ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ሀገራቸው የያዘችው የባሊስቲክ ሚሳኤል ፕሮግራም በፍፁም ለድርድር የማይቀርብ መሆኑን በፅኑ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ በፓኪስታን ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ተገን በማድረግ በሰጡት መግለጫ፣ ኢራን ራሷን ለመከላከል የገነባችው የሚሳኤል አቅም ባይኖር ኖሮ አሁን ላይ የሀገሪቱ እጣ ፈንታ እንደ ጋዛ ሊሆን እንደሚችል አስገንዝበዋል።
ማሱድ ፔዜሽኪያን አክለውም፣ “ለራሳችን መከላከያ የያዝናቸው ሚሳኤሎች ባይኖሩ ኖሮ፣ እስራኤል እና አሜሪካ ለሽማግሌም ሆነ ለህፃን ሳያዝኑ ኢራንን ልክ እንደ ጋዛ ያፈርሷት ነበር” ሲሉ የጦር መሣሪያዎቻቸው ለሀገሪቱ ህልውና ወሳኝ መሆናቸውን አስምረውበታል።
ኢራን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን፣ ከማንኛውም አካል ጋር በመከላከያ አቅሟ ዙሪያ በፍፁም ለድርድር እንደማትቀመጥ ፕሬዝዳንቱ በቁርጠኝነት ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ