ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሊቨርፑል በዚህ ክረምት የተከላካይ መስመሩን ማጠናከር ዋነኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አድርጎ ወደ ዝውውር ገበያው ለመግባት መዘጋጀቱ ተዘግቧል። በክለቡ የግራ ተከላካይ መስመር ላይ ሚሎስ ኬርኬዝ እና ኮስታስ ሲሚካስ በመኖራቸው ቦታው አስተማማኝ ቢሆንም፤ በመሀል ተከላካይ ክፍል ግን ያለው አማራጭ አናሳ ሆኗል። በተለይም የኢብራሂማ ኮናቴ ክለቡን ለቆ መውጣት፣ እንዲሁም የቪርጅል ቫን ዳይክ እና ጆ ጎሜዝ ውል ወደ መጨረሻው ዓመት መግባቱ ሊቨርፑልን ልምድ ላላቸው ተከላካዮች እጥረት ዳርጎታል። ምንም እንኳን ክለቡ ወጣቱን ጄርሚ ዣኬን ከሬኔ ማስፈረም ቢችልም፣ እንዲሁም ጆቫኒ ሌኦኒ ከከባድ የጉልበት ጉዳት ቢያገግምም፤ ሊቨርፑል ለረጅም እና ለአጭር ጊዜ የሚጠቅመውን አስተማማኝ ተከላካይ ለማግኘት የኮከቦችን ዝርዝር አዘጋጅቷል።
ሊቨርፑል በዝርዝሩ ቀዳሚ ያደረገው በአውሮፓ በስፋት ከሚፈለጉ ተከላካዮች አንዱ የሆነውን የስፖርቲንግ ሊዝበኑን ጎንካሎ ኢናሲዮን ነው። ክለቡ ኳስን ከኋላ መስርቶ ወደ ፊት ማሳለፍ የሚችል እና የግራ እግር ተጫዋች የሆነ ተከላካይ የሚፈልግ ሲሆን፤ ይህ የ24 ዓመቱ ተጫዋች ለቫን ዳይክ ምርጥ አጋዥ ይሆናል ተብሎ ይታመናል። ለስፖርቲንግ ከ250 በላይ ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለውና ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ቋሚ ተሰላፊ መሆን የቻለው ኢናሲዮ፣ በውሉ ላይ የ52 ሚሊዮን ፓውንድ ማፍረሻ ያለው በመሆኑ ለሊቨርፑል ተመጣጣኝ የገንዘብ አማራጭ ሊሆን ይችላል።
ምንም እንኳን ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ተጫዋቹን ቀደም ብለው ቢፈልጉትም፣ ሊቨርፑል ግን የኮናቴን ምትክ በአስቸኳይ ስለሚፈልግ ተጫዋቹን ለማግኘት የተሻለ ዕድል አለው ተብሏል። ከኢናሲዮ በተጨማሪ የናፖሊው ሳም ቢውኬማ፣ የቶተንሃሙ ወጣት ሉካ ቩስኮቪች እና የኖቲንግሃም ፎረስቱ ሙሪሎ በሊቨርፑል የዝውውር ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ክለቡ የተከላካይ መስመሩን የወደፊት ዕድል ለመገንባት በሚቀጥሉት ሳምንታት ጠንካራ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ለአይነ ስውራን ቤተሰቦቹ ሲል ብቻውን 4 ኪሎ ሜትር መንገድ የገነባው አባት
መስከረም 09 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በኔፓል ዳንግ ግዛት በሚገኝ ሳታሌ መንደር ውስጥ የሚኖሩት አቶ ቻንድራቢር ኦሊ፣ ለአይነ ስውር ባለቤታቸውና... read more
በመዲናዋ ፍቃድ እና ህጋዊነት ያላቸው ተንቀሳቃሽ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች 9ሺህ ብቻ ናቸው ተባለ
ሐምሌ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እንዳስታወቀው አሁንም ድረስ ያለ ፈቃድ የሚንቀሳቀሱ የሞተር ሳይክል ተጠቃሚዎች ስለመኖራቸው አስታውቋል፡፡
መናኸሪያ... read more
በዓለም ወካይ ቅርስነት በተመዘገበው የ”ሔር ኢሴ” ባሕላዊ ሕግ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ
በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም የማይዳሰስ ወካይ ቅርስነት በተመዘገበው ''ሔር ኢሴ'' በተሰኘው የኢሳ ማህበረሰብ ባሕላዊ መተዳደሪያ ሕግ... read more
በወልዲያና አካባቢው የሃይል አቅርቦት ተቋረጠ
ከአላማጣ - ኮሞቦልቻ የተዘረጋ 230 ኪ.ቮ ከፍተኛ ሃይል አስተላለፊ መስመር ላይ ብልሽት ስላጋጠመ ከዶሮ ግብር ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሃይል ያገኙ... read more
ሞሮኮ ከአለም ዋንጫ ዝግጅት ጋር በተያያዘ በርካታ ውሾችን እየገደለች እንደምትገኝ ተገልጿል
ሕዳር 04 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ሞሮኮ ለዓለም ዋንጫ ዝግጅት በሺዎች የሚቆጠሩ ውሾችን በመንገድ ላይ በመግደል መከሰሷም ተሰምቷል።
የ2030 የዓለም ዋንጫን... read more
በምክር ቤቱ የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴ አመራሮች ተሰየሙ
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ27ኛ መደበኛ ስብሰባው በምክር ቤቱ የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴ አመራሮችን ሰይሟል፡፡
አፈ ጉባኤ... read more
ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የደረሱ ሰብሎችን እንዳይጎዳ በጊዜ ምርት ለመሰበሰብ ቅደመ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ክልሎች ገለጹ
ጥቅምት 10 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) አልፎ አልፎ የሚከሰተው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የደረሱ ሰብሎችን እንዳይጎዳ ሁሉን የህብረተሰብ ክፍሎች ያሳተፈ የምርት መሰበሰብ... read more
ሲፈን ሀሰን ነሀሴ ወር ላይ በሚደረገው የሲድኒ ማራቶን ላይ እንደምትካፈል አሳወቀች
ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰኝ በመጪው መስከረም ወር ላይ በሀገረ ጃፓን ቶኪዮ ከተማ ላይ በሚከናወነው... read more
የጥብቅና ሙያ በገቢ ግብር ተካቶ እንደማንኛውም የንግድ ሥራ መታየት የለበትም ሲል የፌደራል ጠበቆች ማህበር ገለጸ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ የጥብቅና ሙያ እንደሌላው... read more
102 ዓመቱ ጃፓናዊ አዛውንት የፉጂ ተራራን በመውጣት የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገቡ
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በጃፓን የ102 ዓመቱ አዛውንት ኮኪቺ አኩዛዋ የፉጂ ተራራን በመውጣት የአለማችን ትልቁ የዕድሜ ባለፀጋ ተራራ ወጪ በመሆን... read more
ምላሽ ይስጡ