ግንቦት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም ፖለቲካ ትኩረት አሁንም በቻይና መናገሻ ከተማ ላይ ያረፈ ሲሆን የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን በታላቁ የሕዝብ አዳራሽ ካስተናገዱ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በዚሁ ታሪካዊ ሥፍራ በደማቅ ወታደራዊ ክብር ተቀብለዋል።
የቻይና ወታደሮች፣ የጦር ኃይሎች የሙዚቃ ባንድ እና የሩሲያና ቻይናን ባንዲራዎች የሚያወገረግቡ ሕፃናት በቤጂንግ መሃል ለፕሬዚዳንት ፑቲን ከፍተኛ ክብር የታየበት አቀባበል አድርገውላቸዋል። በመቀጠልም ሁለቱ መሪዎች በጠበበ እና በሰፊው የልዑካን ቡድን መዋቅር የፊት ለፊት ውይይት ያደረጉ ሲሆን በውይይቱም ላይ የንግድ እና የኢነርጂ ትብብር፣ የዩክሬን ጦርነት፣ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ እንዲሁም በቻይና እና ሩሲያ መካከል ስላለው ስልታዊ አጋርነት በሰፊው መክረዋል።
በዚህ ታሪካዊ ስብሰባ ላይ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ለቻይና ምንጊዜም አስተማማኝ የኢነርጂ አቅራቢ ሆና እንደምትቀጥል በድጋሚ ያረጋገጡ ሲሆን በሌላ በኩል ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወደ ጫካ ሕግ እንዳይመለስ እና የኃያላን ፍላጎት በደካሞች ላይ እንዳይጫን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። አክለውም በመካከለኛው ምስራቅ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
ይህ በሞስኮ እና በቤጂንግ መካከል ያለው ወዳጅነት በደመቀበት በዚሁ ዕለት፣ ቻይና ከዋሽንግተን ጋር ያላትን ግንኙነት ለማመጣጠን ትልቅ እርምጃ መውሰዷን አረጋግጣለች። ቤጂንግ ሁለት መቶ የቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማቀዷን ይፋ ያደረገች ሲሆን፣ ከአሜሪካ ጋር ያለውን የንግድ ስምምነት ለማራዘም ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች። ይህ እርምጃ ቻይና በሞስኮ እና በዋሽንግተን መካከል ያላትን የዲፕሎማሲ እና የንግድ ሚዛን በጥንቃቄ እየጠበቀች መሆኑን ለዓለም ያሳየችበት ትልቅ ኩነት ሆኖ ተመዝግቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በጎንደር ከተማ የአፄ ፋሲለደስ ቤተመንግስት መጠናቀቁ ለጥምቀት የመጡ ታዳሚያን ቁጥር እንዲጨምር አድርጎታል ተባለ
ጥር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከፍተኛ ድምቀት ከሚከበሩ የአደባባይ ክብረ በዓላት መካከል አንዱ የጥምቀት በዓል መሆኑን ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች... read more
ኢትዮጵያ አስከፊ ታሪኳን ያደሰችበት ሻምፒዮና ፍጻሜውን አግኝቷል
መስከረም 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በጃፓን ዋና ከተማ ቶኪዮ ላይ ከመስከረም 3-11 ተካሂዶ ፍጻሜውን አግኝቷል። በውድድሩ... read more
ባለፉት 11 ወራት 1ሺሕ 400 በህገ ወጥ ተይዘው የነበሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለመንግስት ተመላሽ እንዲሆን መደረጉ ተገለጸ
ሰኔ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 11 ወራት 1ሺሕ 400 የሚሆኑ በህገ ወጥ አካላት ተይዘው የነበሩ የጋራ... read more
የዉጭ ሃገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን የሚወስነዉ አዋጅ ህገ-መንግስታዊ ተቃርኖ የለበትም ተባለ
ሰኔ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለ ይዞታ የሚያደረጋቸው ረቂቅ አዋጅ ህገ መንግስታዊ መርሆችን ማዕከል... read more
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሰራ ሂደቱ ምንም አይነት የአገልግሎት መቋረጥ ስጋት አይኖርበትም ተባለ
ይህ የተገለጸዉ የሚዲያ ባለሙያዎች ትላንት የመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎትን እንዲጎበኙ በተደረገበት ወቅት ነዉ።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ... read more
ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለትግራይ ልማት ማህበር የተሰጠ ማሳሰቢያ
ሙሉ መግለጫው ከታች ተያይዟል
ጉዳዩ፡ ማህበሩ በቅርቡ ያካሄደው ጉባኤን ይመለከታል
የትግራይ ልማት ማህበር (ትልማ) በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በመዝገብ... read more
በቼክ ሪፐብሊክ ለተሽከርካሪ ወንበር ተጠቃሚዎች ምቹ መንገዶችን የሚያሳይ ካርታ በይፋ ሥራ ላይ ዋለ
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የቼክ ሪፐብሊክ መንግስት የአካል ጉዳተኞችን ተንቀሳቃሽነት እና ነጻነት ለማሻሻል ያለመ አዲስ አሰራር በይፋ ተግባራዊ... read more
የህብረቱ አባል ሀገራት ልምድ የሚለዋወጡበት ጉባኤ እየተካሄድ መሆኑ ተገለጸ
የካቲት 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) 38ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በነገው እለት የህብረቱ አባል ሀገራትና የክብር እንግዶች በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ከመሪዎች... read more
በበየነ መረብ የሚሰጠው የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና በሙከራ ፈተና ወቅት የሶፍትዌር ችግር ማጋጠሙ ተገለጸ
👉የትምህርት ፈተናዎችና ምዘና አገልግሎት በበኩሉ በሃገር አቀፍ ደረጃ የኮምፒውተር ድጋፍ ሰጪ ቡድን አቋቁሞ ችግሩን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ገልጿል::
በሞዴል ፈተና ወቅት... read more
የፌዴራል መንግሥት ባስፈለገ እና በተገደበ ሁኔታ በክልሎች ጣልቃ እንዲገባ የሚያስችለው አዋጅ መጽደቁ የዜጎችን ሰላምና ደህንነትን ለማረጋግጥ ያግዛል ተባለ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ የማሻሻያ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል፡፡
የአዋጁ... read more
ምላሽ ይስጡ