ሰኔ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር የሀገሪቱን የባህር ኃይል ይበልጥ ለማዘመንና ስልታዊ አቅሟን ለማሳደግ የያዘችው ታላቅ እቅድ አካል የሆነችውንና በኑክሌር ኃይል የምትሰራውን ‘ደ ግራስ’ (De Grasse) የተሰኘች እጅግ ዘመናዊ የባህር ሰርጓጅ መርከብ በይፋ መረከቡ ታውቋል።
በቼርቦርግ የባህር ወደብ የተገነባችውና በውሃ ውስጥ እስከ 5 ሺህ 200 ቶን ክብደት የመሸከም አቅም ያላት ይህቺ ሰርጓጅ መርከብ፤ ፈረንሳይ እድሜጠገብ የሆኑትን የ‘ሩቢስ’ (Rubis) ዝርያ መርከቦቿን ለመተካት ከቀረጸችው የስድስት ሰርጓጅ መርከቦች ፕሮግራም መካከል የመጨረሻዋና እጅግ አስፈሪዋ መሆኗ ተነግሯል።
የባህር ላይ ጥቃቶችን፣ የረጅም ርቀት የስለላ ስራዎችንና ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን በልዩ ብቃት የመወጣት አቅም ያላት ይህቺ የ‘ባራኩዳ’ (Barracuda) ዝርያ መርከብ፤ ሙሉ በሙሉ በውሃ ውስጥ ተደብቃ ለ270 ቀናት ያህል ያለ ምንም መቆራረጥ ስራዋን ማከናወን የምትችል ሲሆን 65 የቡድን አባላትንም በውስጧ ትይዛለች። ይበልጥ አስፈሪ የሚያደርጋት ደግሞ በውስጧ የታጠቀቻቸው የባህር ላይ ክሩዝ ሚሳኤሎች፣ የ‘F21’ ከባድ ቶርፔዶዎች እና የ‘Exocet SM39’ የፀረ-መርከብ ሚሳኤሎች መሆናቸውን ወታደራዊ ተንታኞች ገልጸዋል።
የፈረንሳይ የመከላከያ ግዥ ኤጀንሲ (DGA) በበላይነት የመራው ይህ የባራኩዳ ፕሮጀክት፤ በድብቅ የመጓዝ (stealth) እና የረጅም ጊዜ ጽናትን ከኑክሌር አቅም ጋር በማጣመር በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ውስጥ ካሉ እጅግ የላቁና አስፈሪ የኑክሌር ጥቃት ሰርጓጅ መርከብ ንድፎች መካከል ቀዳሚው ተደርጎ ተወስዷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በበጀት አመቱ ወደ 50 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ዋጋ የሚያወጣ መድሃኒት ማስወገዱ ተገለጸ
ሰኔ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በባለስልጣኑ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ገልገሎ ኦልጂራ፤ እንደ አገር የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው እና... read more
በህገ ወጥ መልኩ ከሃገር የወጡ 220 ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ
ጂቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት(IOM) ጋር በመተባበር በህገ ወጥ መልኩ ከሃገር የወጡ 220 ፍልሰተኞችን በባቡር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጉን... read more
በህጻናት ፓርላማዎች የሚነሱ ጥያቄዎች ተፈጻሚ እየሆኑ አይደለም ተባለ
ኅዳር 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የህጻናት መብትን፤ ችግሮችን እና በህጻናት ልጆች ላይ ለሚከሰቱ ጥቃቶች እና መሰል በደሎችን ማስተጋባት እንዲችሉ በህጻናት... read more
ኢሰመኮ ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚቀርብላቸው ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን ቢገለጽም ቅሬታዎች አልደረሱኝም ሲል የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ
ኅዳር 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚቀርብላቸው ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠንም ሆነ... read more
ፍርድ ቤቱ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወሰነ
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞ የከተማዋ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አሳለፈ።
የከተማዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት... read more
በመቀሌ ከተማ ከ15ሺ ሊትር በላይ ነዳጅ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወረ መያዙ ተገለጸ
ባለፉት 15 ቀናት ምንም አይነት ነዳጅ ወደ ክልሉ አለመግባቱን ያስታወቀው የትግራይ ክልል የንግድና ሸማቾች ጥበቃ ቢሮ፣ በመቀሌ ከተማ በህገ... read more
የባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ባለንብረቶች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ መሆናቸውን ካላረጋገጡ መስራት እንደማይችሉ ተገለጸ
ኅዳር 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከዚህ ቀደም ባለንብረቶች ከተለያዩ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ቀድመው ይጠቀሙበት በነበረው የሰሌዳ ቁጥር ይሰሩ... read more
ቻይና የጠፈርተኞችን ምግብ ለማሻሻል የመጀመሪያውን ጭስ አልባ ምድጃ ወደ ጠፈር ጣቢያዋ ላከች
ጥቅምት 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቻይና ለጠፈር ምርምር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሌላ አስደናቂ እርምጃ ወስዳለች። የቻይና የጠፈር መርሃ ግብር (China's space... read more
አፍሪካ በ2030 አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስን በራሷ መልክ በሥነምግባር፣ በአካታችነት እና ዘላቂነት ቅርፅ ማስያዝ እንደሚኖርባት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) ገለጹ
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለአፍሪካ ትብብር እና ብልፅግና" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው ኤክስፖ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ... read more
የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገለፀ
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጪው መስከረም 16 ቀን 2019 የሚከበረው የደመራ እንዲሁም የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ቢሮው... read more
ምላሽ ይስጡ