳሰስ
🔰የእስራኤል ዝርዝር መረጃ‼️
እስራኤል በ2025 የህዝብ ብዛቷ ወደ 9,517,181 የተጠጋ ሰዎች እንዳሏት መረጃዎች አመላክተዋል።
የቆዳ ስፋት ደግሞ 22,145 ካሬ ኪሎ ሜትር እንደሆነና... read more
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ አውቶብስ የታክሲ አገልግሎት ማስጀመሩን ገለጸ
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት መዲናዋ ላይ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ለመቀነስ በ10 የተመረጡ ቦታዎች ላይ የከተማ አውቶቡስ የታክሲ... read more
ምላሽ ይስጡ