ግንቦት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፉ የመጡት የሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) መረጃ ማዕከላት በአቅራቢያቸው በሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ አስከፊ የአካል እና የስነ-ልቦና ጤና እክል እያስከተሉ መሆኑ ይፋ ሆኗል። ማዕከላቱን በማንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙት ግዙፍ ወታደራዊ መሰል ማሽነሪዎች የሚወጣው ድምፅ አልባ ንዝረት ለአካባቢው ማህበረሰብ ታላቅ ስጋት ሆኗል።
በማዕከላቱ አቅራቢያ የሚኖሩ በርካታ ዜጎች በየቀኑ ከፍተኛ የሆነ ራስ ምታት፣ ማዞር፣ የማቅለሽለሽ ስሜት፣ የጆሮ ውስጥ ጩኸት እና ከእቅልፍ እጥረት ጋር የተያያዙ ከባድ የጤና ችግሮች እያጋጠሟቸው መሆኑን በምሬት እየገለጹ ይገኛሉ።
ለዚህ ቀውስ ዋነኛው መንስኤ ከማዕከላቱ የሚወጣው “ኢንፍራሳውንድ” (Infrasound) የተባለው እጅግ ዝቅተኛ ድግግሞሽ ያለው የድምፅ ንዝረት መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን፣ ይህ ንዝረት ከተለመደው የሰው ልጅ የመስማት አቅም በታች በመሆኑ በተራ የድምፅ መለኪያ መሣሪያዎች ላይ ሳይመዘገብ ሙሉ በሙሉ ጸጥተኛ መስሎ የሰውን አካል ግን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳ ነው ተብሏል።
እነዚህ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ሰርቨሮችን ለማቀዝቀዝ የሚያገለግሉ የኢንዱስትሪ ማራገቢያዎችን፣ ተርባይኖችን እና ግዙፍ የናፍጣ ጄነሬተሮችን በቀን 24 ሰዓት ያለ ምንም ማቋረጥ ያንቀሳቅሳሉ። ይህ ቀጣይነት ያለው ውህድ ንዝረት በአካባቢው ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ የሚገኝ ሲሆን፣ አዳዲስ የሰው ሰራሽ አስተዋጽኦ ማዕከላት ግንባታ ወደ መኖሪያ መንደሮች እየተጠጋ መምጣቱ ህዝቡን ክፉኛ አስቆጥቷል።
ከአሰቃቂው የድምፅ እና የንዝረት ብክለት በተጨማሪ እነዚህ ማዕከላት የሚበሉት የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን፣ ለቅዝቃዜ የሚጨርሱት በሚሊዮን የሚቆጠር ጋሎን የከርሰ ምድር ውሃ እና የሚያስከትሉት የአየር ብክለት በአሜሪካውያን ዘንድ ተከታታይ የሰላማዊ ሰልፍ እና የቅሬታ ድምፆች እንዲበራከቱ ምክንያት ሆኗል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በአፍና በከንፈር አካባቢ የሚያጋጥም ቁስል ከየት የመጣ ነው?
👉የህክምና ድህረ ገጾች ስለበሽታው ምን ይላሉ?
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአፍና በከንፈር አካባቢ የሚያጋጥመው ቁስለት ኸርፒስ (Herpes) በሄርፒስ ሲምፕሌክስ ቫይረስ... read more
በዓለም ወካይ ቅርስነት በተመዘገበው የ”ሔር ኢሴ” ባሕላዊ ሕግ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ
በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም የማይዳሰስ ወካይ ቅርስነት በተመዘገበው ''ሔር ኢሴ'' በተሰኘው የኢሳ ማህበረሰብ ባሕላዊ መተዳደሪያ ሕግ... read more
ሩሲያ የድሮን ስጋትን የሚቀይር አዲስ ጥይት ሰራች
👉ከአውቶማቲክ ጠመንጃ ሲተኮስ ወደ ሦስት ተከፍሎ ድሮኖችን የሚያሳድደው “ምኖጎቶቺዬ” በጦር ሜዳ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው! ሐምሌ 03 ቀን... read more
የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት አዋጅ መኖሩን የማያውቁ ተቋማት መኖር የአካል ጉዳተኞች አካታችነት ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ነዉ ተባለ
በሃገራችን የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት አዋጅ ቢኖርም አሁንም የሚታየው የስራ ስምሪት የአካል ጉዳተኛ ሰራተኛውን ያማከለ አሰራር ባለመኖሩ ያለውን የግንዛቤ ክፍተት... read more
የተፋሰሱ ሃገራት ኮሚሽን ሊቋቋም ባለበት ወቅት ግብጽ ወደ ናይል ትብብር መመለሷን ኢትዮጵያ በአጽዕኖት መከታተል አለባት ተባለ
የአባይ ውሃን በፍትሀዊነት እና በምክንያታዊነት ለመጠቀም ከ15 ዓመት በፊት የተቋቋመ የናይል ቤዚ ኢንሼቲቭ ህጋዊ ቢሆንም ግብፅ ውድቅ ማድረጓዋ እና የናይል... read more
በጋምቤላ ክልል አራት ሺሕ የሚደርሱ ዜጎች በየሳምንቱ በወባ በሽታ እየተያዙ ነዉ ተባለ
ታህሳስ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በጋምቤላ ክልል የወባ በሽታ ምርመራ ከሚያደርጉ ከሀምሳ በላይ ሰዎች በበሽታው የተያዙ መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ... read more
የኢትዮጵያ ፖሊስ ጥናት ኢንስቲትዩት ባለፉት 2 አመታት ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር የተገናኘ ጥናት አላካሄድኩም አለ
ጥር 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተቋማት በተለያዩ ጉዳዮች የሚያወጧቸዉን ሪፖርቶች ፖሊሲዎችን ለመፈተሽና ለፖሊሲ ግብዓትነት እየተጠቀምኩባቸዉ ነዉ ሲል የኢትዮጵያ ፖሊሰ ጥናት... read more
በመዲናዋ ሰርግን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈጽሙ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል👉ፖሊስ
በአዲስ አበባ ከተማ በዓላትና ሰርግን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈጽሙ መንገድ የሚዘጉ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።
ሕብረተሰቡ... read more
በ2025 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የአለም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጭ በ29 በመቶ ጨምሯል ተባለ
ሚያዚያ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በቻይና እና አሜሪካ መካከል የተስተዋለው ቀጣይነት ያለው ቀረጥ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጭ ላይ የተወሰነ ተጽዕኖ... read more
በሀገራዊ ምክክሩ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምን አደረጉ?
በሀገራዊ ምክክር ሂደት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሚና ምንድን ነው? ድምፃቸውን ለሕዝብ በማሰማት እና የኅብረተሰቡን ግንዛቤ በማስፋት ረገድ ምን አከናወኑ? በዚህ... read more
ምላሽ ይስጡ