ሰኔ 18 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) 42ኛው የሻምበል አበበ በቂላ ማራቶን የፊታችን እሁድ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና ሀዋሳ ከተማ በድምቀት እንደሚካሄድ ተጠቆመ። ከደቂቃዎች በፊት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት በውድድሩ ቅድመ ዝግጅት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጥቷል።
ይህ ታሪካዊ የሩጫ ውድድር በ12 ክለቦች እና በ4 የክልል ቡድኖች በድምሩ በ16 ክለቦች መካከል የሚከናወን ሲሆን፥ በሴት 74 እና በወንድ 249 በአጠቃላይ 323 አትሌቶች የሚሳተፉበት ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ለአንጋፋ አትሌቶች በተዘጋጀው ልዩ ምድብ ውስጥ እስከ 50 የሚጠጉ ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
ውድድሩን በበላይነት ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች የሜዳሊያ እና ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፥ በዚህም መሠረት አንደኛ ለሚወጡ 50 ሺህ፣ ሁለተኛ ለሚወጡ 25 ሺህ እንዲሁም ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ለሚያጠናቅቁ 20 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከት ታውቋል። ፌዴሬሽኑ ለአጠቃላይ የገንዘብ ሽልማት ብቻ ከ400 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የመደበ መሆኑም በመግለጫው ላይ ይፋ ሆኗል።
ይህ ውድድር በየዓመቱ የሚከናወን እና ለአገሪቱ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት ትልቅ የውድድር ምዕራፍ መሆኑን የፌዴሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐሪ ጠቁመዋል። በፌዴሬሽኑ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከሚዲያ አካላት ለተነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ከተሰጠበት በኋላ ፍጻሜውን አግኝቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል የሚሰጠውን የ3.3 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ለማገድ በቀረበው ታሪካዊ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ሊመክር ነው
ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል የሚሰጠውን የ3.3 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ሙሉ በሙሉ ለማገድ በቀረበው አዲስ... read more
የትራፊክ አደጋ አሁን ላይ በሽርፍራፊ ሰከንዶች ከ20 እስከ 60 ሰዎችን እየነጠቀን ነዉ ተባለ
የኮቪድ 19 ወረርሽ ዓለም ላይ በተከሰተበት ወቅት በሽታውን ለመግታት መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ በርካታ ያደረጉት ርብርብ ውጤት ማስመዝገቡን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡
የመንገድ ደህንነትና... read more
የአድዋ ገድልን በዲፕሎማሲያዊው መስክ መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ያላት እውቅና የጨመረው እና የአውሮፓ ሀያላን ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር በእኩልነት መንፈስ መደራደራቸውን የቀጠሉት ከአድዋ ማግስት መሆኑ... read more
በመጪው ሳምንት የደሴ ሙዚየም ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ
በደሴ ሙዜም የተዘረፉ ቅርፆችን ለማሰባሰብና ሙዚየሙ ዘመኑን በዋጀ መልኩ በኢዲስ መልክ ለማደስ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ከብሪትሽ ካውንስል ባገኘው 25... read more
ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን በምክክሩ እየተሳተፉ መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዜጎችን ሰላም ለማስፈን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ምክክር አስፈላጊ መሆኑን በኦሮሚያ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ... read more
ለሀገራዊ ምክክሩ ጉባኤ አጀንዳዎች ተለይተው መቅረባቸው ለውይይቱ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ
ሰኔ 19 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን መሠረታዊ ችግሮች በምክክር ለመፍታት ስታደርገው የነበረው ጥረት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ይታወቃል።
ሀገራዊ የምክክር... read more
Fact_checking_tools
አሳሳች ወይም እውነትነታቸው ያልተረጋገጡ ምስሎችን ወይም ቪድዮዎችን ለማጣራት የሚጠቅሙ መሳሪያዎች እና የማረጋገጫ መንገዶች
👉Google Reverse Image Search
ይህ የምረጃ ማጣሪያ በፎቶሾፕ ተመሳስለው... read more
የዓለማችን ብቸኛዋ ሰው አልባ አህጉር አንታርክቲካ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአለማችን ላይ ብቸኛዋ ቋሚ ነዋሪ የሌላት አህጉር አንታርክቲካ መሆኗ ተገለጸ። ይህች በበረዶ የተሸፈነች አህጉር ምንም እንኳን... read more
38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን... read more
የውጭ አገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን በምን መልኩ?
👉
https://youtu.be/MiNUlahQOXk
read more
ምላሽ ይስጡ