👉በቀን 12 ሚሊዮን ኪሎዋት ሰዓት በማከማቸት ለ2 ሚሊዮን አባወራዎች የኤሌክትሪክ ብርሃን የሚሰጠው ሜጋ ፕሮጀክት!
ሐምሌ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የታዳሽ ኃይል ማመንጫዎችን ትልቁን የማከማቻ ፈተና የሚቀይር እጅግ ግዙፍ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በቻይና ተራራማ ቀጠና ውስጥ እየተገነባ ይገኛል። ይህ ተቋም ልክ እንደ አንድ ታላቅ ባትሪ የሚያገለግል ሲሆን፣ በተለያዩ የከፍታ ደረጃዎች ላይ የተሰሩ ሁለት የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎችን (Reservoirs) በመጠቀም ንጹሕ ኢነርጂን የማከማቸት እና መልሶ የመልቀቅ አስገራሚ የቴክኖሎጂ ስራ ያከናውናል።
የኤሌክትሪክ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ በሚጨምርበት ወቅት ውሃው በውስጣዊ መተላለፊያ ዋሻዎች ውስጥ ቁልቁል እንዲፈስ በማድረግ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ይመነጫል። በተቃራኒው የኃይል ፍላጎት በሚቀንስበት እና ትርፍ ኃይል በሚኖርበት ጊዜ ደግሞ፣ ውሃው በፓምፕ አማካኝነት በድጋሚ ወደ ላይኛው ማጠራቀሚያ ተለክቶ ለቀጣይ አገልግሎት ዝግጁ ሆኖ እንዲቀመጥ ይደረጋል።
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በቀን ከ12 ሚሊዮን ኪሎዋት ሰዓት (kWh) በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከማቸት የሚችል ሲሆን፣ ይህም በአማካኝ ለ2 ሚሊዮን ገደማ አባወራዎች አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማድረስ ሙሉ በሙሉ በቂ ነው።
ግንባታው በፈረንጆቹ 2024 መጀመሪያ ላይ የተጀመረው ይህ ታላቅ የምህንድስና ውጤት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ንጹሕ ኢነርጂን በሚያስፈልግበት ወቅት አከማችቶ ለመጠቀም ለሚደረገው ጥረት ታላቅ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የተፈጥሮ ጥርስን እንደገና ማብቀል የሚችል መድኃኒት በሰው ላይ መሞከር ተጀመረ
ጥቅምት 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጃፓን ሰው ሰራሽ ጥርሶችን (Dentures) እና የጥርስ ተከላዎችን (Implants) ወደ ታሪክ የሚሰድ አዲስ ዘመን ሊከፍት... read more
ከስደት ለተመለሱ ዜጎች የስነልቦና ድጋፍ ለመስጠት ስምምነት ተፈረመ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የተሻለ ኑሮና ገቢን ለማግኘት በማሰብ ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚያቀኑ የዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ... read more
ወተት ለምን ተወደደ?
👉
https://youtu.be/-Jy9xIQPybo
read more
ከትራፊክ አደጋ እስከ አሰቃቂ የህይወት ምዕራፍ …የህክምና እጦት
እናት ለቤቷ ምሶሶ እንደሆነች ይታወቃል ልጆችም ከሌላው ቤተሰብ በተሻለ መልኩ ከእናታቸው ጋር የቀረበ ግንኙነት እንደለቸው ነው የሚነገረው፤ በሃገራችን ኢትዮጵያ ብሎም... read more
የጃፓኑ ባል የ20 ዓመታት ዝምታ ፍጻሜ አገኘ
ጥቅምት 27 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ የጃፓን ባል ከባለቤቱ ጋር ከረጅም ጊዜ በፊት ከተፈጠረ አለመግባባት በኋላ ለሙሉ ሃያ ዓመታት ያህል መናገር... read more
በትግራይ ክልል የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ወደ ጦርነት እንዳይገቡ ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች በተለያዩ ምክንያቶች ተገፋፍተው ወደ ጦርነት እንዳይገቡ ቅስቀሳ እያደረገ መሆኑን ስምረት... read more
ሚኒ ፓኪው ወደ ቦክሱ አለም እንደሚመለስ አሳውቋል
በ2021 የቦክስ ጓንቱን የሰቀለው አንጋፋው ቡጢኛ ማኒ ፓኪው ከስፖርቱ ራሱን አግልሎ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተጠምዶ በሀገሩ ፊሊፒንስ ከ2016-22... read more
በምስራቅ ወለጋ ዞን በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሲቡ ሲሬ... read more
አውስትራሊያ ከእሙ አእዋፍ ጋር ያደረገችውና በሽንፈት የተጠናቀቀው አስገራሚው “የእሙ ጦርነት”
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በታሪክ ሰነዶች ውስጥ ሰፍረው ከሚገኙ እጅግ አጃኢብ የሚያስብሉ ክስተቶች መካከል አውስትራሊያ በ1932 እ.ኤ.አ ከሰራዊቷ በተጨማሪ... read more
ከፍቅር መልዕክት ጀርባ ያለው የዓለም አቀፍ የሳይበር ጥቃት! በ’አይ ላቭ ዩ’ ቫይረስ የተፈፀመው ታሪካዊ ውድመት
ሕዳር 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በግንቦት ወር 2000 ዓ.ም የ'አይ ላቭ ዩ' (ILOVEYOU) ቫይረስ በታሪክ እጅግ አውዳሚ ከሆኑ የሳይበር ጥቃቶች... read more
ምላሽ ይስጡ