ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተጠቃሚያቸው እያደገ ከሚገኙት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መተግበሪያዎች መካከል አንዱ የሆነው ቴሌግራም ሲወቀስበት የነበረውን የተጠቃሚዎች ደኅንነት ጥበቃን በተመለከተ የአቋም ለውጥ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡
በዚህም ቴሌግራም ከዓለም አቀፍ ተቋም ጋር በመተባበር የሕጻናት የወሲብ ብዝበዛ ይዘቶች በገጹ ላይ እንዳይዘዋወሩ ለመገደብ መስማማቱ ተገልጿል፡፡
ቴሌግራም ለሕጻናት ጥበቃ የሚያደርግ አሠራርን እንዲከተል ለዓመታት ጫና ሲደረግበት ቢቆይም፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ነበር።
ቴሌግራም አብሮት ለመሥራት የተስማማው ‘ዘ ኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን’ ወይም አይደብሊውኤፍ ተቋም የበይነ መረብ አገልግሎት ሰጪዎች ለሕጻናት ጥበቃ የሚገለገሉበት ነው።
የቴሌግራም መሥራች ፓቫል ዱሮቭ ፓሪስ ውስጥ ከታሰረ በኋላ ቴሌግራም ይዘቶች ላይ ቁጥጥር ለማድረግ ተስማምቷል።
ተቋሙ የቴሌግራም ውሳኔ “ለውጥ የሚያመጣ ነው” ብሏል። ሆኖም ግን ቴሌግራም አሁንም ረዥም ጉዞ እንደሚጠብቀው አክሏል።
የተቋሙ ተጠባባቂ ኃላፊ ዴሬክ ሬይሂል “አይደብሊውኤፍን በመቀላቀል ቴሌግራም በዓለም ቀዳሚ ቦታ ያላቸው የጥንቃቄ አካሄዶች በመከተል ይዘቶችን መገደብ ይችላል” ብሏል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ