ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የለንደኑ ክለብ ቼልሲ እና ኖቲንግሃም ፎረስት በ23 ዓመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ሊያም ዴላፕ ዝውውር ዙሪያ ሙሉ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበዋል።
ባለፈው ክረምት ከኢፕስዊች ታውን በ30 ሚሊዮን ፓውንድ ስታምፎርድ ብሪጅን የተቀላቀለው ዴላፕ፣ በቼልሲ ቤት ባሳለፈው የመጀመሪያ የውድድር ዘመን በጉዳት እና በአሰልጣኞች መቀያየር ምክንያት በቂ የመጫወት እድል ሳያገኝ ቀርቷል።
ቼልሲዎች መጀመሪያ ላይ ለተጫዋቹ እስከ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ዝውውሩን በ45 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ለማጠናቀቅ ፈቃደኛ ሆነዋል። ታይዎ አዎኒዪን በ9 ሚሊዮን ፓውንድ ለኮቨንትሪ ሲቲ የሸጡት ኖቲንግሃም ፎረስቶች፣ በኦሊቨር ግላስነር ስር የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ዴላፕን ዋነኛ ኢላማቸው አድርገውታል።
ኤቨርተኖችም በተጫዋቹ ላይ ፍላጎት ቢኖራቸውም፣ ዴላፕ በፕሪሚየር ሊጉ የመቆየት ፍላጎት ያለው በመሆኑ እና ፎረስትም ድርድሩን በመግፋቱ የሕክምና ምርመራውን አጠናቆ ይፋዊ ውል ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።
ጉዳት እንዲሁም የአሰልጣኞች መቀያየር ተጫዋቹ በብሪጅ የነበረውን ቆይታ ከባድ አድርገውታል። በቼልሲ ማልያ በፕሪሚየር ሊጉ 1 ጎል ብቻ ነው ማስቆጠር የቻለው። ባጠቃላይ በቼልሲ ቆይታው ባደረጋቸው 47 ጨዋታዎች 3 ጎሎችን ብቻ ነው ማስቆጠር የቻለው።
በ24 ዓመቱ ላይ የሚገኘው እንግሊዛዊው አጥቂ የኖቲንጋም ፎረስት የሪከርድ ግዢ ሆኖ ወደ ሲቲ ግራውንድ የሚያመራ ሲሆን፣ ወጥነት ባለው መንገድ ኳስ እና መረብን ለማገናኘት የሚችልበት ወሳኝ የዕድሜ ክልል ላይ ስለሚገኝ ዕድሉን በሚገባ በሲቲ ግራውንድ ይጠቀማል ተብሎ ይገመታል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
አውስትራሊያ የፍልስጤምን መንግስት እውቅና ለመስጠት ማቀዷን ጠቅላይ ሚኒስትር አልባኔዝ ተናገሩ
ነሐሴ 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ ሀገራቸው የፍልስጤምን መንግስት እውቅና እንደምትሰጥ አስታወቁ። ይህ ውሳኔ በመጪው መስከረም... read more
ለአይነ ስውራን ቤተሰቦቹ ሲል ብቻውን 4 ኪሎ ሜትር መንገድ የገነባው አባት
መስከረም 09 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በኔፓል ዳንግ ግዛት በሚገኝ ሳታሌ መንደር ውስጥ የሚኖሩት አቶ ቻንድራቢር ኦሊ፣ ለአይነ ስውር ባለቤታቸውና... read more
በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ዜጎች ከጸጥታ ችግር ባለፈ በህክምና ግብዓት አቅርቦት እጥረት ምክንያት የከፋ ቀውስ ውስጥ ናቸው ተባለ
ባለፉት 5 ዓመታት በአገራችን የተለያዩ አከባቢዎች በሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት የበርካቶች ህይወት ማለፉ፤ ንብረት መውደሙ እና የበዙትም ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን... read more
ወጋገን ባንክ 33ኛ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤን አካሄደ
መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ ከታክስ በፊት 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ሲያስመዘግብ፣ ጠቅላላ ሀብቱም 111.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል።... read more
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) በታሊባን መሪና ዋና ዳኛ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ
ሐምሌ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በአፍጋኒስታን በሚገኙ የሴቶችና ልጃገረዶች መብቶች ላይ ከፍተኛ ጥሰት ፈጽመዋል በሚል በታሊባን... read more
አፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት የሚያስፈልገውን የገንዘብ ድጋፍ በአፍሪካ ልማት ባንክ በኩል ማሰባሰብ ጀመረች
ነሐሴ 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአፍሪካ ልማት ባንክ (AfDB) እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡድን በቢሾፍቱ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ ፋይናንስ ለማሰባሰብ የሚያስችል... read more
ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ ስለመኖሩ በዝርዝር ገምግሞ በቀጣይ አቋሙን ይፋ እንደሚያደርግ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ገለጸ
ህዳር 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በግንቦት ወር ይካሔዳል በተባለው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ፤ ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ ስለመኖሩ በዝርዝር ገምግሞ አቋሙን... read more
ዲዲዬ ዴሾ የሪያል ማድሪድ ቀጣይ አሰልጣኝ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቆመ
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ዲዲየር ዴሻምፕ ከ2026 የዓለም ዋንጫ በኋላ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን እንደሚለቁ ማረጋገጣቸውን ተከትሎ፣ የሪያል ማድሪድ ቀጣይ አሰልጣኝ... read more
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ለመጀመሪያ ጊዜ 39.5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተቋሙ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 96.5 ቢሊዮን ብር ማትረፉን የሃይሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ... read more
ምላሽ ይስጡ