ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የመኪና ባለቤቶች እና አሽከርካሪዎች ለተሽከርካሪዎቻቸው የሞተር ዘይት ሲገዙ ወይም ሲቀይሩ በዘይቱ መያዣ ላይ የተጻፉትን ቁጥሮች እና ፊደላት ትርጉም ማወቅ የሞተሩን እድሜ ለማራዘም ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ። እነዚህ ምልክቶች የዘይቱን ውፍረትና ቅጥነት (Viscosity)፣ የአየር ንብረት ተስማሚነት እና የአለም አቀፍ የጥራት ደረጃ የሚገልጹ መረጃዎች ናቸው።
ለአብነት ያህል SAE 5W-30 API SP የሚለውን የሞተር ዘይት ላይ ያለ ምልክት ብንመለከት ትርጉሙ እንደሚከተለው ይብራራል፦
የውፍረትና ቅጥነት መጠን (Viscosity Grade – SAE)
የመጀመሪያው 5W የሚያመለክተው ዘይቱ በብርድ ወይም በቅዝቃዜ ወቅት ያለውን የቅጥነት ደረጃ ነው። W የሚለው ፊደል Winter (ክረምት/ቅዝቃዜ) የሚለውን የሚያስረዳ ሲሆን ከ W በፊት ያለው ቁጥር አነስተኛ በሆነ መጠን ዘይቱ በቅዝቃዜ ወቅት በፍጥነት በመፍሰስ ሞተሩ ሲነሳ ወዲያውኑ የመጠበቅ አቅሙ ከፍተኛ ይሆናል።
ከዳሽ ( – ) በኋላ ያለው 30 ቁጥር ደግሞ ሞተሩ በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ በሚሰራበት ወቅት የሚኖረውን የዘይት ውፍረት ያሳያል። ይህ ቁጥር ከፍ ባለ ቁጥር ዘይቱ በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ውፍረቱን ሳይለቅ የመጠበቅ አቅሙ የጎላ ይሆናል።
በመቀጠል የሚገኘው API SP የሚለው ምልክት የሰሜን አሜሪካው የፔትሮሊየም ኢንስቲትዩት የጥራት ማረጋገጫ ነው። API ከሚለው ጽሁፍ ቀጥሎ የሚመጣው የመጀመሪያው ፊደል S ከሆነ ዘይቱ ለቤንዚን (Petrol) ሞተር የተሰራ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን C ከሆነ ደግሞ ለዲዘል (Diesel) ሞተር የሚያገለግል ነው።
ከ S ወይም C ቀጥሎ የሚመጣው ሁለተኛው ፊደል (ለምሳሌ SP) የቴክኖሎጂውን አዲስነትና የጥራት ደረጃ ያመለክታል። በፊደላት ቅደም ተከተል መሰረት ሁለተኛው ፊደል ወደ Z በጠጋ ቁጥር ዘይቱ ዘመናዊና ከፍተኛ የሞተር መከላከል አቅም ያለው መሆኑን ያረጋግጣል።
በተጨማሪም በዘይቱ መያዣ ላይ Full Synthetic የሚል ጽሁፍ ካለ ዘይቱ በላቦራቶሪ የተሰራና ረጅም ርቀት የሚያስኬድ ሲሆን፤ Semi-Synthetic ከሆነ ደግሞ ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ ዘይት ቅልቅል ነው። Mineral Oil የሚለው ደግሞ ከተፈጥሮ ድፍድፍ ነዳጅ የተጣራና በየአጭር ርቀቱ መለወጥ የሚኖርበት መሆኑን ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በመዲናዋ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጀምሮ የተላላፊ በሽታ ልየታ መጀመሩ ተገለፀ
ሕዳር 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በጂንካ ከተማ የተስተዋለውን የማርቨርግ ቫይረስን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ የቅድመ መከላከል ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ... read more
የመንገድ ደህንነት ጥራትን የሚያስገድድ አዲስ ዘመናዊ አሰራር ይፋ ተደረገ
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የመንገድ ላይ አደጋዎችን ለመቀነስ ወሳኝ እርምጃ ነው የተባለ ሲሆን፣ ጥራት እና ደረጃ የወጣላቸው የፍጥነት መቆጣጠሪያዎች፣ የደህንነት... read more
ከገቢ ግብር፣ ታክስና ቀረጥ ጋር ተያይዞ በ2016 በጀት አመት ወደ 309.8 ሚሊዮን ብር ሳይሰበሰብ መቅረቱ ተገለፀ
ሰኔ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2016 የበጀት ዓመት የፋይናንስ ህጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት በዛሬው እለት ለህዝብ... read more
ትራምፕ በካናዳ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ታክስ ምክንያት ከካናዳ ጋር የንግድ ንግግሮችን አቆሙ
ሰኔ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ካናዳ በአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ለመጣል ባቀደችው ታክስ ምክንያት ከካናዳ ጋር... read more
“ምንም ሳላጠፋ ነው የተቀጣሁት” ሲል አነጋጋሪው ተጫዋች ፕሬስቲያኒ በአዲስ ቃለ መጠይቅ ተናገረ
መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ጂያንሉካ ፕሬስቲያኒ በቪኒሲየስ ጁኒየር ላይ የዘረኝነት ስድብ ሰድቧል በሚል የቀረበበትን ክስ በአዲስ ቃለ መጠይቅ ያስተባበለ ሲሆን፤... read more
በትግራይ ከሚካሄደዉ የምክክር ሂደት በፊት ልዩ ዉይይት ከወጣቶች ጋር እንደሚኖር ተጠቆመ
ሰኔ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል የሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የምክክር ሂደት ከመጀመሩ አስቀድሞ ከክልሉ ወጣቶች ጋር ልዩ የውይይት... read more
በየሳምንቱ ከ200 በላይ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ እየተጠቁ መሆኑ ተገለፀ
ጥቅምት 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአማራ ክልል በየሳምንቱ ከ200 በላይ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ እየተጠቁ መሆኑን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት... read more
የአሜሪካው አፓቺ የውጊያ ሄሊኮፕተር በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ አቅራቢያ ተከሰከሰች
ሰኔ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ አቅራቢያ ከፍተኛ ወታደራዊ ስምሪት ላይ የነበረች የአሜሪካ ጦር ኃይል ኤኤች-64 አፓቺ (AH-64 Apache)... read more
ክሪፕቶ ከረንሲን በኢትዮጵያ መተግበር የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ተገለጸ
ታኅሳስ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከወረቀት እና የሳንቲም ገንዘብ በተጨማሪ የዲጂታል ገንዘቦች የክፍያና ኢንቨስትመንት አማራጭ እየሆኑ እንዳሉ ይገለፃል፡፡
ሀገራት ከእነዚህ መገበያያ... read more
🔰በቻይና ሰማይ ላይ የታየው 5 ጸሃዮች ምንድናቸው? እንዴት ተከሰቱ?
ሐምሌ 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቻይና ሰማይ ላይ እጅግ ያልተለመደ እና አስገራሚ የተፈጥሮ ክስተት ታይቷል። "ሰንዳግስ" (Sundogs) በመባል የሚታወቀው ይህ... read more
ምላሽ ይስጡ