ሰኔ 18 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) 42ኛው የሻምበል አበበ በቂላ ማራቶን የፊታችን እሁድ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና ሀዋሳ ከተማ በድምቀት እንደሚካሄድ ተጠቆመ። ከደቂቃዎች በፊት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት በውድድሩ ቅድመ ዝግጅት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጥቷል።
ይህ ታሪካዊ የሩጫ ውድድር በ12 ክለቦች እና በ4 የክልል ቡድኖች በድምሩ በ16 ክለቦች መካከል የሚከናወን ሲሆን፥ በሴት 74 እና በወንድ 249 በአጠቃላይ 323 አትሌቶች የሚሳተፉበት ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ለአንጋፋ አትሌቶች በተዘጋጀው ልዩ ምድብ ውስጥ እስከ 50 የሚጠጉ ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
ውድድሩን በበላይነት ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች የሜዳሊያ እና ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፥ በዚህም መሠረት አንደኛ ለሚወጡ 50 ሺህ፣ ሁለተኛ ለሚወጡ 25 ሺህ እንዲሁም ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ለሚያጠናቅቁ 20 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከት ታውቋል። ፌዴሬሽኑ ለአጠቃላይ የገንዘብ ሽልማት ብቻ ከ400 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የመደበ መሆኑም በመግለጫው ላይ ይፋ ሆኗል።
ይህ ውድድር በየዓመቱ የሚከናወን እና ለአገሪቱ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት ትልቅ የውድድር ምዕራፍ መሆኑን የፌዴሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐሪ ጠቁመዋል። በፌዴሬሽኑ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከሚዲያ አካላት ለተነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ከተሰጠበት በኋላ ፍጻሜውን አግኝቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
አሜሪካ እና ዩክሬን በሩሲያ ጦርነት ዙሪያ ‘የተሻሻለ’ የሰላም እቅድ ላይ ተስማሙ
ሕዳር 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የዩናይትድ ስቴትስ እና የዩክሬን ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በዘላቂነት ለማቆም የሚያስችል... read more
የሊትዌኒያዊው አጭበርባሪ ከፌስቡክና ከጎግል 122 ሚሊዮን ዶላር ያለ ‘ሃኪንግ’ ሰረቀ
ሕዳር 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በ2013 እና 2015 ዓ.ም መካከል የተከሰተው ይህ የፋይናንስ ወንጀል በቴክኖሎጂ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስገራሚ ከሆኑት... read more
የታላላቅ ኃያላን ፍልሚያ በቤጂንግ፦ ሺ ጂንፒንግ ዶናልድ ትራምፕን ካስተናገዱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ቭላድሚር ፑቲንን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተቀበሉ!
ግንቦት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም ፖለቲካ ትኩረት አሁንም በቻይና መናገሻ ከተማ ላይ ያረፈ ሲሆን የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የአሜሪካውን... read more
ሊቨርፑል ፊቱን ወደ ጎንዛሎ ኢናሲዮ በማዞር ይህን ፖርቹጋላዊ የመሀል ተከላካይ ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመሩን የሚጠቁሙ መረጃዎች ወጡ
ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሊቨርፑል በዚህ ክረምት የተከላካይ መስመሩን ማጠናከር ዋነኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አድርጎ ወደ ዝውውር ገበያው ለመግባት... read more
የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭት ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ሊስፋፋ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 08 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ የዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ሕትመትና ሥርጭትን ወደ 60 አዳዲስ ወረዳዎች ለማስፋፋት ዝግጅት... read more
አፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት የሚያስፈልገውን የገንዘብ ድጋፍ በአፍሪካ ልማት ባንክ በኩል ማሰባሰብ ጀመረች
ነሐሴ 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአፍሪካ ልማት ባንክ (AfDB) እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡድን በቢሾፍቱ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ ፋይናንስ ለማሰባሰብ የሚያስችል... read more
የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እስክታገኝ ድረስ ጥረት ማድረጋችን እንቀጥላለን አሉ
በጉባኤው ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አፍሪካ በዚህ በ21ኛው ከፍለ ዘመን ያነሳችሁ ጥያቄ ተገቢና በቅርቡ... read more
ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካና ደቡብ ኮሪያን ወታደራዊ ልምምድ በመቃወም ለሁለተኛ ጊዜ የክሩዝ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች
መጋቢት 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ታዳጊ ልጃቸውን ኪም ጁ ኤን በማስከተል በሀገሪቱ ስልታዊ የክሩዝ... read more
አፍሪካ ቀስ በቀስ እየተሰነጠቀች አዲስ ውቅያኖስ የመፍጠር ሁኔታዋ እየሰፋ ነው ተባለ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለዓመታት የሳይንስ ሊቃውንትን ትኩረት ሲስብ የቆየው የአፍሪካ ቀጣናዊ ለውጥ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
አፍሪካ አህጉር ቀስ... read more
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አንድ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ
ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አንድ ሞቢል እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በእንጨትና... read more
ምላሽ ይስጡ