መስከረም 3 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአውሮፓ ሀገራት ወታደሮቻቸውን ወደ ዩክሬን የሚልኩ ከሆነ ከሩሲያ ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ውስጥ እንደመግባት ይቆጠራል ሲሉ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጡ። ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በህንድ በተካሄደው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሲሆን፣ አውሮፓውያን ለዩክሬን ያቀረቡትን ወታደራዊ ድጋፍና የሰላም አስከባሪ ኃይል የመላክ እቅድ በጥብቅ እንደሚቃወሙት ገልጸዋል። አክለውም ሩሲያ ለአውሮፓ ሀገራት ምንም አይነት ስጋት ደቅና እንደማታውቅና ወደፊትም የመጋፋት ፍላጎት እንደሌላት አስታውቀዋል።
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ