ሰኔ 13 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቶዮታው ሊቀመንበር አኪዮ ቶዮዳ (Akio Toyoda) በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ውስጥ አነጋጋሪነታቸውን ቀጥለዋል። ሁሉም ሰው ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EVs) ብቻ ፊቱን እያዞረ መምጣቱ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረባቸው የገለጹት ሊቀመንበሩ፣ ባህላዊ የነዳጅ ሞተሮችን መደገፋቸውን በመቀጠላቸው “ብቸኝነት” እንደሚሰማቸው በግልጽ ተናግረዋል።
ከታዋቂው Carwow የመኪና መድረክ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ቶዮዳ ሲናገሩ፦ “ከሶስት ወይም ከአራት ዓመታት በፊት፣ ‘የሞተር ሽታ፣ ድምፅ እና ራሱ ሞተሩ ይማርከኛል’ ብዬ በግልጽ የተናገርኩት እኔ ብቻ ነበርኩ” ብለዋል።
በርካታ የመኪና አምራቾች ሙሉ በሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እያዞሩ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ቶዮታ ግን የተለየ መንገድ በመከተል ላይ ይገኛል። ኩባንያው እንደ ሌሎቹ ወደ አንድ አማራጭ ብቻ ከመሮጥ ይልቅ በሃይብሪድ፣ በሃይድሮጅን ቴክኖሎጂ፣ በባህላዊ የነዳጅ ሞተሮች (Combustion Engines) እንዲሁም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ በአንድነት ኢንቨስት እያደረገ ይገኛል።
ሊቀመንበሩ አክለውም፣ ባህላዊ ሞተሮች አሁንም በገበያው ውስጥ የራሳቸው ትልቅ ቦታ እንዳላቸውና በሞተር ልማትና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ የብዙ ሺህ ሰራተኞችን የስራ ዕድል እንደሚታደጉ አስገንዝበዋል።
ይህ አነጋጋሪ አስተያየት የተሰጠው ቶዮታ የሙከራ ደረጃ ላይ ያሉ የሃይድሮጅን መኪኖቹን፣ በተለይም የ GR Yaris ሞዴልን በይፋ ባሳየበት በጃፓኑ የሱፐር ታይኪዩ (Super Taikyu) የጽናት እሽቅድምድም ውድድር ላይ መሆኑ ታውቋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የማሳጅ ቤቶች ስራ እና የነዋሪው ቅሬታ
👉
https://youtu.be/Ergmq7Iigxw
read more
በስፔን ከ39,000 ሄክታር በላይ መሬት በሰደድ እሳት ተቃጥሏል ተባለ
👉በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሰደዳቸውም ተመላክቷል
ነሐሴ 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ስፔን ውስጥ ከ39,000 ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት በሰደድ እሳት መቃጠሉን የሀገሪቱ... read more
ከ’ኒያ ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እሌኒ ዳምጠው ጋር የተደረገ ቆይታ
https://youtu.be/mGoRJ_xcaHE
read more
የፓርቲ አመራሮችን ለማሰልጠን የተደረሰው ስምምነት አግባብ ያለውና የፖለቲካ ምህዳሩን ሊያሻሽለው የሚችል ነው ተባለ
ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተለያየ ሃሳብ እና አቋም ያላቸው ከ60 በላይ የሚሆኑ ሃገርና... read more
ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦችን እንዳስወገደ የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ
ኅዳር 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ 6 ሚሊየን 44ሺህ 402 ብር የሚያወጣ ግምት ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦች ናቸው... read more
ዕድሜያቸው ለትምህርት ደርሶ፣ ትምህርት ያልጀመሩ ዓይነ ስውራን ቁጥር አሁንም ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሀገሪቱ ከሚገኙ አካል ጉዳተኞች መካከል 11.8 በመቶ ያህሉ ብቻ የትምህርት ዕድል እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ... read more
በአሜሪካ እና የብሪክስ አባል አገራት መካከል የሚፈጠር ውጥረት እና የንግድ ፉክክር ለአዳጊ ሃገራት የኢኮኖሚ ውድቀት ሊፈጥር ይችላል ተባለ
ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓለም አቀፉ ገበያ ላይ በበላይነት ያለው የመገበያያ ገንዘብ የሀገራቱን የፖለቲካ ሁኔታ የሚወስን እንደመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ከበለጸጉ... read more
“የዓለማችን ቆሻሻው ሰው” ተብለው የሚጠሩት ኢራናዊው አሙ ሀጂ ከ60 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በታጠቡ ማግስት ህይወታቸው አለፈ
ታህሳስ 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከ60 ዓመታት በላይ ገላቸውን ሳይታጠቡ በመቆየት "የዓለማችን ቆሻሻው ሰው" የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቷቸው የነበሩት ኢራናዊው አሙ... read more
“ሚሳኤሎቻችን ባይኖሩ ኖሮ እንደ ጋዛ እንሆን ነበር” — የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ሀገራቸው የያዘችው የባሊስቲክ ሚሳኤል ፕሮግራም በፍፁም ለድርድር የማይቀርብ መሆኑን በፅኑ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ... read more
ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ ለአገር ውስጥ ጥቅል ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጠቃሚ እንደሚሆኑ ተጠቆመ
ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሥራ እንዲጀምሩ አዋጅ... read more
ምላሽ ይስጡ