ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “አካታች የባንክ አገልግሎት ለሁሉም!” በሚል መሪ ቃል፤ ከሰኔ 2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2019 ዓ.ም ድረስ ቆይታ የሚኖረውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነትን የማስፋት ንቅናቄ በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።
ሁለተኛው ብሔራዊ የፋይናንስ አካታችነት ስትራቴጂ እንደሚያሳየው፣ በኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነት ወደ 45 በመቶ ቢያድግም፤ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎትን ሊጠቀም ይችላል ተብሎ ከሚታሰበው የኅብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሆነው 12 በመቶው ብቻ እንደሆነ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገልጸዋል።
በሀገራችን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኅብረተሰብ ክፍል፣ ከሃይማኖታዊ ዕሴቶቹ ጋር የሚስማማ የባንክ አገልግሎት ስላልተዘጋጀለትና ተደራሽ ስላልሆነ ከአካታች የባንክ አገልግሎት ርቆ መቆየቱን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። በተለይም የባንክ አገልግሎት ተደራሽነቱ አናሳ መሆን፣ ሴቶች ከፋይናንስ ሥርዓቱ ተጠቃሚነት በእጅጉ እንዲገለሉ ማድረጉንም አብራርተዋል።
በመሆኑም መንግሥት በኢትዮጵያ የፋይናንስ አካታችነትን እና ተደራሽነትን የሚያጎለብቱ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ያሉት አቶ አቤ ሳኖ፤ ከእነዚህም አንዱ ብሔራዊ ባንክ ከFSD Ethiopia ጋር በመተባበር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን ለማስፋፋት የሚሠራው ሥራ መሆኑን ጠቅሰዋል። ንግድ ባንክ ከFSD Ethiopia ጋር በመተባበር በአፋር፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ አማራ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ፣ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነት ዝቅተኛ በሆነባቸው ከ241 በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች እና የገጠር ቀበሌዎች የሚተገበር የንቅናቄ መርሃ ግብር ማስጀመሩን ገልጸዋል። ፕሮጀክቱ አምስት ሚሊዮን ለሚደርሱ ዜጎች ስለወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ግንዛቤ የመፍጠር ዓላማን ያነገበ መሆኑም ተነግሯል።
ባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ከጀመረበት ጥቅምት 2006 ዓ.ም ጀምሮ፣ በወለድ ምክንያት ከፋይናንስ ሥርዓቱ ተገልለው የነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወደ መደበኛው የኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲገቡ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በሰሜኑ ጦርነት በክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶች አሁንም ሙሉ በሙሉ ተጠግነው ባለመጠናቀቃቸው በዛፍ ስር ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን የትግራይ ክልል አስታወቀ
የፌዴራል መንግስት፣ የአለም ጤና ድርጅት /WHO/ን ጨምሮ በውጪ ሃገራት ያሉ የትግራይ ተወላጆች የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የበጀትና የቁሳቁስ ድጋፎችን... read more
የፓርቲ አመራሮችን ለማሰልጠን የተደረሰው ስምምነት አግባብ ያለውና የፖለቲካ ምህዳሩን ሊያሻሽለው የሚችል ነው ተባለ
ኅዳር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተለያየ ሃሳብ እና አቋም ያላቸው ከ60 በላይ የሚሆኑ ሃገርና... read more
የአድዋ ድልን በስነ-ስዕል በመግለጽ ረገድ ገና እንዳልተሰራበት የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ
የካቲት 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ታሪክን በሙዚቃ፣ በስዕል፣ በተውኔት እና በሌሎች ኪነጥበባዊ ስራዎች የመግለጽ እድል ቢኖርም ኢትዮጵያ ታሪካዊ ሁነቶቿን በተገቢው መልኩ... read more
በአማራ ክልል ያለው ግጭት ከቀጠለ በርካታ ወገኖች ለአዕምሮ ጤና ችግር ይጋለጣሉ ተባለ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር በአማራ ክልል ከሕወሀት ጦርነት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያሉ ግጭቶች እና ውጥረቶች በተማሪዎች፣ በሴቶች፣... read more
ዘመናዊ የባህል፤ቅርስና ቋንቋ መልክዓ ምድረርን ለመፍጠር ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል ተባለ
ዘመኑ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የባህል፣ ቅርስ እና ቋንቋን ለመመዝገብና ለመሰነድ ከፍተኛ እድል የሚሰጥ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ... read more
ጨረቃ እየዛገች ነው – ሳይንቲስቶች
መስከረም 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጠፈር ተመራማሪዎች በጨረቃ ምሰሶዎች አቅራቢያ ሄማታይት የተባለ የማዕድን ዓይነት (በተለምዶ ዝገት በመባል የሚታወቅ) ማግኘታቸው አስገራሚ... read more
አጀንዳቸውን ለሚያቀርብ የታጠቁ ሃይሎች ኮሚሽኑ ሙሉ ዋስትናን ማቅረብ እንደሚችል ተገለጸ
ጥቅምት 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለታጠቁ ሃይሎች በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም አብዛኛዎቹ ጥሪውን እንዳልተቀበሉ ኮሚሽኑ በተደጋጋሚ ሲገልፅ መቆየቱ... read more
በሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከ24 ማለፉ ተገለጸ
👉እሳቱ ዛሬም ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ እንደቀጠለ ነው ተብሏል፡፡
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማ በተከሰተው ሰደድ... read more
ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ትውልዱ እንዲያውቀው በማድረግ ዘርፉን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚገኙ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ትውልዱ እንዲያውቃቸው ማድረግ እንደሚገባ የትንፋሽ ውበት የዋሽንት ኮንሰርት አዘጋጅ አቶ... read more
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞው ዋና ስራ አስፈጻሚ ካፒቴን መሐመድ አሕመድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ኅዳር 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ን እ.ኤ.አ ከ1980 እስከ 1991 ዓ.ም በዋና ስራ አስፈፃሚነት በማገልገል ለአየር መንገዱ... read more
ምላሽ ይስጡ