መስከረም 08 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ2019 ዓ.ም የአየር ሁኔታ ትንበያን ተከትሎ የኤልኒኖ ክስተት ሊያስከትላቸው ስለሚችላቸው የዝናብና የሙቀት ለውጦች የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይፋ አድርጓል። በተለይም በጎርፍ፣ በድርቅ፣ በግብርና ምርት እና በሕዝብ ጤና ላይ ሊከሰቱ ለሚችሉ ተፅዕኖዎች ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅትና የምላሽ ሥራዎች እንዲጠናከሩ በተቋሙ በኩል ባሉት 11 ቅርንጫፍ ማዕከላት በኩል መረጃ የመስጠት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ በክረምቱ ወራት የሰጠው የትንበያ መረጃ 79 በመቶ መከሰቱን ጠቅሰዋል። በዚህም በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮች የአየር ትንበያ መረጃን በመከታተል የዘር ምርጫ፣ የመዝራት ጊዜና የውኃ አጠቃቀም ውሳኔዎችን ከሚገኘው መረጃ ጋር ማስማማት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በሌላ በኩል ኤልኒኖ በክረምት ሲከሰት እና በበጋ ሲከሰት አሉታዊ እንዲሁም አዎንታዊ ተፅዕኖ ያለው መሆኑን በመጥቀስ፣ ችግሮችን ለመቀነስ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ በመሥራት ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል። የአየር ሁኔታ ትንበያን በወቅቱ መከታተል፣ የሥጋት አካባቢዎችን ቀድሞ መለየትና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማጠናከር በኤልኒኖ እና በሌሎችም የአየር ሁኔታ አደጋዎች የሚመጡ ተፅዕኖዎችን ለመቀነስ የሚወጡ መረጃዎችን መከታተል እንደሚገባ ተመላክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የኮርፖሬት ቦንድን ወደ ገበያ ለማስገባት እየተሰራ ነው ተባለ
ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ከመንግስት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ በተጨማሪ የኮርፖሬት ቦንድ ሽያጭ ገበያን ወደ... read more
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 41ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር ጋር ለኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የ53,300,000.00 ኤስ.ዲ.አር... read more
ኢትዮጵያ ከነበረችበት የእዳ ጥገኝነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ሉዋላዊነት መቀየር የቻለችበት ሁኔታ እንዳለ ተገለጸ
መስከረም 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በዛሬው ዕለት 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ... read more
ሶማሊያ በአዲሱ የአፍሪቃ ሕብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ተልእኮ ውስጥ ኢትዮጵያም እንድትካተት መፈለጓን ይፋ አደረገች
👉ኢትዮጵያ አምባሳደሯን ወደ መቃዲሹ እንደምትልክ የተገለጸ ሲሆን፤ ሶማሊያም እንዲሁ አዲስ አምባሳደር ወደ አዲስ አበባ ትልካለች ተብሏል።
ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሶማሊያ... read more
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ የሚጀመር ሲሆን ጉባኤው “የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ አፍሪካውያን“ በሚል መሪ ሀሳብ ላይ ትኩረቱን... read more
የቅርብ ጓደኛቸውን ገድለው መኪና የዘረፉ ግለሰቦች በፅኑ እስራት ተቀጡ
ሚያዚያ 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቅርብ ጓደኛቸውን ህይወት በማጥፋት ሲያሽከረክር የነበረውን መኪና ወስደው የተሰወሩ ሁለት ግለሰቦች ከ23 እስከ 25 ዓመት... read more
ባለፉት 4 ዓመታት አንድም ጊዜ የመረጣቸውን ህዝብ ሂደው ማወያየት እንዳልቻሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ
ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተመርጠው ምክር ቤት የገቡ አባላት ባለፉት 4 አመታት የመረጣቸውን ህዝብ ሂደው በአካል ማወያየት እንዳልቻሉ፤ ምክር ቤቱም መፍትሄ... read more
አፍሪካ ሆልዲንግ ቢዝነስ ግሩፕ ሞዴል ሀሴት ደረጀን የ“GODU Housing and smart real estate” ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ
መስከረም 21 ቀን 2019 (መናኸሪያ ሬዲዮ) — “የተትረፈረፈ ባለጸግነትን ለትውልድ እናወርሳለን” በሚል መሪ ቃል ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኘው አፍሪካ... read more
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚፈጠሩ ሃይቆች በ72 ማህበራት ተደራጅተው የአሳ ማስገር ስራ እንደሚሰሩ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አስታወቀ
ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫነት ባሻገር፤ ተጨማሪ ግድቦችንና ሐይቆችን በመፍጠር በዓሳ ሃብት ላይም... read more
የኢሬቻን ጨምሮ በዓላት ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ለቱሪዝም ፍሰት አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተገለጸ
መስከረም 14 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚከበሩ እንደ ኢሬቻ እና መስቀል ያሉ በዓላት ማህበራዊ ትስስርን ከማጠናከር ባሻገር የቱሪዝም ፍሰትን... read more
ምላሽ ይስጡ