ነሐሴ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ከቬኔዙዌላ ጋር በዓለም ታሪክ ትልቁ የሆነውን የነዳጅ ስምምነት መፈረሟን ይፋ አድርገዋል። በፕሬዝዳንቱ መመሪያ መሠረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ እና የጦር ጉዳዮች ሚኒስትሩ ፒት ሄግሴዝ ከቬኔዙዌላው ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ እንዲሁም ከግል ኩባንያ ጋር በመተባበር ባደረጉት ስምምነት አሜሪካ ከ65 ቢሊዮን ባሬል በላይ የሚሆነውን የቬኔዙዌላ የነዳጅ ተቀማጭ ሀብት በአብዛኛነት እንድትቆጣጠር አስችለዋል። ይህ ታሪካዊ ስምምነት ለአሜሪካ ግብር ከፋዮች ምንም አይነት ወጪ ሳያወጣ የአሜሪካን የነዳጅ ተቀማጭ ሀብት ከሁለት እጥፍ በላይ እንደሚያሳድገው ተገልጻል። በተጨማሪም የአሜሪካን የነዳጅ አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ በመጨመር ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ እንደሚያስገኝ ይጠበቃል። በሌላ በኩል ስምምነቱ ቬኔዙዌላን ወደ ታላቅ እድገት እና ብልጽግና በሚወስደው ጎዳና ላይ የሚያግዛት ከመሆኑም በላይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ፕሬዝዳንት ትራምፕ አስታውቀዋል። _ ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የአሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ጦር በጄጁ ደሴት አቅራቢያ ግዙፍ የጋራ የጦር ልምምድ ሊጀምሩ ነው
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን በደቡብ ኮሪያዋ የጄጁ ደሴት አቅራቢያ የሚካሄደውን "ፍሪደም ኤጅ" (Freedom Edge)... read more
ስልጣን ሊረከቡ የሳምንታት እድሜ የቀራቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ ስደተኞችን እንደሚያባርሩ ገለጹ
ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከአሜሪካው ”NBC” ቴሌቪዥን ጋር ታናንት ቃለ መጠይቅ የነበራቸው ተመራጩ ፕሬዝዳንት በምርጫ ቅስቀሳቸው ቃል በገቡት መሰረት... read more
በፈረንጆቹ 2024 ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ስፔን ለማቋረጥ ሲሞክሩ በባህር ላይ መሞታቸዉ ተገለጸ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዚህ ዓመት ወደ ስፔን ለመድረስ ሲሞክሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ሞተዋል ነዉ የተባለዉ ።
በ2024 ከ10... read more
አፍጋኒስታን በፈተናዎች ውስጥ ብትሆንም መጠነኛ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ነው ሲል የዓለም ባንክ ገለጸ
ኅዳር 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ በቅርቡ ባወጣው መረጃ፣ የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት የ2 ነጥብ 7 በመቶ ጥቅል አገራዊ እድገት አስመዝግበዋል... read more
በጋናው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተቃዋሚው ፓርቲ አሸንፏል
ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጋና ምክትል ፕሬዝዳንት ማሃሙዱ ባውሚያ ቅዳሜ በተካሄደው ምርጫ መሸነፋቸውን አምነው ተቀብለው፤ አሸናፊውን የቀድሞ ፕሬዝዳንት የነበሩትን... read more
የህንድ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞሃን ሲንግ በ92 አመታቸው ማረፋቸዉ ተሰማ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የደቡብ እስያ ሃገርን ለሁለት ጊዜ የመሩት እና ቀደም ሲል የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው የህንድን ኢኮኖሚዋን ነፃ... read more
የ6 ሰዓት አደገኛ ጉዞ በ30 ደቂቃ፦ በቻይና ለተማሪዎች የተገነባው አስደናቂው ኤሌቬተር
ነሐሴ 29 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቻይና ዩናን ግዛት በሚገኘው የኒዙ ወንዝ ታላቅ ገደል ውስጥ የተገነባውና ፉያዎ ላደር በመባል የሚታወቀው የ288... read more
በሞቃዲሾ የደህንነት ካሜራዎችን የሚገጥሙ የሱቅ ባለቤቶች እንደሚገደሉ የተሰጠው ሕገ-ወጥ ማስጠንቀቂያ ስጋት ሆኖብናል አሉ
ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ምስራቅ አፍሪካዊቷን ሀገር ሶማሊያን የሚያስተዳድረው መንግስት አሸባሪውን አልሸባብ ለመቆጣጠር ያስችለኛል ያለውን ሕግ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ... read more
አዘርባጃን ብሔራዊ ሐዘን አወጀች
ታኅሳስ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዘርባጃን በትናትናው ዕለት በካዛኪስታን በተፈጠረ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ብሔራዊ ሐዘን ማወጇን አስታወቀች፡፡
ትናንት የአዘርባጃን 62 መንገደኞችንና... read more
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ለስፔስ ኤክስ (SpaceX) መስራች ኢሎን መስክ ከፍተኛ የመንግሥት የክብር ሜዳሊያ አበረከቱ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ የስፔስ ኤክስ (SpaceX) ባለቤት ለሆኑት ኢሎን መስክ የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሜዳሊያ... read more
ምላሽ ይስጡ