ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ላለፉት አራት ዓመታት አጀንዳዎችን በማሰባሰብና በተለያዩ ምዕራፎች በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ መሸጋገሩን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚቀርቡ ዋና ዋና አጀንዳዎችን ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል።
የአጀንዳዎች ይፋ የማድረጉ መርሃ-ግብር በፒያሳ በሚገኘው ታሪካዊው የአድዋ መታሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፣ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ እንደሚተላለፍ ይጠበቃል።
ይህ አጀንዳዎችን ይፋ የማድረግ ሂደት፣ ሀገሪቱ ለዓመታት የዘለቁና መዋቅራዊ የሆኑ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት ለምታደርገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ ተነግሮለታል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ