ግንቦት 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰውን ልጅ ወደ ማርስ እና ጨረቃ ለማጓጓዝ እንዲሁም በህዋ ላይ በቋሚነት ለማስፈር ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ የተሻገረበት አስገራሚ ሙከራ ተደረገ። የቻይና ሳይንቲስቶች የሰው ልጅ በህዋ ላይ መባዛት (Human Reproduction) የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን በጥልቀት ለማጥናት በጥናት ላይ የተመሰረቱ ሰው ሰራሽ የሰው ልጅ ሽሎችን (Artificial Embryo Models) ወደ ቲያንጎንግ የጠፈር ጣቢያ ልከዋል።
ከግንድ ሴል (Stem Cell) የተሰሩት እነዚህ የሽል ሞዴሎች የሰው ልጅ ከተረገዘ ከ14 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚያሳየውን እጅግ የመጀመሪያ ደረጃ የዕድገት ሂደት ሙሉ በሙሉ መኮረጅ የሚችሉ ናቸው። ሆኖም ግን እነዚህ ሞዴሎች ወደ እውነተኛ የሰው ልጅ ፅንስ ወይም ሙሉ ሰውነት ሊያድጉ የማይችሉ በመሆናቸው ምንም ዓይነት የስነ-ምግባር ጥያቄ እንደማያስነሱ ተመራማሪዎቹ አረጋግጠዋል።
ሳይንቲስቶቹ በዚህ ሙከራ በህዋ ላይ ያለው አነስተኛ የስበት ኃይል እና የኮስሚክ ጨረራ በሰው ልጅ የሴል ዕድገት፣ በጂን መገለጫዎች እና በውስጥ አካላት አወቃቀር ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለማወቅ ፈልገዋል።
ይህ ታሪካዊ ሙከራ ወደ ጠፈር የተላከው በቅርቡ በተኮሰችው ቲያንዙ-10 (Tianzhou-10) በተባለችው የጭነት መንኮራኩር አማካኝነት ሲሆን፣ ሙከራው እየተመራ ያለው በቻይና የሳይንስ አካዳሚ የስነ-ሕይወት ተቋም (Chinese Academy of Sciences’ Institute of Zoology) አማካኝነት ነው።
ሳይንቲስቶች እንዳረጋገጡት ይህ ሽል በህዋ ላይ እንዴት እንደሚንቀሳቀስና እንደሚያድግ የሚታወቅበት ሚስጥር፣ የሰውን ልጅ ወደፊት በጠፈር ጣቢያዎች ወይም በሌሎች ፕላኔቶች ላይ በቋሚነት ለማስፈርና አዳዲስ ቅኝ ግዛቶችን ለመመስረት ለሚደረገው ጉዞ እጅግ ወሳኝና የመጨረሻው ቁልፍ መረጃ ሆኖ ያገለግላል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ድጋፍ የሚሹት በጎ አድራጎት ድርጅቶች..👉
https://youtu.be/eMP3cELi4bk
read more
ራሚስ ባንክ ከ2 ሚሊዮን በላይ አክሲዮኖቹን በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ማስመዝገቡን አስታወቀ
ራሚስ ባንክ 2 ሚሊዮን 101 ሺህ 106 አክሲዮኖችን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በይፋ ማስመዝገቡንና በኢትዮጵያ ሰነዶች ማኅበራዊ ገበያ (ESX) ዋና... read more
ባለፉት 11 ወራት 1ሺሕ 400 በህገ ወጥ ተይዘው የነበሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለመንግስት ተመላሽ እንዲሆን መደረጉ ተገለጸ
ሰኔ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 11 ወራት 1ሺሕ 400 የሚሆኑ በህገ ወጥ አካላት ተይዘው የነበሩ የጋራ... read more
የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት ከሀገር ሸሹ፤ ወታደራዊ ክፍሎች ተቃዋሚዎችን ተቀላቀሉ!
ጥቅምት 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በማዳጋስካር እየተባባሰ የመጣውን የፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ፣ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ከስልጣናቸው በመልቀቅ ከሀገር መውጣታቸው ተዘገበ። ፕሬዚዳንቱን ለቀው እንዲሸሹ... read more
ቻይና ጃፓንን አስጠነቀቀች፡ የታይዋን አቅራቢያ የሚሳኤል ማሰማራት እቅድ ‘በጣም አደገኛ’ ሆኗል ተብሏል
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቻይና የታይዋን ደሴት አቅራቢያ የሚሳኤል ማሰማራት እቅድ ጋር በተያያዘ ጃፓንን በግልጽ አስጠንቅቃለች። የቻይና መንግሥት የውጭ ጉዳይ... read more
ሱዳን ለ30 ወራት ተዘግቶ የቆየውን የካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ ልትከፍት ነው
ጥቅምት 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለፈው ሚያዚያ 2023 በአገሪቱ የጦር ኃይል እና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ በኋላ... read more
የዓለምን ቀልብ የሳበው የሰሜን ኮሪያ የባህር ላይ ወታደራዊ ጉልበት ትርኢት
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በባህር ኃይል የጦር መርከብ ላይ በመገኘት፣ አዳዲስ የክሩዝ እና... read more
አስተግባሪ ያጣው የትንባሆ ቁጥጥር
👉
https://youtu.be/e-KBshnYaRk
read more
በኢንዶኔዢያ የመርከብ የእሳት አደጋ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ ከ500 በላይ ተሳፋሪዎች ወደ ባህር በመዝለል ሕይወታቸውን አተረፉ
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢንዶኔዢያ ሱላዌሲ የባህር ዳርቻ ላይ አንድ ጀልባ በእሳት ከተያያዘ በኋላ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ፣ ከ500 በላይ... read more
የእስራኤል እና የኢራንን ወቅታዊ የህዝብ ብዛትና የቆዳ ስፋት እንዲሁም #ወታደራዊ አቅም ሲዳሰስ
🔰የእስራኤል ዝርዝር መረጃ‼️
እስራኤል በ2025 የህዝብ ብዛቷ ወደ 9,517,181 የተጠጋ ሰዎች እንዳሏት መረጃዎች አመላክተዋል።
የቆዳ ስፋት ደግሞ 22,145 ካሬ ኪሎ ሜትር እንደሆነና... read more
ምላሽ ይስጡ