ሰኔ 18 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) 42ኛው የሻምበል አበበ በቂላ ማራቶን የፊታችን እሁድ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና ሀዋሳ ከተማ በድምቀት እንደሚካሄድ ተጠቆመ። ከደቂቃዎች በፊት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት በውድድሩ ቅድመ ዝግጅት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጥቷል።
ይህ ታሪካዊ የሩጫ ውድድር በ12 ክለቦች እና በ4 የክልል ቡድኖች በድምሩ በ16 ክለቦች መካከል የሚከናወን ሲሆን፥ በሴት 74 እና በወንድ 249 በአጠቃላይ 323 አትሌቶች የሚሳተፉበት ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ለአንጋፋ አትሌቶች በተዘጋጀው ልዩ ምድብ ውስጥ እስከ 50 የሚጠጉ ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
ውድድሩን በበላይነት ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች የሜዳሊያ እና ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፥ በዚህም መሠረት አንደኛ ለሚወጡ 50 ሺህ፣ ሁለተኛ ለሚወጡ 25 ሺህ እንዲሁም ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ለሚያጠናቅቁ 20 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከት ታውቋል። ፌዴሬሽኑ ለአጠቃላይ የገንዘብ ሽልማት ብቻ ከ400 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የመደበ መሆኑም በመግለጫው ላይ ይፋ ሆኗል።
ይህ ውድድር በየዓመቱ የሚከናወን እና ለአገሪቱ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት ትልቅ የውድድር ምዕራፍ መሆኑን የፌዴሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐሪ ጠቁመዋል። በፌዴሬሽኑ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከሚዲያ አካላት ለተነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ከተሰጠበት በኋላ ፍጻሜውን አግኝቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭት ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ሊስፋፋ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 08 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭትን ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ለማስፋፋት ዝግጅት... read more
በሆቴልና መሰል ተቋማት የባለሙያዎችን አለባበስ በተመለከተ ከ50 ሺህ እስከ 1 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ደንብ ጸደቀ
ኅዳር 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በሆቴልና መሰል ተቋማት የባለሙያዎችን አለባበስ በተመለከተ ከ50 ሺሕ እስከ... read more
ቢሮው ለአስተያየት መቀበያነት ይጠቀምበት የነበረው 94 17 የጥቆማ መስጫ መስመር አገልግሎት መስጠት ያቆመው በልማት ምክንያት ገመዱ በመቆረጡ ነው ተባለ
ኅዳር 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች በትራንስፖርት ዘርፉ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር ሲያጋጥማቸው ወደ 94 17 በመደወል... read more
የትግራይ ክልል የኩላሊት ሕመምተኞች በገንዘብ እጥረት እና በአካባቢው ባለው ውጥረት ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ
ሕዳር 10 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በገንዘብ እጥረት እና በአካባቢው ባለው ውጥረት ምክንያት የትግራይ ክልል የኩላሊት ሕመምተኞች ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን... read more
በታይዋን ግድብ በመፍረሱ ምክንያት የ17 ሰዎች ሕይወት አለፈ
መስከረም 14 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በታይዋን ደሴት ላይ በሚገኝ አንድ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ግድብ በመፍረሱ ምክንያት በደረሰው አደጋ 17... read more
🔴ሰበር ወታደራዊ መረጃ፡ የሩሲያ የጦር ጄቶች ከአሜሪካውያን በሁለት እጥፍ የገዘፉበት ሚስጥር ይፋ ሆነ!
ግንቦት 27 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአየር ላይ የበላይነትን ለመጨበጥ የሚደረገው የልዕለ-ኃያላኑ ፍልሚያ ሌላ ምዕራፍ ይዟል። በወታደራዊ አቪዬሽን አለም ውስጥ ትልቅ... read more
የጤና አግልግሎት በመስጠት 25 ዓመታትን ያስቆጠረው አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ጥራትን በማስጠበቅ ረገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በ1992 ዓ.ም የተቋቋመው አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል የተለያዩ የጤና አገልግሎቶችን በመስጠት 25 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የህክምና አሰጣጥ ጥራቱን በማሻሻል አሁን... read more
የታላላቅ ኃያላን ፍልሚያ በቤጂንግ፦ ሺ ጂንፒንግ ዶናልድ ትራምፕን ካስተናገዱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ቭላድሚር ፑቲንን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተቀበሉ!
ግንቦት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም ፖለቲካ ትኩረት አሁንም በቻይና መናገሻ ከተማ ላይ ያረፈ ሲሆን የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የአሜሪካውን... read more
23 ሚሊዮን አሜሪካውያን የቸኮሌት ወተት የሚመጣው ከቡናማ ላሞች ነው ብለው ያምናሉ ተባለ
ሐምሌ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)23 ሚሊዮን አሜሪካውያን የቸኮሌት ወተት የሚመነጨው ከቡናማ ቀለም ካላቸው ላሞች ነው ብለው እንደሚያምኑ ተገለጸ። ይህ መረጃ... read more
ለንጹሕ ኢነርጂ እንደ ግዙፍ ባትሪ የሚያገለግል ታላቅ የውሃ ኃይል ማመንጫ ቻይና እየገነባች ነው
👉በቀን 12 ሚሊዮን ኪሎዋት ሰዓት በማከማቸት ለ2 ሚሊዮን አባወራዎች የኤሌክትሪክ ብርሃን የሚሰጠው ሜጋ ፕሮጀክት! ሐምሌ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የታዳሽ ኃይል... read more
ምላሽ ይስጡ