ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የለንደኑ ክለብ ቼልሲ እና ኖቲንግሃም ፎረስት በ23 ዓመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ሊያም ዴላፕ ዝውውር ዙሪያ ሙሉ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበዋል።
ባለፈው ክረምት ከኢፕስዊች ታውን በ30 ሚሊዮን ፓውንድ ስታምፎርድ ብሪጅን የተቀላቀለው ዴላፕ፣ በቼልሲ ቤት ባሳለፈው የመጀመሪያ የውድድር ዘመን በጉዳት እና በአሰልጣኞች መቀያየር ምክንያት በቂ የመጫወት እድል ሳያገኝ ቀርቷል።
ቼልሲዎች መጀመሪያ ላይ ለተጫዋቹ እስከ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ዝውውሩን በ45 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ለማጠናቀቅ ፈቃደኛ ሆነዋል። ታይዎ አዎኒዪን በ9 ሚሊዮን ፓውንድ ለኮቨንትሪ ሲቲ የሸጡት ኖቲንግሃም ፎረስቶች፣ በኦሊቨር ግላስነር ስር የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ዴላፕን ዋነኛ ኢላማቸው አድርገውታል።
ኤቨርተኖችም በተጫዋቹ ላይ ፍላጎት ቢኖራቸውም፣ ዴላፕ በፕሪሚየር ሊጉ የመቆየት ፍላጎት ያለው በመሆኑ እና ፎረስትም ድርድሩን በመግፋቱ የሕክምና ምርመራውን አጠናቆ ይፋዊ ውል ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።
ጉዳት እንዲሁም የአሰልጣኞች መቀያየር ተጫዋቹ በብሪጅ የነበረውን ቆይታ ከባድ አድርገውታል። በቼልሲ ማልያ በፕሪሚየር ሊጉ 1 ጎል ብቻ ነው ማስቆጠር የቻለው። ባጠቃላይ በቼልሲ ቆይታው ባደረጋቸው 47 ጨዋታዎች 3 ጎሎችን ብቻ ነው ማስቆጠር የቻለው።
በ24 ዓመቱ ላይ የሚገኘው እንግሊዛዊው አጥቂ የኖቲንጋም ፎረስት የሪከርድ ግዢ ሆኖ ወደ ሲቲ ግራውንድ የሚያመራ ሲሆን፣ ወጥነት ባለው መንገድ ኳስ እና መረብን ለማገናኘት የሚችልበት ወሳኝ የዕድሜ ክልል ላይ ስለሚገኝ ዕድሉን በሚገባ በሲቲ ግራውንድ ይጠቀማል ተብሎ ይገመታል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ጎዳና ላይ ያሉትን ጨምሮ ከ1መቶ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሴት ልጆች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከታህሳስ 21 እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2017... read more
የኢሬቻን ጨምሮ በዓላት ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ለቱሪዝም ፍሰት አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተገለጸ
መስከረም 14 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚከበሩ እንደ ኢሬቻ እና መስቀል ያሉ በዓላት ማህበራዊ ትስስርን ከማጠናከር ባሻገር የቱሪዝም ፍሰትን... read more
🚨 ሰበር ዜና፦ በሞስኮ ሰማይ ላይ የድሮን ውሽንፍር! ዩክሬን በሁለት ዓመት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ጥቃት ፈጸመች
ሰኔ 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዩክሬን ላለፉት ሁለት ዓመታት ካደረገቻቸው ጥቃቶች ሁሉ እጅግ ግዙፍ የሆነውን የድሮን ጥቃት በሩሲያ ዋና ከተማ... read more
ራስ ገዙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለምሁራን የሰጠሁት “በህግ የተቀመጠ መብት ስላለኝ ነው” ብሏል
👉ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ስለተሰጠዉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ መረጃ እንደሌለዉ ገልጿል፡፡
ታኅሳስ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ትምህርት ሚኒስቴር ከሰሞኑ የፕሮፌሰርነት ማእረግ መስጠት ጉዳይ... read more
የንግድ ባንክ አዲስ የዲጂታል መተግበሪያ፡ “ሲ.ቢ.ኢ በጄ” በይፋ ቀረበ
ሕዳር 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ "ሲ.ቢ.ኢ በጄ" (CBE ByG) የተሰኘ አዲስ የዲጂታል መተግበሪያ አማራጭ በይፋ አስተዋውቋል።
ባንኩ ይፋ ያደረገው... read more
በመጪው ሳምንት የደሴ ሙዚየም ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ
በደሴ ሙዜም የተዘረፉ ቅርፆችን ለማሰባሰብና ሙዚየሙ ዘመኑን በዋጀ መልኩ በኢዲስ መልክ ለማደስ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ከብሪትሽ ካውንስል ባገኘው 25... read more
ፈረንሳይ እጅግ ዘመናዊዋንና የኑክሌር ኃይል ታጣቂዋን ‘ደ ግራስ’ ሰርጓጅ መርከብ ተረከበች፤ በአውሮፓ የባህር ኃይል ላይ አዲስ የኃይል ሚዛን መፈጠሩ ተገለጸ
ሰኔ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር የሀገሪቱን የባህር ኃይል ይበልጥ ለማዘመንና ስልታዊ አቅሟን ለማሳደግ የያዘችው ታላቅ እቅድ አካል... read more
የክልሉ መንግስት ለ9 መቶ 90 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ9 መቶ 90 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መጪውን የትንሳኤ... read more
የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እና የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ
በመካከለኛው ምስራቅ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ከሰሞኑ የተፈጠረው ከፍተኛ ውጥረት የአለምን የድፍድፍ ነዳጅ ገበያ በእጅጉ አንቀጥቅጧል። እነዚህ ግጭቶች ወደ ሰፊ... read more
በውክልና በተሰጣቸው የተሽከርካሪ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ፈቃድ ላይ የጎላ ክፍተት በፈጸሙ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን በውክልና በተሰጣቸው የተሽከርካሪ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ፈቃድ ላይ የጎላ ክፍተት በፈጸሙ ተቋማት ላይ እርምጃ... read more
ምላሽ ይስጡ