መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ2019 ዓ.ም የአየር ሁኔታ ትንበያን ተከትሎ የኤልኒኖ ክስተት ሊያስከትላቸው ስለሚችላቸው የዝናብና የሙቀት ለውጦች የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይፋ አድርጓል። በተለይም በጎርፍ፣ በድርቅ፣ በግብርና ምርት እና በሕዝብ ጤና ላይ ሊከሰቱ ለሚችሉ ተፅዕኖዎች ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅትና የምላሽ ሥራዎች እንዲጠናከሩ በተቋሙ በኩል ባሉት 11 ቅርንጫፍ ማዕከላት በኩል መረጃ የመስጠት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ በክረምቱ ወራት የሰጠው የትንበያ መረጃ 79 በመቶ መከሰቱን ጠቅሰዋል። በዚህም በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮች የአየር ትንበያ መረጃን በመከታተል የዘር ምርጫ፣ የመዝራት ጊዜና የውኃ አጠቃቀም ውሳኔዎችን ከሚገኘው መረጃ ጋር ማስማማት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በሌላ በኩል ኤልኒኖ በክረምት ሲከሰት እና በበጋ ሲከሰት አሉታዊ እንዲሁም አዎንታዊ ተፅዕኖ ያለው መሆኑን በመጥቀስ፣ ችግሮችን ለመቀነስ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ በመሥራት ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል። የአየር ሁኔታ ትንበያን በወቅቱ መከታተል፣ የሥጋት አካባቢዎችን ቀድሞ መለየትና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማጠናከር በኤልኒኖ እና በሌሎችም የአየር ሁኔታ አደጋዎች የሚመጡ ተፅዕኖዎችን ለመቀነስ የሚወጡ መረጃዎችን መከታተል እንደሚገባ ተመላክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በዲጂታል ዘርፍ ወጣቶችን ለማብቃትና ለማሰልጠን ዓላማ ያደረገው “አዶናይ ቲክቶክ አካዳሚ” ሊከፈት ነው
ሰኔ 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ወጣቶች በፍጥነት እየተለወጠ ያለውን የዲጂታል ዓለም በተሳካ ሁኔታ እንዲቀላቀሉና እንዲያሸንፉ ለማስቻል “አዶናይ ቲክቶክ አካዳሚ” ሥራ... read more
በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን ማህበር አዘጋጅነት የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የታክስ አከፋፈል ስርዓት በስፋት የሚዳሰስበት 22ኛው አለም አቀፍ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
ሐምሌ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) 22ኛውን ዓለም አቀፍ ጉባዔ እየተከናወነ ያለውም ተጋባዥ የሆኑ እንግዶች በተገኙበት እና በፓናል ውይይቶች ነው። በመርሀ-ግብሩም... read more
ከ7 መቶ ሺህ በላይ ህፃናት የልጅነት ልምሻ /ፖሊዮ/ ክትባት መውሰዳቸው ተገለጸ
ታኅሳስ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጀመሪያ ዙር ከመስከረም 27 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ቁጥራቸው 691 ሺህ 307 የሚሆኑ... read more
የኃይል ሥርቆት በፈጸሙ 111 ደንበኞች ላይ ክስ ተመሠረተ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸገር ሪጅን በ8 ወራት ውስጥ አንድ መቶ አስራ አንድ ደንበኞች የኃይል ሥርቆት መፈጸማቸውን ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ እና... read more
በኢትዮጵያ ለ10ኛ ጊዜ የሚከበረው የዳውን ሲንድረም ቀን “የድጋፍ ስርዓቶቻችን ይሻሻሉ” በሚል መርህ እንደሚታሰብ ተገለጸ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ14ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ10ኛ ጊዜ የዳውን ሲንድረም ቀን መጋቢት 28/2017 ዓ.ም “የድጋፍ ስርዓቶቻችን ይሻሻሉ” በሚል መሪ... read more
በኢትዮጵያ የቡና ቱሪዝምን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
በቡና መገኛነቷ በአለም አቀፍ ደረጃ የምትታወቀው ኢትዮጵያ ምርቷን በአለም ገበያ በጥሬው በመላክ በገበያው ተወዳዳሪ መሆኗ ይታወቃል፡፡
ምርቱን እሴትን ጨምሮ ለውጭ ገበያ... read more
ማይናማር ታስረው የነበሩ 459 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ
በስራ ቅጥር ሽፋን በህገወጥ አለምአቀፍ የሰው አዘዋዋሪዎች ወደ ማይናማር ተወስደው ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ መንግስት እያደረጋቸው ያሉ ጥረቶች ቀጥለዋል።
ከሰሞኑ... read more
በ2017 በጀት ዓመት ከውጪ ንግድ ከተገኘው 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር፣ 6 ቢሊየን ዶላሩ ከቻይና ጋር በተደረገ የውጭ ንግድ የተገኘ ነው ተባለ
ጥቅምት 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ የተገለጸው በኢትዮጵያና በሻንሲ ግዛት የኢኮኖሚ እና ንግድ ልውውጥ ትብብር ኮንፈረንስ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ እና የቻይናን... read more
28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተጭበርበሩ
28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡
የባንኩ ሪፖርት... read more
ምላሽ ይስጡ