ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. (መናኸሪያ ሬዲዮ) ለዓመታት የታጣፊ ስልኮችን (Foldable Smartphones) ገበያ በበላይነት ሲመራ የቆየው የደቡብ ኮሪያው የቴክኖሎጂ ግዙፍ ኩባንያ ሳምሰንግ፣ አፕል ወደዚህ ገበያ ለመግባት የሚያደርገውን ዝግጅት በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል። የዘርፉ ተነታኞች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፣ አፕል የመጀመሪያውን ታጣፊ አይፎን ለገበያ ለማቅረብ እየሰራ ይገኛል። ይህም እስካሁን በታጣፊ ስልኮች ዘርፍ ብቸኛ የበላይ ሆኖ የቆየውን የሳምሰንግ ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ ሊፈታተነው እንደሚችል ተገምቷል። ሳምሰንግ በበኩሉ አፕል ወደ ዘርፉ መቀላቀሉ የታጣፊ ስልኮችን የገበያ ድርሻ እና ተቀባይነት እንደሚያሳድገው በማመን ውድድሩን ለመጋፈጥ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እንጂ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እንደሚያስጠነቅቁት፣ አፕል የታወቀውን ጥራት እና የደንበኞች ታማኝነት ተጠቅሞ ወደ ገበያው ከገባ የሳምሰንግን የገበያ ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስበት ይችላል። በመጪዎቹ ዓመታት በሁለቱ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መካከል የሚደረገው የፈጠራ እና የገበያ የበላይነት ውድድር በሞባይል ስልክ ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል።
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ