ሰኔ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ተግባራዊ በሆነው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ውስጥ የሀገር በቀል እውቀት ከጽሑፍ ያለፈ ለትግበራ የተዘጋጀ አካሄድ የለም ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጤና መምህር እና በሀገር በቀል እውቀት ዙሪያ ምርምር የሚያደርጉት ፕሮፌሰር መንገሻ አድማሱ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የተጠና ጥናት ቢኖረውም ወደ ትግበራ አልገባም የሚሉት ባለሙያው፣ ሰነድ ማዘጋጀትና መተግበር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ሌሎች ተቋማትም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ሀገር በቀል እውቀቶችን አካቶ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲተገበር ለማስቻል የማስፈጸሚያ ሰነድ እየተዘጋጀ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የሀገር በቀል እውቀትና የማህበረሰብ ትስስር ዴስክ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላም አለሙ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
ፍኖተ ካርታው መተግበር ከጀመረ ዓመታትን ያስቆጠረ እንደሆነ የተናገሩት ዳይሬክተሯ፣ ነገር ግን የሀገር በቀል እውቀትን አካቶ ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ለማስቻል የሚቀሩ ስራዎች መኖራቸውን አምነዋል።
ዳይሬክተሯ በሚመሩት የሀገር በቀል እውቀትና የማህበረሰብ ትስስር ዴስክ በኩል የማስፈጸሚያ መመሪያ ሰነድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። ይህ ብቻም ሳይሆን አሁን ላይ በካሪኩለም ወይም በስርዓተ ትምህርት ክፍሉም በኩል እንዲሁ የማስፈጸሚያ መመሪያዎች መቀረጻቸውን ገልጸዋል። ስርዓተ ትምህርቱ ሙሉ በሙሉ የሀገር በቀል እውቀትን እንዲያካትት ለማስቻል ነው በቂ ቅድመ ዝግጅት ያስፈለገው ሲሉም አክለው ተናግረዋል።
አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መቅረጽ ያስፈለገው ሀገር በቀል እውቀቶችን ለማካተት እንደሆነ ካሁን ቀደም የትምህርት ሚኒስትሩ መናገራቸው ይታወሳል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በኢትዮጵያ የሚደረጉ የዓለም አቀፍ ተቋማት እና የሀገራት መሪዎች ይፋዊ ጉብኝቶች ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር የሚያግዙ መሆናቸው ተገለጸ
ግንቦት 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ፤ የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም ዳይሬክተር ጉብኝት ኢትዮጵያ ለጀመረችው ሰፊ... read more
የገዛ ልጃቸውን ለህክምና ወጪ የሸጡት አባት ልብ ሰባሪ ታሪክ
ግንቦት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአፍጋኒስታን የሚገኘው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ እና ስራ አጥነት ወላጆችን አስገዳጅ እና ልብ ሰባሪ ውሳኔዎች ላይ... read more
ኢንተርኔት በብርሃን ፍጥነት፣ ጃፓን የዓለም ሪከርድን ሰበረች!
መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የጃፓን ተመራማሪዎች ኢንተርኔት በብርሃን ፍጥነት ማስተላለፍ የሚያስችል አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግበዋል። ተመራማሪዎቹ በሴኮንድ 402... read more
ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተበላሹና ደረጃቸውን ያልጠበቁ የመዋቢያ ምርቶች በቁጥጥር መዋላቸው ተገለጸ
ነሐሴ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በበጀት አመቱ የተበላሹና ደረጃቸውን ያልጠበቁ የመዋቢያ ምርቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን... read more
የዶናልድ ትራምፕ በዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ላይ እየጨመረ ያለው ጫና
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪን በሩሲያ ላይ የሚደረገውን ጦርነት በተመለከተ ጫና... read more
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የውይይት አጀንዳውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከበ
ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በ7 ክፍሎችና በ64 ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ያዘጋጃቸውን አጀንዳ በዛሬው እለት ለኢትዮጵያ... read more
በአዲስ አበባ ከተማ የእብድ ዉሻ በሽታ የተገኘባቸዉን ዉሾች የማስወገዱ ስራ በመደኛ ሁኔታ መቀጠሉ ተገለጸ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ የሺዳኛ በላይሁን የእብድ... read more
በዓመት ሁለት ጊዜ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት የቦክስ ውድድር ለማካሄድ መታቀዱ ተገለጸ
ነሐሴ 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የፕሮፌሽናል ቦክስ ስፖርትን ለማሳደግና በዘርፉ ያሉ ስፖርተኞችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት... read more
በገና በዓል ከ50 በላይ አሸከርካሪዎች ጠጥተው ሲያሽከረክሩ መገኘታቸውና መቀጣታቸዉ ተገለጸ
ጥር 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በ9ኙ ክፍለከተሞች በተመረጡ ቦታዎች በተካሄደ ቁጥጥር የአልኮል ትንፋሽ ምርመራ ከተደረገላቸው 1 ሺ... read more
አዲስ የምርመራ ውጤት ሰውን ልዩ የሚያደርገው የዲ ኤን ኤ ክፍል በአንጎል እድገት ላይ ያለውን ሚና አሳይቷል
በዱክ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ማእከል የተመራ አዲስ ጥናት ሰዎችን ከሌሎች ዝርያዎች የሚለይ እና በአንጎል እድገት ላይ ወሳኝ ሚና የሚጫወት የዲ ኤን... read more
ምላሽ ይስጡ